FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
41.5K subscribers
34K photos
39 videos
9 files
9.46K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የ18ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃ መቻል ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ስፖርታዊ ውድድር አካሄደ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን ሴክተር ኤስት የሚገኙት 18ኛ የኢትዮጵያ  ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ብርሃኑ ረጋሳ የመቻል ስፖርት ክለብ ከተመሰረተ ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስፖርት ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ክለቡን ለማሳደግ በሚደረገው ድጋፍ ግንባር ቀደም በመሆን የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡  

አዛዡ የመቻል 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ እና የገመድ ጉተታ ስፖርታዊ ውድድሩን አሥጀምረዋል።
  
ዘጋቢ የኔብቻ ቦጋለ
ፎቶ ግራፍ ሰናይት ሃይለየሱስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1311🔥2
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የሠራዊቱን ኑሮ ለማሻሻል እና  ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 21 ቀነን 2016 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከመከላከያ ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት  እና ከፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ማዕከል ጋር በመተባበር  በሰነድ ማረጋገጥ እና መመዝገብ እንዲሁም የህግ  ማዕቀፍ እና አሰራር ዙሪያ የምክክር እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ ፋውንዴሽኑ በየጊዜው የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዱ በተቋም ደረጃ በራሱ በሠራዊቱ አባላት በመመስረት የሚገኘው የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን አንዱ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ለሰራዊቱም ሆነ ቤተሰቡ ለችግር ጊዜ ደራሽ እና አጋዥ እንዲሁም በእርጅና ዘመን ምርኩዝ እንዲሆን ታስቦ የተመሰረት በመሆኑ ሁሉም አባል ጠቀሜታውን በሚገባ ተረድቶ አቅሙ በፈቀደ መጠን አክሲዮኑን ሊገዛ ይገባዋል ብለዋል።

ሠራዊቱ በግዳጅ ቀጠናው ሆኖ አክሲዮኑን መግዛት እንዲችል ለማድረግ ወጥ እና ህጋዊ አሰራር ለመዘርጋት  ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሠራዊቱ በየጊዜው የሚያጋጥሙትን ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን  በአካል ተገኝቶ መፈፀምም ሆነ ማስፈፀም ሳይጠበቅበት ካለበት ቦታ ሆኖ የሚያሥፈልጉትን ጥቅሞች እንዲያገኝ ለማድረግ በተቋሙ ባሉ የፍትህ አደረጃጀቶች ስር ባሉ ሙያተኞች አማካኝንት ሰነዶች ተረጋግጠው እና ፀድቀውለት ወደ ፌዴራል የሰነዶች መመዝገብ እና ማረጋገጫ ማዕከል በመላክ የሚፈልገውን አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት  እንዲችል ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን በአዋጁ ላይ በሰፈሩት ድንጋጌዎች መሰረት የውል ሰነድ ማረጋገጥ እና መመዝግብ ስራን ከተቋሙ የፍትህ አካላት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአዋጁ መሠረት ተግባራዊ በማድርግ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

ይህን ማድረግ መቻሉ ደግሞ በአዋጁ ላይ ለዜጎች የተደነገገውን   "የንብረት ማፍራት፤  የመጠቀም እና የማስተላለፍ መብቶችን በማስከበር  የፍትህ ስርዓቱን በማገዝ  የህግ የበላይነትን ማስጠበቅ" የሚሉትን ድንጋጌዎች ሠራዊቱም ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል።

ፋውንዴሽኑ በአዋጁ ወደ ስራ ለመግባት መወሰኑ  እና ለተግባራዊነቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መጀመሩ የተቋሙን የእገልግሎት አስጣጥ ስርዓት በማዘመን  ሠራዊቱን ከአላስፈላጊ እንግልት የሚታደግ ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪም ለፍትህ አካላት በአዋጁ መሠረት የተሰጣቸውን ስራ እና ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ የሚያደርግ በመሆኑ ለዘመናዊ የተቋም ግንባታ ሂደቱ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረውም ከምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ተገልጿል።

ዘጋቢ ኤሊያስ ከለለኝ
ፎቶግራፍ ምስጋናው ከበደ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍227👏4🔥1
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾን ጋር ተወያይተዋል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾን ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ፈረንሳይና ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የቆየ ወታደራዊ ትብብር ያላቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን  በቀጣይም ይህንኑ ትብብር ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

አምባሳደሩ በዕለቱም ከፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትር የተላከውን የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክታቸውን አድርሰዋል፡፡ ዘገባው የሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1612🔥2
መቻል ለኢትዮጵያ የጎዳና ላይ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሁለት ቀናቶች ቀርተውታል።  እሁድ መሥቀል አደባባይ እንገናኝ አይቀርም።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

መቻል በፎቶ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://news.1rj.ru/str/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍183🔥1