FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) – Telegram
FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)
8.51K subscribers
1.31K photos
37 videos
3 files
173 links
ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው
**************
የ2017 ዓ.ም የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
የበዓሉ ሥነ-ሥርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን፤ ሌሊቱን ወደ ስፍራው ሲያቀኑ ያደሩት የበዓሉ ተሳታፊዎች በአሁኑ ሰዓት በዓሉን አድምቀውታል።
ከአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ወደ ሆረ ፊንፊኔ የተመሙት የበዓሉ ታዳሚዎች በባህሉ መሰረት ለፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ ላይም ሲሆኑ፤ በባህላዊ አልባሳት ያጌጡ ወጣቶችም በቡድን ቡድን እየሆኑ ባህላዊ ዜማዎችን በማዜም በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።
📷 በሜሮን ንብረት ፣ በአሰግድ ሲሳይ እና በአፎሚያ ክበበው
#ኢሬቻ #etv #EBC
👍2
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ድምቀቶች
📷 በሜሮን ንብረት ፣ በአሰግድ ሲሳይ እና በአፎሚያ ክበበው
#ኢሬቻ #etv #EBC
👍2🤣1👻1
በሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከተለያዩ ከሀገሪቱ አከባቢዎች የመጡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

ተሳታፊዎች በየብሔሩ ጭፈራና ዜማ በዓሉን እያደመቁ ይገኛሉ ።
በትዕግስቱ ቡቼ
🔥2