FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) – Telegram
FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)
8.51K subscribers
1.31K photos
37 videos
3 files
173 links
ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
ይገምቱ

የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ

በ35ኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቀው የጥሎ ማለፍ መርሃግብሮችተጀምረዋል።

ከእነሱ መካከል ደቡብ አፍሪካ  ከ ካሜሮን የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ በቀጥታ ወደ እናንተ እናደርሳለን።

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በሬዲዮ  እና ማህበራዊ  ትስስር ገፆቹ ማለትም  በፌስቡክ እንዲሁም ዩቲዩብ  ያስተላልፋል::
3👍1
ድራማዊ ክስተት በተስተዋለበት ጨዋታ ሊቨርፑል ከፉልሀም አቻ ተለያየ
****

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ ከፉልሀም ባደረገው ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡

በክራቨንኮቴጅ በተደረገው ጨዋታ ፉልሀም ሃሪ ዊልሰን ያደገበት ክለብ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ሊቨርፑል በፍሎሪያን ቨርዝ አቻ ሆኖ ነበር፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቀቀ ተብሎ ሲጠበቅ ኮዲ ጋክፖ በባከነ ሰዓት ሊቨርፑልን አሸናፊ ለማድረግ የተቃረበች ግብ አስቆጥሯል፡፡

ቢሆንም የተጨመረው ደቂቃ ተጠናቆ የዳኛው ፊሽካ ሲጠበቅ ሃሪሰን ሪድ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ የአቻነት ግብ እንዲሁም የሊቨርፑልን የአሸናፊነት ተስፋ የነጠቀች ግብ አስቆጥሯል፡፡

በባከነ ሰዓት ሁለት ግቦች የተቆጠሩበት አዝናኝ ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ተጠናቋል፡፡

በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ እየታገለ የሚገኘው ሊቨርፑል በውድድር ዓመቱ ለ4ኛ ጊዜ አቻ የተለያየ ሲሆን በ34 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
1
ካሜሩን ደቡብ አፍሪካን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
****

በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በተደረገ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ካሜሩን ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

ጁኒየር ቻማዱ እና ክርስቲያን ኮፋን የካሜሩንን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ ማክጎፓ የደቡብ አፍሪካን አንድ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የኮትዲቯር አፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ገና በጊዜ ከአህጉሩ ውድድር ተሰናባች ሆናለች፡፡

በሩብ ፍጻሜው ካሜሩን ከ አስተናጋጇ ሞሮኮ የምትጫወት ይሆናል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
2🥰1
"እጩ መሆኔ ያስደስታል ፤አሸንፌ ሀገሬን ማኩራት ግን ህልሜ ነው"

ማርሸት ዘውዱ/የአፍሪካ ምርጥ የቴኳንዶ ዳኛ እጩ/

ማስተር ማርሸት ዘውዱ "የአፍሪካ ምርጥ ሴት የቴኳንዶ ዳኛ" ሽልማት እጩ ሆናለች የአፍሪካ ቴኳንዶ ዩኒየን በሚያዘጋጀው የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ሴት ዳኛ ሽልማት ላይ በእጩነት የቀረበቸረዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ማስተር ማርሸት ዘውዱ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አትሌት እና በተጫዋችነት ካሳለፈችው ስኬታማ ጊዜ በኋላም የብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሀገሯን በታማኝነት አገልግላለች።

‎በአሁኑ ወቅት ኢንተርናሽናል ማስተር እና ኢንተርናሽናል ዳኛ በመሆን በዓለም አቀፍ መድረኮች ስሟን እያስጠራች ትገኛለች፡፡

ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የመሰንብቻ ፕሮግራምም ማስተር ማርሸት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

በምን ምክንያት እጩ ሆንሽ?

✍️ "እውነት ለመናገር ምርጫም እንዳለ አላወቅኩም ነበረ፤ የራሴን ጥረት፣ የራሴን ስራ ወይም ደግሞ የራሴን እውቀት ለማሳደግ ጥረት ላይ ያለው ገና ጀማሪ ዳኛ ነኝ አፍሪካን ቴኮንዶ ዩኒየን በራሱ መስፈርት መርጦ ምርጥ አራት ውስጥ ለመግባት ችያለሁ፡:"

✍️ "እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ እና የስፖርት ቤተሰብ ነው እኔም እኩል ምርጫውን ያየሁት ስለዚህ ከዚህ በኋላ ግን አንደኛ ለመውጣት ከአራታችን ናይጄሪያ፣ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ኮኮትዲቯር ጋር ነው እየተፎካከርኩ ያለሁት፡፡"

✍️ " እስከአሁን ባለዉ በህዝብ ድምፅ ነዉ እየተመረጥን ያለነዉ፤ፌስቡክ ላይ አፍሪካን ቴኳንዶ ዩኒየን የሚል ገፅ አለ እዛ በተቀመጠዉ ሊንክ መምረጥ ይቻላል፡፡"

✍️ "በህዝብ ድምጽ ነው ምርጫዉ ሙሉ ለሙሉ እስካሁን እንደ ጻፉት የመጨረሻውን ምርጫ በህዝብ ይመስለኛል ግን የነሱም ደግሞ ሌላ መስፈርት ሊኖራቸው ይችላል እሱን በግልጽ አላወቅኩም ፡፡"

እጩ መሆንሽ ምን ትርጉም አለዉ?

✍️ "አሁን ላይ የመጨረሻ ዕጩ ዉስጥ በመግባቴ ሴቶች እንደሚነሳሱ አስባዉ በዛው ልክ ለኔ እውነት ለመናገር አሁን ላይ ትልቅ የቤት ስራ ነው ቢሆንም ደስ ብሎኛል፡፡"

✍️ "እንደ ሀገር ደግሞ ስትድሄድ ኢትዮጵያ ነው የምትጠራው በማርሸት ስር እና እሱ ደግሞ በጣም ሌላ የሚያስደስት ክፍል ነው እና ብዙ በጣም ብዙ ወጣቶች ተጫዋቾችም ዳኞችም መሆን የሚፈልጉ ሴቶች አሉ እና ከሰራን መድረስ እንደምንችል ማሳያ ይሆናል፡፡"

የስራሽ ፈታኝ ነገር ምን ይሆን?

✍️ "ምንም ጥያቄ የለውም በጣም በጣም ብዙ ፈተናዎች አሉት መጀመሪያ ራሱ ሴትነት ራሱ ፈተና ነው ቢሆንም በእኔ በእኔ እምነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው በቴኳንዶ ውስጥ ደግሞ ብዙ ህመሞች ብዙ ግጭቶች ብዙ ጉዳቶች አሉት፡፡"

✍️ "እኔ የሁለት ልጆች እናት ነኝ ብዙ ጊዜ የሚፈራ ነገር አለ ሰውነት ኪሎ ይጨምራል ህመሞቹ ይመጣሉ ግን እሱ ሁላ ይሄኛው ፈጣሪ የሚሰጥህ ጸጋ ስለሆነ እሱን ተቀብለህ ደግሞ ተመልሰህ መነሳት እንዳለበት ተመልሰህ መውጣት እንዳለብህ ምንም የሚገድበን ነገር እንደሌለ ራስን ማሳመን አለብን፡፡"

✍️ "እንችላለን ማለት አለብን እንችላለን ስንል ግን በባዶ ሜዳ አይደለም እየጣርን እየተማርን የተለያዩ ኮርሶች እድሎች ካሉን እነሱን እየወሰድን ራሳችንን ብቁ እያደረግን ለመድረስ የምንችልበት የማንችልበትም ምክንያት ምንም ነገር የለምና መበርታት ይገባል፡፡"

በሞያሽ ባሳከዉ የምትይዉ ግብ ምንድን ነዉ?

✍️ "ባላሰብኩት መንገድ እና ባላሰብኩት ሰአት ነው እዚህ አራት ውስጥ የገባሁት ይሄ ትልቅ ውጤት ነው ለኔም ለሀገሬም ለስፖርቴም ትልቅ እድገት እና ትልቅ ተስፋ የሚያሳይ ውጤት ነው
በተቻለኝ አቅም ራሴን በተለያዩ ነገሮች ብቁ አድርጌ ኢትዮጵያን እስከ ኦሎምፒክ ደረጃ ድረስ በዳኝነት በወርል ቴክንዶ ለማስጠራት ነው አላማዬ፡፡"
3
ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት 10 ዓመታት ጊዜያዊዎቹን ጨምሮ 9 አሰልጣኞችን አሰናብቷል
****
መንገዱ የጠፋበት ማንችስተር ዩናይትድ ከአንጋፋው አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ ሁነኛ አለቃ ማግኝት አልቻለም፡፡

ፖርቹጋላዊውን ሩብን አሞሪም ያሰናበተው ዩናይትድ ባለፉት 10 ዓመታት ብቻ አምስት ቋሚ እና አራት ጊዜያዊ አሰልጣኞችን ቀያይሯል፡፡

👉ባለፉት 10 ዓመታት በቋሚነት የተቀጠሩ አሰልጣኞች እና
የተሰናበቱበት ጊዜ

• ሉዊስ ቫንሃል በ2016 ሚያዚያ ወር ላይ ተሰናበቱ
• ጆዜ ሞሪኒሆ በ2018 ታህሳስ ወር
• ኦሊጎነር ሶልሻየር 2021 ህዳር ወር
• ኤሪክ ቴንሀ 2024 ጥቅምት ወር
• ሩብን አሞሪም 2026 ጥር ወር

በክለቡ የ1 ዓመት ከ4 ወር ቆይታቸው 37 በመቶ ብቻ የማሸነፍ ንጻሬ ያላቸው ሩብን አሞሪም ከዴቪድ ሞይስ በመቀጠል በፍጥነት የተሰናበቱ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
2
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በ2 ዓመታት የውል ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

#ebcdotstream #EBC #Ethiopia #soccer
1
አዲስ ታሪክ ለመስራት ምሽቱን የሚጠብቀው ቡካዮ ሳካ
******

በ21ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ አርሰናል በሜዳው ኤምሬትስ ሊቨርፑልን የሚያስተናግድበት የሳምንቱ ትልቅ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

አርሰናል በሜዳው ከሊቨርፑል ባደረጋቸው ያለፉት ሦስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ቡካዮ ሳካ በሁሉም ግብ አስቆጥሯል፡፡

እንግሊዛዊው አጥቂ በምሽቱ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ከቻለ በኤምሬትስ ሊቨርፑል ላይ በተከታታይ አራት ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመርያው የአርሰናል ተጫዋች ይሆናል፡፡

ከአሁን በፊት የመርሲሳይዱ ክለብ ላይ በአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር የቻለ አንድም የአርሰናል ተጫዋች የለም፡፡

በአንተነህ ሲሳይ
1