Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
አብዮት በጎውን ከክፉው አጃምሎ ጠርጎብናል። ተሻጋሪ ተቋሞች ለመገንባት አላስቻለንም። ለዚህ ነው ሪፎርምን የመረጥነው። እየመዘንን፣ እያነጠርን፣ እየመረመርን የሚበጀንን እንወስዳለን፤ የማይበጀንን እንጥላለን።
በዚህ ዕሳቤ ታላላቅ ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው። የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ ዘርፍ፣ የሕግ፣ የግብርና፣ የትምህርት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርሞችን እያሳካን በመጓዝ ላይ ነን። በትብብር ከሠራን የማናሳካው ሪፎርም፤ የማይደረስበት ብልጽግና አይኖርም።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

👍8
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
"ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት"፦
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***
ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን መኖራችን ያኮራናል። የግዛት ሉዓላዊነት ብቻውን እንደማይቆም ግን ተረድተናል። ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት።
የምግብ ሉዓላዊነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ፣ የበጀት ሉዓላዊነት፣ ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ ናቸው። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበር አዲሱ ዓይነት ዐርበኝነት ያስፈልገናል። የብሔራዊነት ዐርበኝነት።
የብሔራዊነት ዐርበኝነት በተሠማራንበት መስክ ሁሉ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር የጊዜ፣ የዕውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት መሥዋዕትነትን መክፈል ነው። ሀገር በልጆቿ ትገነባለች ትጠበቃለችም።

👍3❤1
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
“ውትድርና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚገባበት እጅግ የተከበረ ሙያ ነው”፦ኮሎኔል ዘውዱ እንድሪስ
******************
ውትድርና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በፍላጎት የሚገበበት እና የሚኖርበት እጅግ የተከበረ ሙያ ነው ሲሉ ኮሎኔል ዘውዱ እንድሪስ ገልፀዋል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የስልጠና ዋና መምሪያ ውስጥ የስርአተ ትምህርት ዝግጅት እና እድገት መምሪያ ሀላፊ የሆኑት ኮሎኔል ዘውዱ እንድሪስ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ ውትድርና የሀገር ፍቅር መገለጫ የሆነ ለሀገር ክብር ዘብ የምንቆምበት ሞያ ነው ብለዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid03cZyF18ay5fuZi7pwPDSwcZcQjXpgRUTLtjB5bcUWwYhvTHASYkJ1VwLsGqMdgusl

Facebook
Ethiopian Broadcasting Corporation
“ውትድርና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሚገባበት እጅግ የተከበረ ሙያ ነው”፦ኮሎኔል ዘውዱ እንድሪስ
******************
ውትድርና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በፍላጎት የሚገበበት እና የሚኖርበት እጅግ የተከበረ ሙያ ነው ሲሉ ኮሎኔል ዘውዱ እንድሪስ ገልፀዋል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር...

👍5
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ትናንት አልቋል። ዛሬም እየተገባደደ ነው። ነገ ግን ገና አልተነካም። ነገን ለመጠቀም ታድያ ዛሬ መሥራት አለብን።
ሕዳሴ ግድብ፤ የገበታ ለሀገርና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፤ መንገዶችና ግድቦች፤ የተቋም ግንባታ ሥራዎች፤ አረንጓዴ ዐሻራና ኢትዮጵያ ታምርት፤ የኮሪደር ልማትና የሌማት ትሩፋት ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ እና የትምህርት ቤት ምገባ፤ ሀገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ፤ ሌሎችም.. ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንሠራቸው ናቸው።
የነገው ትውልድ እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያን እንደሚረከብ ርግጠኞች ነን። ለነገ ዛሬ እየሠራን ነውና።

👍4👏1
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል 1
https://www.youtube.com/watch?v=ct3xlFWEgcI&ab_channel=EBC

"ትልቅ ነገር ስሰራ ነው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የምመጣው እል ነበር ይህም ተሳክቷል " ፦ ሰውመሆን ይስማው
******************
በ1958 ዓ.ም በደራሲ ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ተደርሶ ለንባብ የበቃው እና ዛሬ ላይ 59 ዓመታትን ያስቆጠረው "ፍቅር እስከ መቃብር" ልብ-ወለድ ወደ ተከታታይ ፊልም ተቀይሯል።
በከፍተኛ ወጪ ይህንኑ ስራ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ስመ ጥሩ የፊልም ባለሙያ ሰውመሆን ይስማው ባደረጉት ስምምነት ወደ ምስል ተቀይሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መተላለፍ ጀምሯል።
የተከታታይ ፊልሙ አዘጋጅ ሰውመሆን ይስማው ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ባደረገው የበአል ቆይታ "ይህ እውን በመሆኑ ደስታ ተሰምቶኛል።" ሲል አስታውቋል።
ወደ ምስል የመቀየሩ ሂደት ረዥም እና አድካሚ ነበር ሲል የገለፀው ሰውመሆን በፊልሙ ውስጥ ሰፊውን ስፍራ የሚይዙትን የፊትአውራሪ መሸሻን መንደር ለመገንባት እስከ አምስት ወር ጊዜ ወስዶብናል" ሲልም ሂደቱን ገልፆታል።
የገፀ ባህርያቱ መረጣም ዘለግ ያለ ጊዜን ወስዷል ያለው ዳይሬክተሩ ሰውመሆን ዋናው ገፀ ባህሪ በዛብህን ፍለጋ በልብ ወለዱ የሚጠቀሰው ስፍራ ወደ ሆነው ጎጃም ማንኩሳ ድረስ ተሻግሯል ሲል ይናገራል።
በእዚህም መነሻነት ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ "የጎጃም ማንኩሳ አከባቢ ተወላጅ የሆነውን ተዋናይ መርጠናል" ሲል ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ገልጿል።
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid036tvSGkPqcRSuUH8oYBJVpxxWmuvcqkhUb5WCQFSEUyBZbVJB394fb4uBPQMbRChSl&id=100063770933024

❤1
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ስርጭት ከጀመረ ዛሬ 89 ዓመት ሞላው
****************
በብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ታሪክ ስሙ ቀድሞ የሚነሳዉ "የኢትዮጵያ ሬዲዮ" አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ዛሬ መስከረም 2/2017 ዓ.ም 89 ዓመት አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ስርጭት የጀመረዉ በዛሬዉ እለት መስከረም 2/1928 ዓ.ም ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡-
"ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ በነገሱ በሁለተኛዉ አመት ኢትዮጵያን ከአለም መንግስታት ጋር የሚያገናኝ "ያለ ሽቦ ቃል የሚያሳልፍ መኪና" የሚቆምበት ቤት ሲመሰረት በሀምሌ 14 ቀን 1923 ዓ.ም የመጀመሪያዉን የማእዘን ድንጋይ አኖሩ"
ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የሬዲዮ ጣቢያ በኢትዮጵያ ለማቋቋም ስራ ሲጀምሩ ቴክኖሎጅዉ በአለም ላይ ገና ለጋ ነበር፡፡
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ በሚባለዉ አካባቢ በ1923 ዓ.ም መሰረት የተጣለለት የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ በታህሳስ ወር 1927 ዓ.ም ተጠናቆ በአመቱ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ "ይህ የምትሰሙት ድምፅ የእኔ የንጉሳችሁ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ነዉ" በማለት የመጀመሪያዉን መልዕክት በሬዲዮ ጣቢያዉ አሰሙ፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02167v3QyFdWwqUZcVpS1qzhz5CJpRqymEcuSgnoscripteBuKN5ArZ8SUBaKUmFkpcc3PBl

Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍4👏2❤1
Forwarded from ETV መዝናኛ
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል ሁለት ከደቂቃዎች በኋላ በኢቢሲ
************
በጉጉት የሚጠበቀው ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ዛሬ ከምሽቱ 2፡20 ሰዓት ጀምሮ በኢቢሲ መዝናኛ ቻናል እንዲሁም ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢቢሲ ዜና ቻናል ይተላለፋል።
ፊልሙን ባመቸዎት ጊዜ ለመመልከት የኢቢሲ ወርልድ የዩቲዩብ ቻናልን https://www.youtube.com/@EBCworld ሰብስክራይብ ያድርጉ።

👍10
Forwarded from ETV መዝናኛ
ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል አራት | Fiker Eske Mekaber Episode 4 Etv | Ethiopia | News zena
https://www.youtube.com/watch?v=LKERgaNGJi0&t=17s&ab_channel=EBC
https://www.youtube.com/watch?v=LKERgaNGJi0&t=17s&ab_channel=EBC
👍8
Forwarded from EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ ለታላቅ ፊልም ትዝታዎ!
***********************
"ፍቅር እስከ መቃብር" ከክፍል1 - ክፍል 4 በተከታታይ በአንድ ምሽት ከ2፡00 ሰአት ጀምሮ
የታላቁን ደራሲ ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ መጽሐፍ ታላቁን ተከታታይ ፊልም "ፍቅር እስከ መቃብር"ን ለቀድሞ የኢቲቪ ታላቅ ፊልም ፕሮግራም ማስታወሻ እነሆ ብለናል።
በኢቢሲ በመዝናኛ ቻናል ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ከቤተሰብዎ እና ከወዳጆችዎ ጋር በመሆን ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት በተከታታይ ይመልከቱ። ትዝታዎን ያድሱ ትዝታ ያኑሩ።
በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
#etv #ፍቅርእስከመቃብር

👍4🔥1