FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1) – Telegram
FM ADDIS 97.1(ኤፍ ኤም አዲስ 97.1)
8.5K subscribers
1.29K photos
37 videos
3 files
172 links
ይህ ትክክለኛ የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቴሌግራም ቻናል ነው
Download Telegram
Forwarded from ETV መዝናኛ
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ
ፍቅር እስከ መቃብር ክፍል ሁለት ከደቂቃዎች በኋላ በኢቢሲ
************

በጉጉት የሚጠበቀው ፍቅር እስከ መቃብር ተከታታይ ፊልም ዛሬ ከምሽቱ 2፡20 ሰዓት ጀምሮ በኢቢሲ መዝናኛ ቻናል እንዲሁም ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢቢሲ ዜና ቻናል ይተላለፋል።

ፊልሙን ባመቸዎት ጊዜ ለመመልከት የኢቢሲ ወርልድ የዩቲዩብ ቻናልን https://www.youtube.com/@EBCworld ሰብስክራይብ ያድርጉ።
👍10
Forwarded from ETV መዝናኛ
ፍቅር እስከ መቃብር - ክፍል አራት | Fiker Eske Mekaber Episode 4 Etv | Ethiopia | News zena
https://www.youtube.com/watch?v=LKERgaNGJi0&t=17s&ab_channel=EBC
👍8
የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ ለታላቅ ፊልም ትዝታዎ!
***********************

"ፍቅር እስከ መቃብር" ከክፍል1 - ክፍል 4 በተከታታይ በአንድ ምሽት ከ2፡00 ሰአት ጀምሮ
የታላቁን ደራሲ ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ መጽሐፍ ታላቁን ተከታታይ ፊልም "ፍቅር እስከ መቃብር"ን ለቀድሞ የኢቲቪ ታላቅ ፊልም ፕሮግራም ማስታወሻ እነሆ ብለናል።

በኢቢሲ በመዝናኛ ቻናል ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ከቤተሰብዎ እና ከወዳጆችዎ ጋር በመሆን ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አራት በተከታታይ ይመልከቱ። ትዝታዎን ያድሱ ትዝታ ያኑሩ።

በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
#etv #ፍቅርእስከመቃብር
👍4🔥1
መግለጫ
ፍቅር እስከመቃብርን በተመለከተ
****************

ፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ ከኢትዮጰያ ሬድዮ ትረካ እስከ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፊልም!

የኢቢሲ የአዲስ ዓመት ስጦታ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተመልካቹን ፍላጎት ለማርካት የትዝታችንን ምልክት የንባብ ልምምዳችን በኩር የስነጽሑፍ ሥራዎች ቁንጮ የሆውን የክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ታላቁን የፈጠራ ሥራ ‹‹ ፍቅር እስከ መቃብር ›› መፅሐፍን ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ ወደ ፊልም በመቀየር እንድትመለከቱት የ አዲስ ዓመት ስጦታ በማድረግ አበርክቷል።

ይኸም ስጦታ ከመስከረም 1-5 2017 ዓ.ም የፊልሙን አራት ክፍሎች በETV ዜና ቻናል፣ በETV መዝናኛ ቻናል ፣ በEBC World የYOU TUBE ገፅ እና በፌስ ቡክ ቲክቶክ እና ኹሉም ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ለክቡራን ተመልካቾቻቸን ቀርቧል።

በቀጣይም ከጥቂት ቀናት በኋላ የ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር›› ፊልም ሁሉም ክፍሎች በዋናነት በETV መዝናኛ ቻናል መተላለፍ ይጀምራሉ።

የፍቅር እስከመቃብርን ትረካ በኢትዮጵያ ራድዮ በወጋየሁ ንጋቱ ተከታትላችሁ ትዝታ የተጋራችሁ አድማጮቻችን ታላቁ ስራ በታላቅ የፊልም ጥበብ ተገልጦ በመደበኛነት እንድትከታተሉን የዘመን ትዝታም እንድትጋሩ በታላቅ አክብሮት እንጋብዛችኋለን።

በአዲስ አመት ስጦታችን መነሻም ለታላቁ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ፣ በመጽሃፉ ላይ ተመስርተው ወደተከታታይ ፊልም በመለወጥ ስራው ላይ ለተሳተፉ ባለሙያዎች ብሎም በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የኢቢሲ ቤተሰቦች ለሰጣችሁን አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን።

በቅርብ ቀን በመደበኛው ስርጭት ፍቅር እስቀመቃብርን ጠብቁት!

መልካም አዲስ ዓመት!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን

መስከረም 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
#ፍቅርእስከመቃብር #etv
👍13👎1
ትዝታ ዘ ፊትበር ወ አልታድ ሰፈር….


ዛሬ በየኛ ሰፈር ፕሮግራም ከ20 ዓመት በፊት ከፍልውሃ እና ፊትበር ተነሰተው አልታድ ሰፈር (ትንሿ ፊት በር) መኖሪያቸውን ካደረጉ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

የሰፈሩ ተወላጆች እና ነዋሪዎች ሰፈራቸውን “እምዬ ፊት በር” እያሉ ይጠሯታል፡፡ ስለ ሰፈራቸው አውርተው የማይተግቡት የፊት በር ልጆች በምልሰት ወደ ኋላ በምናብ ይዘውን ይነጉዳሉ፡፡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችንም እያነሳሳን አውግተናል፤ እነሆ ሙሉ ዝግጅቱን ታደምጡት ዘንድ ጋበዝናችሁ፡፡
👍7
Live stream finished (12 days)
#etv ቅኝት ስፖርት በኤፍ ኤም አዲስ 97.1

ማንቸስተር ሲቲ ከ ዋትፎርድ

በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የ2024/25 የውድድር ዓመት የ3ኛ ዙር ጨዋታ
https://www.facebook.com/share/v/qPr9cy2sVq7cUodj/?mibextid=oFDknk
👍9😁1
ኢቢሲ ወደ ይዘት

#የዛሬይቱ_ኢትዮጵያ
ነገን ዛሬ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ወደ ይዘት በሚል በጀመረው ለውጥ መሰረት አዳዲስ የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያዎችን በማድረግ ወደ ተመልካቾች የተለያዩ ዝግጅቶችን ማድረስ ጀምሯል።

ከእነዚህ አዳዲስ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ- ነገን ዛሬ ፕሮግራም የሀገራችንን እድገትና ልማት፣ የኢትጵያን ልዕልና የሚያረጋግጡ፣ ሰላምና ልማትን የሚያፋጥኑ፣ ዜጎች የጋራ ታሪክ፣ የጋራ ተስፋ፣ የጋራ ሀገር እንዲፈጥሩና እንዲያፀኑ የሚያሰችሉ ይዘቶች ፤ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችሉ የአስተሳሰብ፣ ፍልስፍናዊ ጉዳዮች፣ ኪነ-ጥበባዊ፣ የባህል፣ የታሪክ፣ የእምነት፣ የልማትና የማህራዊ መስተጋር ጉዳዮች በስፋት የሚዳሱበትና ውይይት የሚደረግበት ሳምንታዊ ፕሮግራም እነሆ ዛሬ ይጀምራል።

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ - ነገን ዛሬ በየሳምንቱ ረቡዕ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ወደ እናንተ እናደርሳለን።

ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ በኢቲቪ ዜና ብቻ ይጠብቁን
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ
ነገን ዛሬ
ትርክት ትናንት ፤ ዛሬና ነገ
#etv #EBC #የዛሬይቱ_ኢትዮጵያ
👍4🥰1
ቅኝት ስፖርት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1

ማንቸስተር ዩናይትድ ከትዌንቴ የዩሮፓ ሊግ

https://www.facebook.com/share/v/YBKyx6SqqbdSmnv6/?mibextid=oFDknk
👍8👎1