TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
910 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
Forwarded from Alpha Market
#Discount_Week_Starts_Today!

Enjoy 10% OFF on each @AlphaMarket21 products

Featured products include:
AirPods Pro (Apple)
Headset (P9, JBL)
Galaxy Buds2
And many more!
Browse more deals on @AlphaMarket21
Contact: @ordernow21 | 0931463406
Free delivery available.

We don’t just sell — we guarantee!

@Alphamarket21
1
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የማስተርስ ፕሮግራም (MPH) የ2018 ዓ.ም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ቅዳሜ ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

የእረፍት ቀናት መርሐግብር አመልካቾች ፈተና ጠዋት 4:00 እና የመደበኛ መርሐግብር አመልካቾች ፈተና ከሰዓት 8:00 እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፦
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ዲጂታል ላይብራሪ

(ለፈተናው የተመረጡ አመልካቾች ዝርዝር በተቋሙ የማኅበራዊ ሚዲያ ይመልከቱ፡፡)

@TEMARI_Net1
Let’s Talk Womanhood!
🩸 Menstrual Health, 🎗️ Cervical Cancer & Everything in Between!
📅 Date: November 6 (Thursday)
Time: 8:00 L.T
📍 Location: Eshetu Chole Hall
👩‍🎓 All are welcome — Men too!
💬 Because supporting women starts with understanding them

Register here 👇👇👇
https://forms.office.com/r/v9dX6pQPHA

      Join us for:
Q&A sessions
🎉 Exciting giveaways
📜 Certificates will be sent via email after the program!
Let’s learn, share, and empower together!

@TEMARI_Net1
#Health
" በአሁኑ ሰአት ከወጣቶች በዘለለ እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የስኳር እና የጨው ይዘት ያላቸው የታሸጉ ምግቦች ናቸው " - የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር

ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ ተዘጋጅቷል።

አዋጁ መዘጋጀቱን ተከትሎ ፦
- የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጭ ማህበራት ህብረት (CORHA)፣
- የኢትዮጵያ የልብ ማህበር፣
- የኢትዮጵያ የስኳር በሽታ ማህበር እና የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር በጋራ በመሆን ከቀናት በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም አበራ " በአሁኑ ሰአት ከወጣቶች በዘለለ እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው " ብለዋል።

" ለኩላሊት በሽታዎች ዋነኛ ምክንያቱ የስኳር እና የጨው ይዘት ያላቸው የታሸጉ ምግቦች ናቸው " ሲሉም ገልፀዋል።

አቶ ቢኒያም አበራ በዝርዝር ምን አሉ ?

" በማህበራችን ውስጥ አብዛኛው ኩላሊታቸው የተጎዱ ሰዎች ለኩላሊታቸው መጎዳት ዋነኛ ምክንያት የሆነው ደም ግፊት እና የስኳር በሽታዎች ናቸው። እነዚህ በሽታዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከአመጋገብ ስርአት ጋር የተገናኙ ናቸው። ምክንያቱም የታሸጉ ምግቦች በአብዛኛው የስኳር እና የጨው ይዘት አላቸው።

በተለይ ደግሞ በፋብሪካ የሚቀነባበሩ ምግቦች በውስጣቸው በምግብ ማቀነባበር ስርአት ውስጥ የተጠራቀመ የስብ ክምችት አለ። ይህ የሚጨመር ስኳር ሰዎች በሚመገቡበት ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሰውነት ውስጥ ከፍተኛ  የስኳር መጠን እንዲገባ ያደርጋል። ይህ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያዛባዋል፤ በዚህም የስኳር በሽታ እንዲከሰት ያደርጋል። በምግብ ውስጥ የሚጨመር ንጥረ ነገር ደግሞ የደም ግፊትን ያመጣል። በመሆኑም ኩላሊት ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ ያዳክሙታል። በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ኩላሊት ስራውን እንዳይሰራ ያደርጋል።

እነዚህ ነገሮች በተናጠልም ሆነ በድምር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች እያጠቁ ያሉ ንጥረ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ እነዚህን ንጥረ ነገሮች ወደ ዜጎች በሚመጡበት ጊዜ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል።

በታሸጉ ምግቦች ሽፋን ላይ በውስጣቸው የያዙት ንጥረ ነገር በአይነት እና በመጠን ሊገለጽ እንዲሁም ሰዎች እነዚህን ሲመገቡ ሊደርስባቸው የሚችሉ ጉዳቶች በመሸፈኛቸው ላይ በጉልህ መቀመጥ አለባቸው።

በታሸጉ ምግቦች ላይ በቂ ቁጥጥርና ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።

እነዚህ ምግቦች በማህበረሰባችን ላይ እያደረሱት ያለው ጉዳት እና ቀውስ ለመቀነስ ማህበራችን ይህ አዋጅ ቶሎ ተፈጻሚ እንዲሆን ይሰራል " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግብ ህክምና ባለሙያ እና የኢትዮጵያ ስነ ምግብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ዘላለም ከበደ " ኢትዮጵያ በፋብሪካ በተቀነባበሩ እና ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት ለሚደርሱ የጤና ጉዳቶች በየዓመቱ ከ31 ቢሊየን ብር በላይ ታወጣለች " ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም " በየስአቱ 25 ሰው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ማለትም በስኳር፣ በኩላሊት፣ በጉበት እና በልብ እንዲሁም በደም ቧንቧ በሽታዎች ይሞታሉ፣ በአሁኑ ስአት የህመሙ ጫና ከ52 በመቶ በላይ ሆኗል " ነው ያሉት።

" የምግብ ጥራትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በርካታ ሰዎች የታሸጉ ምግቦች ጥሩ እየመሰሏቸው ሲገዙ ይታያል። ይህ በጥናት መረጋገጥ አለበት። ማህበረሰቡ ባለው የግንዛቤ ክፍተት ምክንያት እየተጠቀመ እየተጎዳ ነው " ብለዋል።

" ማህበረሰቡ በአዋጁ መሰረት ክልከላ የሚደረግባቸው የስብ፣ የስኳር እና የጨው መጠናቸውን ያልጻፉ የታሸጉ ምግቦችን ሲያዩ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ አለባቸው። አዋጁ ቶሎ ወደ ተግባር ገብቶ ክፍተቶቹ እየታዩ መስተካከያ ሊደረግበት ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

©tikvahethiopia

@TEMARI_Net1
3💯1
የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር የሠሩት ወጣቶች 👏

ሰመረ ገ/ልዑል እና ሁለት ጓደኞቹ የኢንጂነሪንግ መምህራን ናቸው፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በሚያዘጋጀው የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል፡፡

መምህራኖቹ በኢንስቲትዩቱ በመታገዝ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻርጅ የሚያደርግና በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተ ቴክኖሎጂ ፈጥረዋል፡፡

Ultra AC Wall Box EV Charger የተሰኘው ፈጠራው፤ AC Power የሚጠቀም ሲሆን 22 ኪዋ የሚደርስ output አለው፡፡

ፈጠራው በተለይ በኢትዮጵያ እያደገ በመሔድ ላይ ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያስችል መምህራኑ ተናግረዋል፡፡

በብዛት ወደማምረት አለመግባታቸውን የገለፁት ፈጣሪዎቹ፤ እስካሁን ባለው ሒደት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የማቴርያል እና የገንዘብ አቅርቦት እንዳደረገላቸው ገልፀዋል፡፡

@TEMARI_Net1
🔥42
በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን በሁለት ሳምንት ውስጥ የመጠጥ ውሃ ሊጠፋ ይችላል ተብሏል።

በሃገሪቱ አጋጠመ በተባለ ታሪካዊ የድርቅ አደጋ የቴህራን ከተማ ዋነኛ የመጠጥ ውሃ ምንጭ በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሊደርቅ ይችላል ተብሏል።

አሚር ካቢር ግድብ የተባለው የከተማዋ የመጠጥ ውሃ ምንጭ በአሁኑ ጊዜ መያዝ የሚችለውን 8 በመቶ ውሃ ብቻ እንደያዘ ተገልጿል።

የያዘው ውሃም ቴህራንን ሊያጠጣ የሚችለው ለመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ብቻ መሆኑ ተነግሯል።

በኢራን ከአስርት አመታት በኋላ ከባዱ ድርቅ ተከስቷል ሲባል በቴህራን አካባቢም የእርጥበት መጠኑ በ100% ቀንሷል ተብሏል።

የ10 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ የሆነችው ቴህራን ነዋሪዎቿ በቀን 3 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ይጠቀማሉ ተብሏል።

በተመሳሳይ የኢራን ጎረቤቷ ኢራቅ ከ1993 ወዲህ ከባዱን ድርቅ እያስተናገደች ሲሆን ሁለቱ ታዋቂ ወንዞች ኤፍራጥስ እና ጤግሮስም የውሃ መጠናቸው በ27% ቀንሷል።

በመላው አለም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የውሃ እጥረት እያጋጠመ ሲሆን ውሃን ከየትኛውም ጊዜ በላይ በጥንቃቄ መጠቀም የሚገባበት ጊዜ ስለመድረሱም የኢራንና ኢራቅ ሁኔታ ማሳያ ሆነዋል።

መረጃው የአልጄዚራ ነው።

Via;,TikvahethMagazine

@TEMARI_Net1
👏1
Forwarded from Alpha Market
#Discount_Continues_This_Week!

Enjoy 10% OFF on each @AlphaMarket21 products

Featured products include:
AirPods Pro (Apple)
Headset (P9, JBL)
Galaxy Buds2
And many more!
Browse more deals on @AlphaMarket21
Contact: @ordernow21 | 0931463406
Free delivery available.

We don’t just sell — we guarantee!

@Alphamarket21
1