Forwarded from AAU MEREJA
#Logocompetition
🎨 Calling all creatives! 🇸🇪🇪🇹
Celebrate 80 years of friendship between Sweden and Ethiopia by designing the official anniversary logo! 🌟
💰 Prize: 100,000 ETB equivalent
🗓️ Deadline: 5 December 2025
Show us your vision of unity, history, and the future!
👉 submit your application here: https://lnkd.in/dP9CuxpA
@AAUMEREJA

🇮🇹 Italy is calling! Italian universities have officially announced scholarships for 2026 — offering international students the chance to study in Europe at world-ranked institutions.
👉 Apply now at Gamyto.com and secure your spot!
@AAUMEREJA
👉 Apply now at Gamyto.com and secure your spot!
@AAUMEREJA
❤3
Forwarded from AAU MEREJA
ዩኒቨርሲቲዎች በለብለብ እያስተማሩ ተማሪዎችን ማስመረቃቸውን እንዲያቆሙ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡
የዩኒቨርሲቲዎቹ ስኬት መለካት ያለበት ባስመረቁት ተማሪ ብዛት ሳይሆን፣ በተማሪዎቻቸው ብቃት ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡
34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው፡፡
ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን ለመፍጠር ጥራት ያለው ትምህርት መስጠት የግድ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ በኋላ ለተማሪዎቻቸው ዲግሪ ሲሰጡ ያሰለጠኗቸው ተመራቂዎች ከሌላው ዓለም ጋር መወዳደር እንደሚችሉ ማረጋገጥ ሲችሉ ብቻ ሥራቸውን ተወጥተዋል ማለት እንደሚቻል ሚኒስሩ ገልፀዋል፡፡
በቅርቡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በተደረገ ምልከታ ትምህርት ማስተማር ያልጀመሩ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ይህን “እንዝህላልነት“ ሊቆጣጠሩ ይገባል፣ “መምህራን ገብተዋል ወይ፣ ማስተማር ጀምረዋል ወይ? ይህን መቆጣጠርና ማስተካከል ይኖርብናል“ ብለዋል፡፡ #ShegerFM
©tikvahuniversity

👏4❤1
#Opportunity📣
🚀6-Month Remote Digital Health Africa Internship Program 2026🚀
✨The Digital Health Africa (DHA) Internship Program 2026 is a 6-month remote, skill-based experience that empowers young Africans to co-create solutions and stories shaping the continent’s digital health ecosystem.
What You’ll Gain:
✅Hands-on experience in media, research, policy, and youth engagement
✅Mentorship from top professionals in health innovation
✅Certificate of Completion & Letter of Recommendation
✅Portfolio feature on DHA’s platforms
✅Membership in the DHA Youth & Alumni Network
Eligibility:
🔸Aged 18–35
🔸Student, graduate, or young professional passionate about digital health or tech
🔸Based in Africa or working on Africa-focused projects
🔸Able to commit 8–10 hours weekly (Jan–June 2026)
🔸Comfortable working remotely
🔗Apply: https://lnkd.in/djHkBuDF
📝Deadline: November 27, 2025
"If this isn't for you, please share it with others who might be interested."🙏
Follow us👇for more opportunities
@TEMARI_Net1

ቻይና የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቿ የአዕምሮ ጤና እንዲሻሻል በየቀኑ የ2 ሰዓት የአካል እንቅስቃሴ እንዲሰሩ አስገድዳለች።
ቻይና የተማሪዎቿን የአዕምሮ ጤና ለመጠበቅ ከአካል እንቅስቃሴው በተጨማሪ ክፍል ውስጥ ስልክ መጠቀምንና በኢንተርኔት ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ "screen-free" ክፍለ ጊዜ መጀመሯ ተዘግቧል።
ቻይና ሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚሰጧቸውን የቤት ስራዎች እንዲቆጣጠሩና በመማሪያ ቀናት የሁለት ሰዓት የአካል እንቀስቃሴ እንዲሰጡ አዛለች።
በተጨማሪ ተማሪዎች በቂ እንቅልፍ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ስትል የትምህርት ጫና ሊኖርባቸው አይገባም ብላለች።
በቻይና ካለው የትምህርት ጫና ጋር በተያያዘ ተማሪዎች ለጭንቀት ይጋለጣሉ ሲባል ይህም እንቅልፍ እንዳያገኙ እንደሚያደርገግና አዕምሯቸውን እንደሚጎዳው ተነግሯል።
ቻይና እንደዚሁም የአስተማሪዎችንም ጫና ስትቀንስ በበዓል ቀናትና በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት እንዳይሰሩም ከልክላለች።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።

ደቡብ አፍሪካ በራሷ የሰራችውን የኮሌራ ክትባት በሰዎች ላይ መሞከር ጀመረች።
በአፍ የሚሰጠው የኮሌራ ክትባቱ ኬፕታውን መቀመጫውን ባደረገ ባዮቫክ የተሰኘ ተቋም መበልፀጉ ተነግሯል።
ክትባቱ በአሁኑ ጊዜ ሙከራ ላይ ሲሆን በቀጣይ አሁን ገበያ ላይ ካሉት ክትባቶች ጋር ለማነፃፀር የሚረዳ ሙከራ ይደረጋል ተብሏል።
ደቡብ አፍሪካ ሙከራው አፍሪካ በራሷ ክትባት መስራት እንደምትችል ያሳየ ነው ስትል ሙከራው ከተሳካ በአለም አቀፍ ደረጃ በአፍ የሚሰጠውን የኮሌራ ክትባት በማምረት ሁለተኛ እንደምትሆንም ተስፋ ጥላለች።
ከሙከራው እንደሚገኘው ውጤትም ክትባቱ በ2028 በአፍሪካ ጥቅም ላይ ይውላል ሲሉ የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር አስታውቀዋል።
የአለም የጤና ድርጅት በየአመቱ እስከ 4 ሚሊየን ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተው በየአመቱ እስከ 143 ሺህ ሰዎች እንደሚሞቱ ሲገልፅ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ደግሞ አፍሪካውያን ናቸው።
ዘገባው የተገኘው ከአፍሪካ ኒውስ ነው።

❤1👍1
ናይጄሪያ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶቿ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ማስተማሯን ትታ ወደ እንግሊዝኛ ተመለሰች።
ናይጄሪያ ከ3 አመት በፊት ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይበልጥ ትምህርትን መረዳት ይችላሉ በሚል እሳቤ የተገበረችውን ፖሊሲ በመተው ወደ እንግሊዝኛ ተመልሳለች።
የትምህርት ሚኒስትሩ ቱንጂ አላውሳ ፖሊሲው የተፈለገውን ውጤት አላመጣም ያሉ ሲሆን እንግሊዝኛ ከቅድመ ትምህርት አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲት ድረስ የማስተማሪያ ቋንቋ ይሆናል ብለዋል።
ልጆች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ ትምህርትን የበለጠ እንደሚረዱ የተመድን ጨምሮ የተለያዩ ጥናቶች ማሳየታቸውን ተከትሎ ፖሊሲው በቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር መተግበሩም ተገልጿል።
ናይጄሪያ በፈተና የተሞላ የትምህርት ስርዓት ያላት ሲሆን 85 በመቶው ህፃናቷ ወደ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቢገቡም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚጨርሱት ከግማሽ አይበልጡም የተባለ ሲሆን የትምህርት ሚኒስትሩ አብዛኛው የሚወድቀው ተማሪ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ከሚማሩባቸው አካባቢዎች የመጡ ናቸው ብለዋል።
ከሌላው ሃገር በበለጠ ናይጄሪያ 10 ሚሊየን ልጆቾ ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውም ተገልጿል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።

❤2
ያንጎ ኢትዮጵያ ከቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ዘመቻ አካሄደ
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ ህዳር 3፣2018 ዓ.ም
የአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ኢትዮጵያ (በፍራንቻይዝ ጂ2ጂ አይቲ ሶሉሽንስ አ.ማ. እና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የሚተዳደር) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ዘመቻ ጀምሯል። ዘመቻው ያንጎ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመደገፍ ያለውን ተነሳሽነትን ያማከለ ነው።
የያንጎ ኢትዮጵያ የፍራንቻይዝ አጋሮች እና አጋር አሽከርካሪዎች በበጎ ፍቃደኝነት ደም በመለገስ ላይ ሲሆኑ ይህም የደም ተፈላጊነት ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር ኩባንያው ህብረተሰቡን ለማገልገል ያለው ቁርጠኝነትን አጉልቶ ያሳያል፡፡
"ያንጎ እውነተኛ እድገት ከማህበረሰቡ ደህንነት ጋር አብሮ የተሳሰረ ነው ብሎ ያምናል። ይህ ዘመቻ የመተሳሰብ፣የኃላፊነት እና የትብብር እሴቶቻችንን ያሳያል። ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጎን በመቆማችን ኩራት ይሰማናል፤ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ለሌሎችም ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡" በማለት በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ ዶ/ር ይቅናለም አበበ ተናግረዋል።
የደም ልገሳ ዘመቻው የበጎ ፈቃደኝነትን እና የማኅበረሰብ መንፈስን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ ትናንሽ የግለሰብ ተግባራት ተባብረው ትርጉም ያለው ማኅበራዊ ተፅእኖ መፍጠር እንደሚችሉ የያንጎን እምነት የሚያጠናክር ነው።

Guys cholle Lounge(FBE) ከዛሬ ጀምሮ እሁድም አገለግሎት መስጠት ጀመሯል፣
ወደፊት እስከምሽት አንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን ።
ለNone cafe ጓደኛሕ #share አድርግለት😂
@AAUMEREJA
ወደፊት እስከምሽት አንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን ።
ለNone cafe ጓደኛሕ #share አድርግለት😂
@AAUMEREJA
🔥3❤1
Forwarded from AAU MEREJA
ተማሪዎች ሊያስተምሩ ነው😂
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።
ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።
የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።
ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። #Fortune

🤬11❤1🕊1
ደቡብ ኮሪያ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስትል ሁሉንም አይነት በረራ አቁማ ነበር።
ደቡብ ኮሪያ 500,000 ያህል ተማሪዎቿ ከባድ የሚባለውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እየፈተነች ሲሆን ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ቦታቸው በጊዜ እንዲደርሱ ሲባል ሌሎች በረራዎች ለግማሽ ሰዓት ቆመው ነበር ተብሏል።
በሁሉም ኤርፖርቶች ተማሪዎች ለፈተናው ሲቀመጡ እንዳይጉላሉ በማሰብ አውሮፕላኖች ለ30 ደቂቃ ከማረፍና ከመብረር ተከልክለው ነበር።
በውሳኔው 65 አለም አቀፍ በረራዎችን ጨምሮ 140 በረራዎች ሲስተጓጓሉ አውሮፕላኖችም ከ3000 ሜትር ከፍታ በታች ከመብረር ታግደው ነበር።
በተጨማሪ ተፈታኞች በጊዜ እንዲደደርሱ ቢሮዎች ከተለመደው ሰዓት በአንድ ሰዓት ዘግይተው እንዲከፈቱ ተደርጓል።
ደቡብ ኮሪያ ዘንድሮ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተፈታኞችን እያስፈተነች ሲሆን ቁጥሩም ከ2019 በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው የተፈታኝ ቁጥር ነው ተብሏል።
ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን መርጠው ሲፈተኑ ፈተናው እስከ 13 ሰዓት ድረስ ሊፈጅ ይችላል።

❤4😐2
በውሃ እጥረት እየተፈተነች ያለችው ኢራን እጇን ለፀሎት ወደ ሰማይ ስትዘረጋ ቴክኖሎጂን በመጠቀምም ዝናብ ለማዝናብ እየሞከረች ነው።
ኢራን ከፍተኛ በሆነ የውሃ እጥረት እየተፈተነች ስትሆን የዋና ከተማዋን የሚያጠጡ ግድቦች አቅምም ወደ 5% ወርዷል።
ይህንንም ተከትሎ ኢራን የ"Cloud seeding" በመጠቀም ዝናብ ለማዝነብ እየሞከረች ነው።
"Cloud Seeding" አውሮፕላንን ወይም ጄኔሬተር በመጠቀም ወደ ደመና ጨዋማ ኬሚካሎችን በመርጨት ዝናብ ለማዝነብ የሚደረግ ሙከራ ሲሆን ይህንን ዘዴ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመዋለች።
ኢራን ይህንን ዘዴ ኡሪማ በተሰኘው ትልቁ ኃይቋ ላይ ሞክራለች።
ከተለመደው አማካይ የዝናብ መጠን በዚህ አመት የዝናብ መጠኗ በ89 በመቶ እንደቀነሰ የገለጸችው ኢራን ዝናብ እንዲዘንብም የአደባባይ ጸሎት አርብ እለት አድርጋለች።
ቅዳሜ ዕለትም ከቴህራን በስተሰሜን በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በረዶ የታየ ሲሆን በምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች የተወሰነ ዝናብም ዘንቧል ተብሏል።
ኢራን በ50 አመት ውስጥ ከባዱን ድርቅ እያስተናገደች መሆኗንም ገልፃ ውሃ በሚያባክኑት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብላለች።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
#TikvahethMagazine

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ3ኛ ዓመት ቡሃላ ለ1 ዓመት የማስተማር ግዴታ አለባቸው ተብሎ በተላለፈው የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ላይ የቻናላችን አቋም እንደሚከተለው ይሆናል፣
በሌሎች ሀገራት ተማሪ ወይም የከፍተኛ ት/ት ምሩቅ ለተጠራበት ሀገራዊ ጥሪ (እስከ መዋጋት) ድረስ እንዲሳተፍ ሊገደድ ይችላል ፤ በዘሕ መሠረት ተማሪዎች ሐዝባቸውን ለ1 ዓመት ቢያስተምሩ ችግር የለውም፣ ይሕ መሆን ያለበት ግን ሰፊ ውይይት ከተደረገበት ቡሃላ እና ሁሉም ተማሪ ጉዳዩ ለሀገር ጠቃሚ መሆኑን ካመነበት ብቻ መሆን አለበት እንላለን ።
የናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል ?

❤11🤬5😁3
Forwarded from AAU MEREJA
ለ1 ዓመት ያስተምራሉ የሚለው ጉዳይ እንደ ሐሳብ ቀረበ እንጂ የጸደቀ ነገር የለም ሲል የኢት/ ከፍ/ተቋም/ ተማሪዎች ህብረት አስታውቋል።
#share
@AAUMEREJA
#share
@AAUMEREJA
Forwarded from HULT Prize at Addis Ababa University
🔥 Build an Idea. Change the World. 🌍
Hult Prize is finally here at Addis Ababa University — and YOU could be the next million-dollar founder! 💡💰
Are you passionate about solving real problems?
Do you dream of launching your own startup?
Then this is your moment.
✨ Why Join Hult Prize?
✔️ Learn global entrepreneurship skills
✔️ Build a startup from scratch
✔️ Work with amazing teammates
✔️ Pitch your idea on an international stage
✔️ Stand a chance to win $1,000,000 to grow your startup!
This is more than a competition — it’s a life-changing journey.
If you believe your idea can make the world a better place, Hult Prize is where you start.
🔥Updates dropping soon!🔥
🔥 Big updates are coming. Stay close.
JOIN US: [HERE]
Follow us for all announcements:
Telegram | LiinkedIn | Instagram | TikTok

❤1
የተማሪዎቹ ጥያቄ ምንድነው ?
" ውሳኔው ተቀባይነት የሌለው ነው " - ተማሪዎች
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለ1 ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል መባሉን መዘገቡ ይታወቃል።
ውሳኔው በሚመለከት ለምክር ቤት አባላት ቀርበው ያብራሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) " ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥረት ምክንያት እንደሆነ " አስረድተዋል።
ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ተገልጿል።
ይህንንም ለመቅረፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህርነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም መገለጹን ተከትሎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ ውሳኔው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።
ጉዳዩ ከተሰማበት ቀን አንስቶ በተለያዩ የሃገሪቱ ዩንቨርስቲዎች መነጋገሪያ የሆነው ይህ ውሳኔ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ለማሰማት ሰልፍ ማድረጋቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎች ሰምቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበርካታ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስለጉዳዩ በማነጋገር እንደተረዳው ጉዳዩን በሚዲያ ላይ ከመስማት በቀር በአሁኑ ሰዓት የሦስተኛ ዓመት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የሚቀጥለው አመት የማስተማር አገልግሎት ስለመስጠታቸው ከዩኒቨርሲቲያቸው በኩል የተገለጸላቸው ነገር የለም።
ከሃዋሳ ፣ ባህርዳር፣ ወለጋ፣ አምቦ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መደወላቡ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ፣ ሐዋሳ ፣ ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከአርባምንጭ ዩንቨርሲቲዎች ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ጉዳዩን በመደናገጥ መስማታቸውን ገልጸው ውሳኔውን ግራ አጋቢ ሲሉ ገልጸውታል።
ተማሪዎቹ በሰጡን ቃል " በጉዳዩ ላይ ጥርት ያለ የሰማነው ነገር የለም እንዴት እንደምንሄድ፣ ሰርቪሱን በምን አይነት መንገድ እንደምንሰጥ ያወቅነው ነገር የለም ጉዳዩ ግራ አጋቢ ሆኖብናል " ነው ያሉት።
ቃላቸውን የሰጡን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውሳኔውን እንዲሰሙበት ከተደረገበት ጊዜ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የሰላም ሁኔታ እንዲሁም ከትምህርት ቆይታቸው ርዝመት አንጻር በማቅረብ ጉዳዩን " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ገልጸውታል።
ቲክቫህ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ?
" መሃል ላይ ገብተን ነው የተነገረን /ይህ ሃሳብ የመጣው ፣አማራጭ እንኳን ማየት የማንችልበት ሁኔታ ላይ ነው ውሳኔውን የሰማነው አንድ አመት ቀልድ አይደለም ለእኛ።
በጣም ቅሬታ አለን ካለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር ክልል ላይ ሄዳቹ ታስተምራላቹ የተባለው ነገር ተቀባይነት የለውም ሰላም የሰፈነበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለነው።
ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጠቱ ግዴታ ነው ከተባለም እንደ አማራጭ የትምህርት ቆይታችንን ጨርሰን ካጠናቀቅን በኋላ ቢሆን የተሻለ ነበር ፣የግዴታ ሦስተኛ አመት ላይ ከተባለ አንድ አመት ሙሉ ሌላ ቦታ ውለን ድጋሚ ወደ ትምህርት ልንመለስ ነው ይህ ደግሞ አግባብ አይደለም።
በጉዳዩ ላይ ጥርት ያለ የሰማነው ነገር የለም እንዴት እንደምንሄድ፣ ሰርቪሱን በምን አይነት መንገድ እንደምንሰጥ ያወቅነው ነገር የለም ጉዳዩ ግራ አጋቢ ሆኖብናል።
ለመቀበል ትንሽ ከብዶናል የእኛ ባች በርካታ ለውጦችን ያየ ነው ፣ ሬሚዲያል የተጀመረበት ነው ከሦስት እና ከአራት አመት በፊት ፍሬሽማን ኮርስ ተጀምሮ የሦስት አመት ዲግሪ ወደ አራት ከፍ አለ አሁን ደግሞ አገልግሎት ይጀምራል ከተባለ አምስት እና ስድስት አመት ልንቆይ ነው ማለት ነው።
ከትምህርት አለም ርቀን ድጋሚ ወደ ትምህርት አለም መመለስ ማለት ከባድ ነው የዲፓርትመንት ኮርሶች ተያያዥ ኮርሶች ስለሆኑ አንድ አመት መስክ ላይ ቆይቶ በድጋሚ ወደ ትምህርት መመለስ የዩኒቨርሲቲ ቆይታችንን ከባድ ያደርግብናል።
መውጫ ፈተና ያለብን ከመሆኑም አኳያ የንባብ ጊዜያችንን የሚያጣብብ በመሆኑ ለመቀበል ከብዶናል።
አገልግሎቱን ብንቀበለው እንኳን ለምሳሌ የህክምና ተማሪዎች ኢንተርንሺፕ እየወጡ ነገር ግን የሚመረቁበት አመት አይገፋም የእኛም ቢሆን ደስ የሚለን ተመሳሳዩን መንገድ ነው።
' ታስተምራላቹ ' ከተባለ እንኳን የትኞቹ ተማሪዎች እና ምን አይነት የአቅም ደረጃ ላይ ያሉት ያስተምራሉ የሚለው ግልጽ አይደለም።
ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለክረምት እረፍት ሦስት ወር ከሰኔ ጀምሮ እስከ ነሐሴ እናርፋለን ይህንን ሦስት ወር አገልግሉ በተባልንበት ቦታ ሁሉ አገልግለን በቀጣይ አመት ወደ ትምህርታችን መመለስ ነው የምንፈልገው።
ካለቀ በኋላ አስተምሩ ብንባል በበጎ ፈቃድ ወጥተን በደስታ እናገለግላለን ነገር ግን አንድ አመት ተገፍቶ ከሆነ ግን ከትምህርቱ መንፈስ እንወጣለን።
ዛሬ ነገ ይመረቅልኛል ብሎ የሚጠብቅ ወላጅ አንድ አመት ተጨምሯል ስትላቸው ተስፋቸው እያጠረ ይመጣል አብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የደሃ ልጅ ነው በደሃ ቤተሰብ ላይ አንድ አመት መጨመር በጣም ይከብዳል።
በምን አይነት መንገድ ተገምግሞ እዚህ ሃሳብ ላይ እንደተደረሰ ባይገባንም በውሳኔው ደስተኞ አይደለንም የምደባ ቦታችንም አሳስቢ ነው "ሲሉ ገልጸዋል ።
በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia

❤9