TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
910 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
ያንጎ ኢትዮጵያ ከቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ዘመቻ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ ህዳር 3፣2018 ዓ.ም
 
የአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ኢትዮጵያ (በፍራንቻይዝ ጂ2ጂ አይቲ ሶሉሽንስ አ.ማ. እና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ኃ.የተ.የግ.ማ. የሚተዳደር) ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ዘመቻ ጀምሯል። ዘመቻው ያንጎ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመደገፍ ያለውን ተነሳሽነትን ያማከለ ነው።
 
የያንጎ ኢትዮጵያ የፍራንቻይዝ አጋሮች እና አጋር አሽከርካሪዎች በበጎ ፍቃደኝነት ደም በመለገስ ላይ ሲሆኑ ይህም የደም ተፈላጊነት ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር ኩባንያው ህብረተሰቡን ለማገልገል ያለው ቁርጠኝነትን አጉልቶ ያሳያል፡፡
 
"ያንጎ እውነተኛ እድገት ከማህበረሰቡ ደህንነት ጋር አብሮ የተሳሰረ ነው ብሎ ያምናል። ይህ ዘመቻ የመተሳሰብ፣የኃላፊነት እና የትብብር እሴቶቻችንን ያሳያል። ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጎን በመቆማችን ኩራት ይሰማናል፤ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ለሌሎችም ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡" በማለት በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ ዶ/ር ይቅናለም አበበ ተናግረዋል።
 
የደም ልገሳ ዘመቻው የበጎ ፈቃደኝነትን እና የማኅበረሰብ መንፈስን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ ትናንሽ የግለሰብ ተግባራት ተባብረው ትርጉም ያለው ማኅበራዊ ተፅእኖ መፍጠር እንደሚችሉ የያንጎን እምነት የሚያጠናክር ነው።
 
@TEMARI_Net1
Forwarded from AAU MEREJA
Guys cholle Lounge(FBE) ከዛሬ ጀምሮ እሁድም አገለግሎት መስጠት ጀመሯል፣
ወደፊት እስከምሽት አንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን ።

ለNone cafe ጓደኛሕ #share አድርግለት😂

@AAUMEREJA
🔥31
Forwarded from AAU MEREJA
ተማሪዎች ሊያስተምሩ ነው😂

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። #Fortune

@AAUMEREJA
🤬111🕊1
ደቡብ ኮሪያ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስትል ሁሉንም አይነት በረራ አቁማ ነበር።

ደቡብ ኮሪያ 500,000 ያህል ተማሪዎቿ ከባድ የሚባለውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እየፈተነች ሲሆን ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ቦታቸው በጊዜ እንዲደርሱ ሲባል ሌሎች በረራዎች ለግማሽ ሰዓት ቆመው ነበር ተብሏል።

በሁሉም ኤርፖርቶች ተማሪዎች ለፈተናው ሲቀመጡ እንዳይጉላሉ በማሰብ አውሮፕላኖች ለ30 ደቂቃ ከማረፍና ከመብረር ተከልክለው ነበር።

በውሳኔው 65 አለም አቀፍ በረራዎችን ጨምሮ 140 በረራዎች ሲስተጓጓሉ አውሮፕላኖችም ከ3000 ሜትር ከፍታ በታች ከመብረር ታግደው ነበር።

በተጨማሪ ተፈታኞች በጊዜ እንዲደደርሱ ቢሮዎች ከተለመደው ሰዓት በአንድ ሰዓት ዘግይተው እንዲከፈቱ ተደርጓል።

ደቡብ ኮሪያ ዘንድሮ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተፈታኞችን እያስፈተነች ሲሆን ቁጥሩም ከ2019 በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው የተፈታኝ ቁጥር ነው ተብሏል።

ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን መርጠው ሲፈተኑ ፈተናው እስከ 13 ሰዓት ድረስ ሊፈጅ ይችላል።

ዘገባው የሮይተርስ ነው

@TEMARI_Net1
4😐2
በውሃ እጥረት እየተፈተነች ያለችው ኢራን እጇን ለፀሎት ወደ ሰማይ ስትዘረጋ ቴክኖሎጂን በመጠቀምም ዝናብ ለማዝናብ እየሞከረች ነው።

ኢራን ከፍተኛ በሆነ የውሃ እጥረት እየተፈተነች ስትሆን የዋና ከተማዋን የሚያጠጡ ግድቦች አቅምም ወደ 5% ወርዷል።

ይህንንም ተከትሎ ኢራን የ"Cloud seeding" በመጠቀም ዝናብ ለማዝነብ እየሞከረች ነው።

"Cloud Seeding" አውሮፕላንን ወይም ጄኔሬተር በመጠቀም ወደ ደመና ጨዋማ ኬሚካሎችን በመርጨት ዝናብ ለማዝነብ የሚደረግ ሙከራ ሲሆን ይህንን ዘዴ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመዋለች።

ኢራን ይህንን ዘዴ ኡሪማ በተሰኘው ትልቁ ኃይቋ ላይ ሞክራለች።

ከተለመደው አማካይ የዝናብ መጠን በዚህ አመት የዝናብ መጠኗ በ89 በመቶ እንደቀነሰ የገለጸችው ኢራን ዝናብ እንዲዘንብም የአደባባይ ጸሎት አርብ እለት አድርጋለች።

ቅዳሜ ዕለትም ከቴህራን በስተሰሜን በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በረዶ የታየ ሲሆን በምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች የተወሰነ ዝናብም ዘንቧል ተብሏል።

ኢራን በ50 አመት ውስጥ ከባዱን ድርቅ እያስተናገደች መሆኗንም ገልፃ ውሃ በሚያባክኑት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብላለች።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

#TikvahethMagazine

@TEMARI_Net1
2
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ3ኛ ዓመት ቡሃላ ለ1 ዓመት የማስተማር ግዴታ አለባቸው ተብሎ በተላለፈው የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ላይ የቻናላችን አቋም እንደሚከተለው ይሆናል፣

በሌሎች ሀገራት ተማሪ ወይም የከፍተኛ ት/ት ምሩቅ ለተጠራበት ሀገራዊ ጥሪ (እስከ መዋጋት) ድረስ እንዲሳተፍ ሊገደድ ይችላል ፤ በዘሕ መሠረት ተማሪዎች ሐዝባቸውን ለ1 ዓመት ቢያስተምሩ ችግር የለውም፣ ይሕ መሆን ያለበት ግን ሰፊ ውይይት ከተደረገበት ቡሃላ እና ሁሉም ተማሪ ጉዳዩ ለሀገር ጠቃሚ መሆኑን ካመነበት ብቻ መሆን አለበት እንላለን ።

የናንተስ ሃሳብ ምን ይመስላል ?

@TEMARI_Net1
11🤬5😁3
Forwarded from AAU MEREJA
ለ1 ዓመት ያስተምራሉ የሚለው ጉዳይ እንደ ሐሳብ ቀረበ እንጂ የጸደቀ ነገር የለም ሲል የኢት/ ከፍ/ተቋም/ ተማሪዎች ህብረት አስታውቋል።

#share

@AAUMEREJA
🔥 Build an Idea. Change the World. 🌍
Hult Prize is finally here at Addis Ababa University — and YOU could be the next million-dollar founder! 💡💰

Are you passionate about solving real problems?
Do you dream of launching your own startup?
Then this is your moment.

Why Join Hult Prize?
✔️ Learn global entrepreneurship skills
✔️ Build a startup from scratch
✔️ Work with amazing teammates
✔️ Pitch your idea on an international stage
✔️ Stand a chance to win $1,000,000 to grow your startup!

This is more than a competition — it’s a life-changing journey.
If you believe your idea can make the world a better place, Hult Prize is where you start.

🔥Updates dropping soon!🔥

🔥 Big updates are coming. Stay close.

JOIN US: [
HERE]

Follow us for all announcements:
Telegram | LiinkedIn | Instagram | TikTok
1
የተማሪዎቹ ጥያቄ ምንድነው ?

" ውሳኔው ተቀባይነት የሌለው ነው " - ተማሪዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለ1 ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል መባሉን መዘገቡ ይታወቃል።

ውሳኔው በሚመለከት ለምክር ቤት አባላት ቀርበው ያብራሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)  " ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥረት ምክንያት እንደሆነ " አስረድተዋል።

ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ተገልጿል።

ይህንንም ለመቅረፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህርነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም መገለጹን ተከትሎ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ ውሳኔው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

ጉዳዩ ከተሰማበት ቀን አንስቶ በተለያዩ የሃገሪቱ ዩንቨርስቲዎች መነጋገሪያ የሆነው ይህ ውሳኔ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ለማሰማት ሰልፍ ማድረጋቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎች ሰምቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበርካታ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስለጉዳዩ በማነጋገር እንደተረዳው ጉዳዩን በሚዲያ ላይ ከመስማት በቀር በአሁኑ ሰዓት የሦስተኛ ዓመት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የሚቀጥለው አመት የማስተማር አገልግሎት ስለመስጠታቸው ከዩኒቨርሲቲያቸው በኩል የተገለጸላቸው ነገር የለም።

ከሃዋሳ ፣ ባህርዳር፣ ወለጋ፣ አምቦ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መደወላቡ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬዳዋ፣ ሐዋሳ ፣ ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከአርባምንጭ ዩንቨርሲቲዎች ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ጉዳዩን በመደናገጥ መስማታቸውን ገልጸው ውሳኔውን ግራ አጋቢ ሲሉ ገልጸውታል።

ተማሪዎቹ በሰጡን ቃል " በጉዳዩ ላይ ጥርት ያለ የሰማነው ነገር የለም እንዴት እንደምንሄድ፣ ሰርቪሱን በምን አይነት መንገድ እንደምንሰጥ ያወቅነው ነገር የለም ጉዳዩ ግራ አጋቢ ሆኖብናል " ነው ያሉት።

ቃላቸውን የሰጡን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውሳኔውን እንዲሰሙበት ከተደረገበት ጊዜ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የሰላም ሁኔታ እንዲሁም ከትምህርት ቆይታቸው ርዝመት አንጻር በማቅረብ ጉዳዩን " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ገልጸውታል።

ቲክቫህ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዝርዝር ምን አሉ ?

" መሃል ላይ ገብተን ነው የተነገረን /ይህ ሃሳብ የመጣው ፣አማራጭ እንኳን ማየት የማንችልበት ሁኔታ ላይ ነው ውሳኔውን የሰማነው አንድ አመት ቀልድ አይደለም ለእኛ።

በጣም ቅሬታ አለን ካለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር ክልል ላይ ሄዳቹ ታስተምራላቹ የተባለው ነገር ተቀባይነት የለውም ሰላም የሰፈነበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለነው።

ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጠቱ ግዴታ ነው ከተባለም እንደ አማራጭ የትምህርት ቆይታችንን ጨርሰን ካጠናቀቅን በኋላ ቢሆን የተሻለ ነበር ፣የግዴታ ሦስተኛ አመት ላይ ከተባለ አንድ አመት ሙሉ ሌላ ቦታ ውለን ድጋሚ ወደ ትምህርት ልንመለስ ነው ይህ ደግሞ አግባብ አይደለም።

በጉዳዩ ላይ ጥርት ያለ የሰማነው ነገር የለም እንዴት እንደምንሄድ፣ ሰርቪሱን በምን አይነት መንገድ እንደምንሰጥ ያወቅነው ነገር የለም ጉዳዩ ግራ አጋቢ ሆኖብናል።

ለመቀበል ትንሽ ከብዶናል የእኛ ባች በርካታ ለውጦችን ያየ ነው ፣ ሬሚዲያል የተጀመረበት ነው ከሦስት እና ከአራት አመት በፊት ፍሬሽማን ኮርስ ተጀምሮ የሦስት አመት ዲግሪ ወደ አራት ከፍ አለ አሁን ደግሞ አገልግሎት ይጀምራል ከተባለ አምስት እና ስድስት አመት ልንቆይ ነው ማለት ነው።

ከትምህርት አለም ርቀን ድጋሚ ወደ ትምህርት አለም መመለስ ማለት ከባድ ነው የዲፓርትመንት ኮርሶች ተያያዥ ኮርሶች ስለሆኑ አንድ አመት መስክ ላይ ቆይቶ በድጋሚ ወደ ትምህርት መመለስ የዩኒቨርሲቲ ቆይታችንን ከባድ ያደርግብናል።

መውጫ ፈተና ያለብን ከመሆኑም አኳያ የንባብ ጊዜያችንን የሚያጣብብ በመሆኑ ለመቀበል ከብዶናል።

አገልግሎቱን ብንቀበለው እንኳን ለምሳሌ የህክምና ተማሪዎች ኢንተርንሺፕ እየወጡ ነገር ግን የሚመረቁበት አመት አይገፋም የእኛም ቢሆን ደስ የሚለን ተመሳሳዩን መንገድ ነው።

' ታስተምራላቹ ' ከተባለ እንኳን የትኞቹ ተማሪዎች እና ምን አይነት የአቅም ደረጃ ላይ ያሉት ያስተምራሉ የሚለው ግልጽ አይደለም።

ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለክረምት እረፍት ሦስት ወር ከሰኔ ጀምሮ እስከ ነሐሴ እናርፋለን ይህንን ሦስት ወር አገልግሉ በተባልንበት ቦታ ሁሉ አገልግለን በቀጣይ አመት ወደ ትምህርታችን መመለስ ነው የምንፈልገው።

ካለቀ በኋላ አስተምሩ ብንባል በበጎ ፈቃድ ወጥተን በደስታ እናገለግላለን ነገር ግን አንድ አመት ተገፍቶ ከሆነ ግን ከትምህርቱ መንፈስ እንወጣለን።

ዛሬ ነገ ይመረቅልኛል ብሎ የሚጠብቅ ወላጅ አንድ አመት ተጨምሯል ስትላቸው ተስፋቸው እያጠረ ይመጣል አብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የደሃ ልጅ ነው በደሃ ቤተሰብ ላይ አንድ አመት መጨመር በጣም ይከብዳል።

በምን አይነት መንገድ ተገምግሞ እዚህ ሃሳብ ላይ እንደተደረሰ ባይገባንም በውሳኔው ደስተኞ አይደለንም የምደባ ቦታችንም አሳስቢ ነው "ሲሉ ገልጸዋል ።

በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
9
የተማሪዎች የሥነ ምግባር ረቂቅ መመሪያ በውስጡ ምን ምን አካቷል?

"Crazy day፣ olds day፣ Valentine day " እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር ይከለክላል።


መመሪያው በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ፣ የግል፣ በኃይማኖት ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶችና ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በሚማሩ ተማሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

በመመሪያው የተማሪዎች መብትና ግዴታዎች ሲቀመጡ በተማሪዎች ግዴታ ስር ፀጉርን በአግባቡ መሰራት/ማሳጠር፣ ከተፈጥሯዊ ጸጉራቸው ውጪ እንዳይጠቀሙ ተቀምጧል።

የሴቶቾ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ ቀሚስ ቁመት ከባት በታች መሆን ያለበት ሲሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን ልብስ መልበስ የሚለውም ተካቷል።

በመመሪያው ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ ጫት መቃም፣ ዕፆችን መጠቀም/ማዘዋወር እንደዚሁም ሞባይልና የሙዚቃ ማዳመጫዎችን ወደ ትምህርት ቤት ይዞ መምጣት ይገኙበታል።

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ኃይማኖታዊ አምልኮ ስርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማከናወንም በመመሪያው ተከልክሏል።

በመመሪያው ሀገራዊ እሴት ያልሆኑ መጤ ነገሮችን በሰውነት ላይ መነቀስ ሲከለከል፤ ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም ከመቀባትና ከመኳኳል እንደዚሁም አላስፈላጊ ጌጥ ከማድረግ ይከለክላል።

በተጨማሪም በረቂቁ  በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ ያላቸውን ድርጊቶች (Crazy Day, Gentle Day, Olds Day, Baby Day, Fruit Day, Tomato 
Day, Valentine Day, April the full, Color Day, Pyjama Day…etc) መፈጸም፤ እና ሌሎችም አላስፈላጊ የሆኑ ባህልን የማይገልፁ ድርጊቶችን ማክበር እንደማይቻል ተገልጿል።

የተከለከሉ ተግባራትን በሚፈፅመት ላይ የተለያያ የእርምት እርምጃዎች ሲቀመጡ ቀላል እርምጃ ሊያስወስዱ በሚችሉ ጥፋቶች ስር ከፀጉር ጋር የተያያዙ እና ሌሎች ቀላል ጥፋቶች ተካተዋል።

የትምህርት ቤት ፕላዝማና ኮምፒውተር ለሌላ አላማ መጠቀም፣ በአጥር መዝልና መሽሎክ፣ ከላይ የተጠቀሱ አላስፈላጊ ባህሎችን ማክበር፣ አሉታዊ ምልክቶችን መነቀስ፣ ድብድብ እንደዚሁም ኃይማኖታዊ ስርዓት መፈፀምና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በከባድ ጥፋት ውስጥ ተካተዋል።

የቅጣት እርከኑ እንደ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃና ጥፋቱ ሲለያይ ለከባድ የስነ ምግባር ግድፈት  በመደበኛ ህግ መሰረት የህግ ተጠያቂነት ይኖራል።

መመሪያው የዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴ ስብጥር እንደዚሁም ተግባርና ኃላፊነትን በዝርዝር አስቀምጧል።

በተጨማሪ መመሪያው በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትን ተግባርያ ኃላፊነትም ዘርዝሮ ሲያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለ መሸኛ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብንም ከልክሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በመመሪያው ላይ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች በ  https://forms.gle/R72ai6EiMnzZtGsC6 እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

@TikvahethMagazine
4
የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው ረቂቅ ደንብ በውስጡ ምን ይዟል?

በመላ ሃገሪቱ ባሉ ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉ የመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ትምህርት ቤቶችና አካባቢው ተፈፃሚ ይሆናል የተባለው ይህ ረቂቅ ደንብ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰብሳቢነት የሚመራ ግብረ-ኃይል ጭምር እንዲቋቋም የሚያስችል አሰራር ዘርግቷል።

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምህርት ቤቶችና አካባቢው ተብለው የተለዩት ከትምህርት ቤቱ እስከ 500 ሜትር ባለው ርቀት ውሰሰጥ ያሉ አከባቢዎች ናቸው።

ደንቡን ለማውጣት በትምህርት ተቋማትና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ተግባራት በመስፋፋታቸው፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተማሪዎች ለአደንዛዥ ዕፆችና አደገኛ መድኃኒቶች ተጋላጭነታቸው እየሰፋ መሄዱ በምክንያትነት ተቀምጧል።

በዚህ ደንብ መሰረት በትምህርት ቤቶችና አካባቢው የተከለከሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው ?

- ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ "ዲ.ኤስ.ቲቪ" ቤቶች፤ ከረንቡላ፣ ፑል፣
ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶች፤

- የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፤ የሰውነት መታሻ ቤቶችና የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች፤

- የሲጋራ መሸጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፤ የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝሪያ ያላቸው ህገወጥ መድሃኒቶችና ሱስ የሚያስዙ ዕፆች [ይዞ መገኘት]፤

- በመማር ማስተማሩ ላይ ተፅዕኖ የሚያደርጉ ድምፅ፣ ጫጫታ፣ መጥፎ ጠረን የሚያወጡ፣ የትራፊክ ፍሰት፣ ገበያ፣ ፋብሪካ፣ ወፍጮ ቤቶች፣ ብረታ-ብረት ብየዳ ቤቶች፣ እንጨት መሰንጠቂያ ቤቶች፣ ጋራዥ ቤቶች፣ አውቶብስ ፌርማታዎች እና የጣውላ ውጤት ማምረቻ ድርጅቶችን ያጠቃልላል።


እነዚህ ተግባራት “ትምህርት ቤትና አካባቢ” ተብለው በተለዩ ማለትም የትምህርት ቤት ግቢውን እና በሁሉም አቅጣጫ ከአጥሩ እስከ 500 ሜትር ርቀት ባለው ቦታ ላይ መፈጸም ይከለክላል።

ይህንን ተግባር ማን በበላይነት ይመራዋል ?

በዚህ ደንብ መሠረት በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ነገሮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በፌደራል ደረጃ “ተከላካይ ግብረ-ኃይል” እንደሚቋቋም ይገልጻል።

ይህ ግብረ-ኃይል ም/ጠ/ሚኒስትሩ በሰብሳቢነት የትምህርት ሚኒስትሩ በም/ሰብሳቢነት የሚመራ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ 6 ሚኒስትሮችን በአባልነት ያካተተ ነው።

በተጨማሪም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰብሳቢ፤ የመምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት፤ የሲቪክ ማህበራት ፕሬዝዳንት፤ የተማሪዎች ወላጆች ህብረት ፕሬዝዳንትን በአባልነት ያካተተ ነው።

ተከላካይ ግብረ-ኃይሉ ይሄንኑ ተግባር ወደ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማውረድ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

በትምህርት ቤትና አካባቢ የተከለከሉትን ተግባራት ፈፅሞ የተገኘ ምን ይቀጣል ?

ህጉን ለተላለፉ፥ በቅጣት ደረጃ ከ10,000 ብር - 150,000 ብር የገንዘብ ቅጣት በረቂቅ ደንቡ ተቀምጧል። ለምሳሌ፦

- የጫት መሸጫና መቃሚያ የከፈተ 50,000 ብር እና ቦታውን መዝጋት፤

- ማንኛውንም ዓይነት ቁማር ቤት የከፈተ 150,000 ብር እና ቁማር ቤቱን መዝጋት፤

- የሰውነት መታሻ/Massage House ቤት የከፈተ 150,000 ብር እና ማሳጅ ቤቱን መዝጋት የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ቀድሞ በተከፈቱት ላይ ደንቡ ተግባራዊ ይሆናል ?

ይህ ደንብ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ትክክለኛውን ርቀት ሳይጠብቁ በትምህርት ቤትና አካባቢ የተከፈቱ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮች ላይ ደንቡ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን የማስተካከያ ጊዜን እና የማካካሻ ጉዳይን በተመለከተ በዝርዝር መመሪያ የሚወሰን
ይሆናል ሲል አስቀምጧል።

በተጨማሪም በረቂቅ ደንቡ ማንኛውም የንግድ ፈቃድ ሰጭ አካል ፈቃዱን ለንግድ ፈቀድ ጠያቂው ከመስጠቱ በፊት የነጋዴውን የስራ ቦታ ከትምህርት ቤት ያለውን ርቀት በምልከታ ማረጋገጥ አለበት ይላል።

በደንቡ ላይ ምክረ ሃሳብ ለመስጠት https://forms.gle/HisAZoyTpmo1ZFCA6 መጠቀም ይቻላል።

#TikvahEthiopia

@TEMARI_Net1
4
🔥 Build an Idea. Change the World. 🌍
Hult Prize is finally here at Addis Ababa University — and YOU could be the next million-dollar founder! 💡💰

Are you passionate about solving real problems?
Do you dream of launching your own startup?
Then this is your moment.

Why Join Hult Prize?
✔️ Learn global entrepreneurship skills
✔️ Build a startup from scratch
✔️ Work with amazing teammates
✔️ Pitch your idea on an international stage
✔️ Stand a chance to win $1,000,000 to grow your startup!

This is more than a competition — it’s a life-changing journey.
If you believe your idea can make the world a better place, Hult Prize is where you start.

🔥Updates dropping soon!🔥

🔥 Big updates are coming. Stay close.

JOIN US: [
HERE]

Follow us for all announcements:
Telegram | LiinkedIn | Instagram | TikTok
Research paper በምትሰሩበት ወቅት ለReference የሚጠቅሟችሁን research paper ማግኘት የሚያስችሏችሁን ድረገፆች እንደሚከተለው አሰናድተንላችኋል።

ssrn.com ከዚህ ቀደም የተሰሩ በርካታ research papers የምታገኙበት እና download ማድረግ የሚያስችላችሁ ድረገፅ ነው።

Journals.sagepub.com እንደ health እና social scince ያሉ feild ላይ የምታጠኑ ከሆነ ይህ ድረገፅ ሊጠቅማችሁ ይችላል። Advanced search የሚለውን በመንካት በተሰሩበት ቀን filter ማድረግ እና search ማድረግ የሚያስችል featureም አለው።

Springeropen.com በርካታ የተሰሩ research papers የምታገኙበት ሲሆን ጥሩ የሚባሉ papers ልታገኙበት ትችላላችሁ።

Sciencedirect.com በቅርብ የተሰሩ research papers የምታገኙበት ድረገፅ ነው።

Researchget.com በርካታ ሪሰርቸሮች የሰሩትን ሪሰርች እዚህ ድረገፅ ላይ upload ስለሚያደርጉ በርካታ research papers ማግኘት ትችላላችሁ።

©bighabesha_softwares

@TEMARI_Net1
2