TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.1K subscribers
911 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
ቴሌግራማችሁን update አድርጉት አዳዲስ ዝማኔዎች ተጨምረዋል።

Group call
ከዘህ በፊት ከ2 በላይ Group call ለማድረግ የግድ Group create ማድረግ ግዴታ ነበር። አሁን ግን Group create ማድረግ አይጠበቅብንም። አንድ ለአንድ እያወራን ሌሎች ሰዎችን add ማድረግ እንችላለን።

How to start a group call
From an existing call. Just call anyone on Telegram, then tap the 'Add Person' button in the top right corner of your screen — and you're all set.
From the Calls Tab. Open your Calls Tab (you may need to enable it via Settings > Recent Calls), then tap New Call and select multiple people to call.
Using a link. In the Calls Tab, tap New Call, then select New Call Link.

Automated Business Accounts
Telegram premium ተጠቃሚዎች በTelegram business feature ላይ 3rd party chatbot በጨመር ይችላሉ።
እነዚህ ቦቶች message automatically መመለስ ይችላሉ፤ profile manage ማድረግ ይችላሉ፤ gift & star manage ማድረግ ይችላሉ፤ story manage ማድረግ ይችላሉ። ከ10 በላይ automated ተግባሮችን መፈጸም ይችላሉ።

Easily share

የቻናል post ላይ የshare ቀስቷን ጫን አድርጎ በመያዝ ለሰዎች ወይም ለራሳችን በቀላሉ share ማድረግ እንችላለን።

Frozen account
contact ላይ save ላላደረጋችሁት ሰዎች በተደጋጋሚ spam message የምትልኩ ከሆነ፤ ወይም በአካውንታችሁ scam የምታደርጉ ከሆነ አካውንታችሁ freeze ሊደረግ ይችላል። freeze ከተደረገ message መላክ አትችሉም፣ groupና ቻናል ላይ መፃፍ አትችሉም። Read-only mode ስለሚሆን ማንበብና ማየት እንጂ ምንም አይነት ሌሎች ተግባሮችን መፈጸም አትችሉም።
Appeal ማድረግ ግን ትችላላችሁ።

በመጨረሻም Telegram ይህን ብለዋል።
"We welcome security researchers to study the detailed documentation and open source code that powers the new group calls. For more than 10 years, Telegram has offered over $100,000 to anyone who could crack its encryption protocol — and no one has ever succeeded."😂😂
🔥1
#4kilo_Culture_Day
Date Postponed!🚨

📆 New Date: Saturday, May 10 at 5LT
📍 Location: 4-Kilo Campus

Due to financial and sponsorship inconvenience, our Culture Day has been postponed.

We sincerely apologize for the change and truly appreciate your understanding.

Come dressed in your vibrant cultural attire as we unite to honor our heritage!

Proudly brought to you by 4Kilo GC Committees

If you want cultural clothes DM @Asuela16 
or
📞  0943300613
  📞 0962638245
Place; Shiromeda አዳራሽ ( ቁጥር 122 ፈ)

#CultureDay #UnityInDiversity #DemakEvents #AddisAbabaUniversity #AAU #4kilo


@TEMARI_NET1
ስልክ ከመግዛታችሁ በፊት ስለስልኩ በዝርዝር ማዋቅ ከፈለጋችሁ እነዚህን 3 ድረ ገፆች check አድርጋቸው።

1. https://nanoreview.net/
2. https://www.gsmarena.com/
3. https://versus.com/


@TEMARI_NET1
#Update

Most people love extracting audio more than video—it's just so convenient! 🎵 In response to popular demand (and my friend's request), @SaveLink_Robot now supports audio extraction from videos across multiple platforms. 

Currently supported platforms: Instagram, Facebook, X (Twitter), YouTube, and Pinterest

Simply download a video, and @SaveLink_Robot will ask if you'd like the audio version too! 🎧 

Try it out today and make your playlists even better! 

#AudioExtraction #SaveLinkRobot #VideoToAudio #DownloadMusic #TechForLife #SocialMediaTools #YouTubeDownload #InstagramAudio #PinterestAudio #DigitalConvenience 
Internship Opportunity at the African Union!

The AU Internship Program is open for applications! Gain hands-on experience, develop professional skills, and work in a multicultural environment. Apply Now: https://wp.me/p23f03-7uu

🔹 50 Internship Positions Available
🔹 Open to final-year students & recent graduates from AU Member States
🔹 Various departments across the AU Commission
🔹 3-month internship, renewable once

Important: Completing the AU CV template is MANDATORY for your application!

Apply Now: https://wp.me/p23f03-7uu
📅 Deadline: December 31, 2025

📍 Location: Addis Ababa, Ethiopia


@Temari_Net1
👍2
#MoE

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 50 ሺህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ከደረጃ በታች ናቸው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻልና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻያ ኃላፊ ዳዊት አዘነ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እስካሁን ከ7,900 በላይ የቅድመ መደበኛ፣ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ የ29,900 ትምህርት ቤቶች እድሳትና ጥገና ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል፡፡

©️tikvahuniversity

@Temari_Net1
👍2😁2💔1
#MoE

በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እንዳሉት፥ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ተግባራቸው አድርገው" ሊሠሩ ይገባል።

በዚህም በዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጥሮ የተሰጡ የአካባቢው ፀጋዎች ላይ ራዕይ ይዘው መሥራት እንደሚገባቸው አንስተዋል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በማዕድን ላይ ሰፊ ምርምር በማድረግ ሀገርን የሚጠቅም ሥራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

©️tikvahuniversity

@Temari_Net1
#ዲቪ2026 ውጤት ይፋ አልተደረገም ‼️


በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ዲቪ 2026 ውጤት ይፋ ተደርጓል የሚል መረጃ በማየት አልሰራ አለን ብላቹህ በውስጥ ለምትጠይቁን የቻናላችን ቤተሰቦች ዲቪ 2026 ከዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከአንድ ሰዓት በፊት ይፋ አይደረግም።


የዲቪ 2026 ውጤት ይፋ በተደረገ ቅጽበት መረጃውን የምናጋራቹህ ይሆናል።


📌አምና ዲቪ 2025 ቅዳሜ 04_May 2024 ምሽት አንድ ሰዓት ውጤት ይለቀቃል ተብሎ እኩለ ሌሊት ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ዘንድሮም ከምሽት አንድ ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ባለው ጊዜ እንደሚለቀቅ ይጠበቃል።



፨ የዲቪ አሸናፊዎች ግላዊ መረጃዎችን እንደ Confirmation number እና date of birth ያሉ መረጃዎቻችሁን ለማታምኑት ሰው አሳልፋቹህ አትስጡ።

@TEMARI_NET1
👍2
Happy World Press Freedom Day!


On this #WorldPressFreedomDay, we celebrate the courage of journalists who speak truth to power and the freedom that keeps democracy alive.
Let’s protect press freedom — because without it, there’s no freedom at all.

@Temari_Net1
👍1😁1
TEMARI-NET
#ዲቪ2026 ውጤት ይፋ አልተደረገም ‼️ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ዲቪ 2026 ውጤት ይፋ ተደርጓል የሚል መረጃ በማየት አልሰራ አለን ብላቹህ በውስጥ ለምትጠይቁን የቻናላችን ቤተሰቦች ዲቪ 2026 ከዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከአንድ ሰዓት በፊት ይፋ አይደረግም። የዲቪ 2026 ውጤት ይፋ በተደረገ ቅጽበት መረጃውን የምናጋራቹህ ይሆናል። 📌አምና ዲቪ 2025 ቅዳሜ 04_May…
ዲቪ 2026 ይፋ ሆኗል‼️

የአሜሪካ ዲቪ (Diversity Visa) ሎተሪ 2026 ዛሬ ምሽት ይፋ መደረጉን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አሳውቋል።

መ/ቤቱ፥ አመልካቾች መመረጥ አለመመረጣቸውን / ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማየት የሚችሉት በ dvprogram.state.gov/ESC/ ላይ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት #ብቻ መሆኑን አሳስቧል።

📌ከዚህ ውጭ የዲቪ ውጤት የሚታይበት ምንም አይነት መንገድ የለም።

N.B. ዲቪ የሚደርሳቸው ሰዎች የሚስጥር ቁጥሩን እስከ ቀጣይ አመት መስከረም መጨረሻ ቀናት መያዝ አለባቸው።

ምናልባት "ዲቪ ደርሷችኃል ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው የምንደውለው፣ ኢሜል / ቴክስት መልዕክት የሚንልከው " የሚሉ አጭበርባሪ ስለሚኖሩ ጥንቃቄ አድርጐ።

እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ፥ የዲቪ ተመራጭ መሆን ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ #ዋስትና አይሆንም።

የዲቪ ሎተሪ ተመራጭ መሆን የቪዛ ጥያቄ ለማቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ሲሆን በቀጥታ ለቪዛ ወይም ለቃለመጠይቅ ዋስትና አይሰጥም። (Selection does not guarantee an interview or a visa.)

@Temari_Net1
1👍1
#FYI

አ.አ ነገ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች!!

116ኛውን የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በዚህም መሠረት፦

👉 ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ
👉 ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ
👉 ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
👉 ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ
👉 ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ )
👉 ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ
👉 ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ወደ ለገሃር መብራት
👉 ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ
👉ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት
👉ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ )
👉ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል
ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ
👉ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
በተጨማሪም፦
👉 ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም
👉 ከብሔራዊ ቤተጰመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ማለትም ከ25/08/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ሲሆን እንዲሁም ለዚሁ ፕሮግራም ሲባል ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

  @TEMARI_NET1
👍2
#MoH

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተመዛኞች ከዛሬ ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0115186275 / 0115186276 ላይ በመደወል  ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሚያዝያ 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ክልል ተቆጣጣሪ አካላት በመሔድ የሚጠበቅባችሁን ቅድመ ሁኔታዎች በሟሟላት የሙያ ፈቃድ መውሰድ የምትችላላችሁ ተብሏል።

የስም ፊደል ግድፈት ያለባችሁ ተመዛኞች ሙሉ በሙሉ የስም ትርጉም ለውጥ ከሌለው በስተቀር ከዲግሪያችሁ ጋር በማመሳከር የምትስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

@Temari_Net1
👍1
ግራኝ ሰዎች ቢሊየነር የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው።

በዓለም ላይ ባሉ 500 ትላልቅ ኩባንያዎች መሪዎች መካከል የግራ-እጅ ሰዎች በግልጽ በብዛት ይታያሉ። ለምሳሌ እንደ ቢል ጌትስ፣ ስቲቭ ጆብስ እና ማርክ ዙከርበርግ ያሉ ታዋቂ ሥራ ፈጣሪዎች እንደዚህ ነበሩ። ከዚህም በላይ በ1000 ከፍተኛ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል 91 በመቶ የሚሆኑት ግራ-እጅ የሆኑ ሲሆኑ የኩባንያዎቻቸው የፋይናንስ አፈጻጸም ከአማካይ ገበያ በእጅጉ የላቀ ነበር።

ይህ የሚያመለክተው ግራ-እጅ መሆን ለተሳካ የንግድ አመራር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ልዩ የእውቀት ችሎታዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ያመላክታል።
Via፦ ፊደል ፖስት

ግራኞች የታል ብሩ😁

@TEMARI_NET1
😁9😐3👍1
የቻይና ግዙፉ የሀይል ማመንጫ Three Gorges dam የምድርን ሽክርክሪት እየቀነስ እንደሆነ ተነገረ።

የNASA ሳይንቲስቶች የቻይና ግዙፉ የሀይድሮ ኤልክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ (Three Gorges dam) የምድራችን አክሲስ በ2 ሴንቲ ሜትር ሽፍት እንዳደረገ አረጋግጠናል ብለዋል።

ይህም የቀኑን ርዝመት በ0.06 ማይክሮ ሰከንድ እንዲጨምር አድርጎታል።

ይህ ትልቅ የኃይል ማመንጫ በአመት 80 ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችን ያለማቆራረጥ ሀይል የሚሰጥ ሲሆን ከአዲስ አበባ ባህርዳር የሚሆን ቦታ ይሸፈናል።

@TEMARI_NET1
👍2😁1
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት በኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መስጠት ይጀምራል።

እ.አ.አ. በ2026 ከ2ዐ እስከ 25 ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር ዩኒቨርስቲው ገልጿል።

ለዚህም ዩኒቨርሲቲው ከቻይናው ሽንግዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የካሪኩለም ቀረጻ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል እንዲሆን መመረጡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እና የቻይናው ሽንግዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስር የአፍሪካ ኑክሌር ሳይንስ ማዕከል እንዲቋቋም ስምምነት ተደርጓል፡፡

ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ባለፈ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የሚመጡ ተማሪዎች የሚቀበል መሆኑ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው አምስት ኢትዮጵያውያንን ወደ ሩሲያ እና ቻይና በመላክ በኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመጀመርያ ዲግሪ ሥልጠና ላይ መሆናቸውንና የመጨረሻ ዓመት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

የኑክሌር ሳይንስ ቴክኖሎጂ ማዕከሉን ሥራ ለማስጀመር ብቻ 200 ሚሊዮን ብር ይፈጃል የተባለ ሲሆን፤ ወጪውን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡ #ሪፖርተር

©️tikvahuniversity

@TEMARI_NET1
😁8👍4🔥2👏2
ከተማሪዎች ማደሪያ ክፍል ውስጥ የሞባይል ስልኮችና ላፕቶፕ የሰረቁ በእስራት ተቀጡ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኝ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍል ( Dormitory )ከሌሊቱ 8፡30 ሠዓት ገደማ ነው፡፡

ተከሳሾች ኃ/ማርያም ደጉና ተመስገን ጌትነት የተባሉ ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲ ካምፓሱ ተማሪ የነበሩና ተመርቀው የወጡ ሲሆን በተጠቀሰው ዕለት ወደ የተማሪዎች ማረፊያ ክፍል ( Dormitory ) በመግባት ንብረትነታቸው የተማሪ ኤርሚያስ ክንዳለምና ኢዮብ ስማቸው የሆኑ ግምታቸው 15 ሺህ እና 11ሺህ ብር የሚያወጡ ሁለት የሞባይል ስልኮችን እንዲሁም ግምቱ 43ሺህ ብር የሚያወጣ አንድ ላፕቶፕ ሰርቀው በግቢው ውስጥ ከሚገኝ መፀዳጃ ቤት አካባቢ ዕቃውን ሰውረዋል፡፡

ነገር ግን በሰዓቱ በተማሪዎቹ ዶርም አካባቢ ከተፈፀመው የስርቆት ወንጀል ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ግርግርም በጥበቃ ስራ ላይ የሚገኙ የግቢው ፖሊስ አባላት በሚመጡበት ወቅትም ተከሳሾች በአጥር ዘለው ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርጉም ባለመሳካቱ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

በወቅቱም የንብረቶቻቸውን መጥፋት ያወቁት የግል ተበዳይ ተማሪዎች በስልኮቻቸው ላይ ተደጋጋሚ ጊዜ በመደወል ዕቃዎቹ ከተደበቁበት መፀዳጃ አካባቢ ጥሪ በመሰማቱ ዕቃቸውን ሊያገኙም ችለዋል፡፡

የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም መረጃ የደረሰውም የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያም ተከሳሾችን በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን የምርመራ ተግባር ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ፖሊስ በተከሳሾች ላይ ተገቢውን ማስረጃ በማደራጀት በዐ/ህግ በኩል ክስ እንዲመሰረት ያደረገ ሲሆን ተጣርቶ የቀረበለትን የወንጀል ምርመራ መዝገብ የተመለከተው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ፈጣን ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው ኃ/ማርያም ደጉን በ7 ዓመት እንዲሁም ተመስገን ጌትነትን በ4 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጡም ወስኖባቸዋል፡፡

በትምህርት ተቋማት አካባቢ ያለው የደህንነት ሁኔታ መጠናከር እንዳለበት የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የጥበቃ ባለሙያዎች ወደ ግቢው የሚገቡና የሚወጡ ማንኛቸውንም ግለሰቦች መታወቂያ በሚገባ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

ምንጭ:- አአ ፖሊስ

@TEMARI_NET1
😁10👍6💔3🙏21
Students competition_GC69 2025docx_250505_163117 2.pdf
179.6 KB
Dear AAU community 

We hereby attach an opportunity for female students interested in Nuclear sciences and Technology.
Note that the deadline for application is on May 30 , 2025.

For further information , refer to the attached pdf file.

Good Luck 

@TEMARI_NET1
ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማቅረብ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል- አቶ አረጋ ከበደ

ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን በማቅረብና በመተግበር የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡

በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 24ኛው የጋራ ፎረም ጉባዔ በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ በ"ቨርቹዋል" ንግግር ያደረጉ አቶ አረጋ ከበደ ÷ ዩኒቨርሲቲዎች የማሕበረሰብን የእድገት ደረጃ በመቃኘት አጋዥ ተግባራት ላይ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

የአማራ ክልልን ኢኮኖሚ እድገት ማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱን ጠቁመው ÷ይህም ክልሉ ከገባበት ዘርፍ ብዙ ቀውስ እንዲወጣ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ የመልማት ጸጋን መሠረት ባደረገ መልኩ ስድስት የልማት ኮሪደሮች መለየታቸውን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡

ስለሆነም ዩኒቨርሲቲዎች ይህን ባገናዘበ መልኩ በጥናት፣ በምርምር እና በማማከር አገልግሎት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡

ክልሉ ካጋጠመው ማህበራዊ ቀውስ እና ዘርፈ ብዙ ችግር እንዲወጣ ዩኒቨርሲቲዎች በጥናትና ምርምር የታገዘ የመፍትሔ ሃሳብ እንዲያቀርቡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚህ ረገድ የክልሉ መንግስት ለዩኒቨርሲቲዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

@TEMARI_NET1
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ምልመላ ማድረግ ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መልምሎ ለማስተማር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን በማካሔድ ላይ ይገኛል።

በዚህም ከመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሒዷል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ቅበላና ምልመላ ዙሪያ ገለጻ ከተደረገላቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ይጠቀሳሉ።

በወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በፈጠራ ክህሎት ልዩ አቅም ያላቸው ተማሪዎች በውድድር ዩኒቨርሲቲውን መቀላቀል እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጤና፣ በኢንጅነሪግ እና ሌሎችም የሙያ ዘርፎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት መገለፁ ይታወሳል።

©️tikvahuniversity

@TEMARI_NET1
👍1