TEMARI-NET – Telegram
TEMARI-NET
4.11K subscribers
911 photos
17 videos
167 files
288 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ።

የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።

በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡

በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ ከላይ ተያይዟል።

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው ተብሏል።

መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተላከ ነው።

©️tikvahethiopia

@TEMARI_NET1
👍1
Let’s Help Save the Life of Journalist Addis Chekol !

Addis Chekol has served as the Ethiopian correspondent for Voice of America’s Horn of Africa Service for over six years. Based in Dire Dawa, he has diligently reported on the city and its surrounding areas.
Known for his professionalism, integrity, and compassionate spirit, Addis has also built a strong following through his active presence on social media.

https://gofund.me/6b954aa5
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም


@TEMARI_NET1
👍3
GC cup final at main campus
Accounting vs commerce second half result
Acc 2-1 com
👍1
አስቸኳይ!!

ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች የባህል ቀን /culture day በሜዳ በፍቃድ ምክንያት ከዋናው ግቢ ወደ ኤፍ ቢ ኢ ተቀይሯል።

ከ 7:30 ጀምሮ ስለሚካሄድ ወደዚህ ኑ!
GC Committee 🥰
@TEMARI_NET1
👍1
Happy mother"s day
እድሜና ጤና ለሁሉም እናቶቻችን ይሁንልን✍️🙏🙏🙏



@TEMARI_NET1
16👍1
#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።


@TEMARI_NET1
ትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አጋዥ portal ይፋ አድርጓል።

እዚህ Portal ላይ
ለተለያዩ የትምህርት አይነቶች የቪዲዬ tutorial ታገኛላችሁ።
የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ታገኛላችሁ።
የonline መፈተኛ ጣቢያችሁን ማየት ትችላላችሁ።
https://examinfo.moe.gov.et/guides

የመፈተኛ Portal
https://exam8.ethernet.edu.et
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሻሽሎ ባወጣው የአካዳሚክ ካላንደር የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ያሳያል።

ዩኒቨርሲቲው የ2017 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ሰኔ 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

(የተሻሻለው የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል፡፡)

@TEMARI_NET1
🤬4👏3
የመውጫ ፈተና በድጋሚ መውሰድ ለምትፈልጉ በሙሉ


የዳግም ምዝገባ ቀነ ገደብ  እስከ ግንቦት 5 ፣

ለመመዝገብ👇
https://exam.ethernet.edu.et

Step 1 Provide Username

Step 2 Verify Fayda ID

Step 3 Review Fayda Profile

Step 4 Update Preference

Step 5 Complete Payment and Registration
👍1
የዜጎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በነጻ የቀረበው የኮደርስ ስልጠና

የዜጎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ኢትዮጵያ በነጻ እንዲቀርብ ያደረገችው የኮደርስ ስልጠና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚጠይቅ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካሪ አብዮት ባዩ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ፕሮግራም ወጣቶች የዲጂታል ክህሎት ኖሯቸው በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያስችላል ብለዋል አማካሪው፡፡

የሚሰጡ ስልጠናዎችም፤ በፕሮግራሚንግ፣ በዳታ ሳይንስ እና በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በተለያዩ የሥራ መስኮች አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ አሁን እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን በዲጂታል ለመደገፍ እና ተወዳዳሪ ለመሆን ስልጠናው እንደሚያግዝም ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ስልጠናዎች ግለሰቦች በውጭ ምንዛሪ ክፍያ በመፈጸም የሚያገኟቸው መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህ ለአብዛኛው የሀገራችን ወጣት አዳጋች መሆኑን በመገንዘብ መንግሥት በነጻ ማቅረቡን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም ዕድሉን በነጻ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

በተሰጠው ስምንት ሳምንት ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ፥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትልዎታል።

@TEMARI_NET1
👍3
የኢመደአ የ2017 ዓ/ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) #INSA ላለፉት ሦስት ተከታታይ አመታት በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸዉን ታዳጊዎች እየመለመለ በማሰልጠን ወደ ተቋሙ እና ወደ ሳይበር ኢንዱስትሪዉ እንዲቀላቀሉ ሲያደርግ ቆይቷል። በያዝነው 2017 ዓ.ም ከባለፉት ሦስት አመታት በተሻለ ሁኔታ በመላ ሀገሪቱ ልዩ ታለንት ያላቸዉን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት እስከ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ያሉ በመመልመል ለ4ኛ ዙር ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም በሳይበር ደህንነት፤ በዴቨሎፕመንት፤ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ ላይ ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት (Talent with passion) ያላችሁ በታለንት ማእከሉ የቴሌግራም ቻናል ( https://news.1rj.ru/str/cteinsa ) በመግባት ስለ ፕሮግራሙ በቂ መረጃ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ቻሌንጁን ለመመዝገብ የሚከተለዉን ሊንክ ተጠቅማችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።  https://talent.insa.gov.et

@TEMARI_NET1