TechVibe – Telegram
TechVibe
742 subscribers
460 photos
34 videos
33 files
208 links
I'm Eyob, a self-taught dev sharing my Tech journey, tips, tools, and real-world projects. Let’s grow together😊

DM for any project ideas @alnova19

Personal site: https://eyobsimachew.vercel.app
My Github: https://github.com/Eyob-smax
Download Telegram
በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመሥራት የተግባባ፣ የጋራ አስተሳሰብ ያለውና የወደፊቱን የተገናዘበ አመራር መስጠት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ።
--------------------------------------

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የምክክር መድረክ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የተገኙት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገራችንን የትምህርት ሥርዓት የመምራት እድል እንደተሰጠው አመራር በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር በመረዳት የተቀራረበ አመለካከት በመያዝ አመራር መስጠት ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ትምህርትን እያየን ባለንበት መንገድ መሥራት አንችልም ያሉት ሚኒሰትሩ በረጅም ጊዜ አቅደን ብቁ ተወዳዳሪ እና በስነ-ምግባር የታነፁ ልጆች ለማፍራት የሚያስችል ትምህርት እየሰጠን ነው የሚለውን ማሰብና መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በትምህርት ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህ ረገድ የጋራ አስተሳሰብ በአዲስ መልክና ማዕቀፍ መያዝ ይገባል ብለዋል።

አክለውም ከአጭር ጊዜ አስተሳሰብ ወጥተን የሚቀጥለውን ትውልድ በዓለም ተወዳዳሪ፣ ክህሎት ያለው፣ ግብረ ገብነትን የተላበሰ እንዲሆን ለማድረግ የጋራ አስተሳሰብ ይዞ መሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አሁን ዓለም ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት የተሻለ ብቃትና ክህሎት ያላቸው እንዲሁም በስነ ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ የሁሉም ክልልና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ሁሉንም ለማስደሰት እንደሚጥር ሰው ከንቱ የለም!  ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ነገር አይደሰትም እኮ ፤ በተለያየ ነገር ለሚደሰቱ ሰዎች ስንል ደግሞ እኛ እንደ ወረቀት መተታጠፍ የለብንም። ሁሉንም ለማስደሰት ስንሞክር ሁሉንም እናሳዝናለን !

🌟ምን እናርግ ታዲያ? ህሊናችን የሚነግረንን አይምሮአችን የሚያዘንን ልባችንን በደስታ የሚቀበለውን ብቻ መርጦ ማድረግ፤ ያኔ ሰዎች ቢደሰቱም ባይደሰቱም ህሊናችን ግን ምን ነካህ እያለ አያስጨንቀንም። ለህሊናው እንደሚታመን ሰው ሰላም የከበበው የለም!

🌐JOIN :
@mayaofficial19
TechVibe
2015 Grade 8 Maths model exam.pdf
➡️ለወድማቻቹ እና ለእህቶቻቹ አድርሱልን🥰

🌐JOIN :
@mayaofficial19
CH-8 ECONOMY, ENVIRONMENT AND CLIMATE CHANGE.pdf
279.3 KB
⬜️Economics short Note

🔥Unit :- 8

🌐JOIN : @mayaofficial19
CH-7 MACROECONOMIC REFORMS IN ETHIOPIA.pdf
323.2 KB
⬜️Economics short Note

🔥Unit :- 7

🌐JOIN : @mayaofficial19
CH-6 POVERTY AND INEQUALITY.pdf
313.8 KB
⬜️Economics short Note

🔥Unit :- 6

🌐JOIN : @Mayaofficial19
CH-5 TAX THEORY AND PRACTICE.pdf
373.8 KB
⬜️Economics short Note

🔥Unit :- 5

🌐JOIN : @mayaofficial19
CH-4 MACROECONOMIC POLICY INSTRUMENTS.pdf
748.5 KB
⬜️Economics short Note

🔥Unit :- 4

🌐JOIN : @mayaofficial19
CH3-Sustainable-Development Part - 3.pptx
1.6 MB
⬜️Economics short Note

🔥Unit :- 3

🌐JOIN : @mayaofficial19
Physics Entrance Exam 2024[@QesemAcademy] (1).pdf
540.5 KB
🧪 Physics Entrance Exam 2024 - በ ቀሰም Academy የተዘጋጀ

👑 ከ Grade 9-12 አዲሱን ከ ድሮ Curriculum ጋር በማቀናጀት የተዘጋጀ

MoE Standardized 50 Questions with Answer and Explanations

🌐 ልፍታችንን የምትረዱ ከሆነ ፣ ለሁሉም ተፈታኞች እንዲደርስ Share አርጉልን!

🌐JOIN :
@mayaofficial19
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።


@mayaofficial19 ✈️
Entrance Schedule

🌐JOIN : @mayaofficial19  | ከ High school እስከ Campus አበረናችሁ ነን!
በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በኦንላይን ለመስጠት እየተከናወኑ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።

በውውይይቱ የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል።

የመልቀቂያ ፈተናውን በአዲስ አበባ በበይነ መረብ ለመስጠት ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስፈልጉ፦

➭ ኮምፒውተሮች፣
➭ ላፕቶፖች፣
➭ ታብሌቶችና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከወዲሁ ማዘጋጀት በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሐግብር እንዲሰጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል። #አዲስአበባትምህርትቢሮ

🌐JOIN : @mayaofficial19  | ከ High school እስከ Campus አበረናችሁ ነን!