Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሀሰተኛ ሰነድን በመጠቀም ሊያጭበረብሩ የሞከሩ ግለሠቦች በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ
******
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ውስጥ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማስጨረስ በሚል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማያውቃቸው ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም አገልግሎቱን ለማግኘት በቀረቡበት ወቅት የያዙት ሰነድ ሀሰተኛ ወይም ትክክለኛ የተቋሙ ሰነድ አለመሆኑን በማረጋገጥ ወዲያውኑ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ እንዲያዙ ተደርገዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአሁኑ ሰዓት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ በርካታ የሪፎርም ፣ የአደረጃጀትና አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን አሰራሮች በኦንላይን ከሰው ንክኪ ነፃ እንዲሁም የዜጎችን ምልልስና እንግልት በእጅጉ ቀለል በሚያደርግ መልኩ ተግባራዊ አድርጓቸዋል።

ለተለያዩ የማጭበርበር ስራዎች የማይመች ሲሆን ከተገኘም በቀላሉ መለየትና መያዝ የሚያስችልም መሆኑ ተጠቅሷል።

የከተማው ነዋሪ ከእንዲህ አይነት ተግባር ውስጥ ካሉ አጭበርባሪዎች ተቆጥቦ በህጉ መሠረት ብቻ መብቱን በቀላሉና በፈለገ ሰዓት ያለምንም ምልልስና እንግልት አገልግሎት እንዲያገኝ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ከተማችንን ከህገወጦች እንዲጠብቅ የከተማ አስተዳደሩ ማሳሰቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
አርሶ አደሮች ምርታማነትን የሚያሳድግ አዳዲስ የቴክኖሎጅ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ማድረግ ይገባል
****
(ኢ ፕ ድ)

በክልሉ በሁሉም አካባቢ የታየው የሰብል ልማት ቁመና እንደሀገር ያለውን የምግብ ክፍተት ለመሙላት ትልቅ አቅም አለው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ተናገሩ።

የግብርናው ዘርፍ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በአርሶ አደሮች እየለማ ያለ የሩዝ ሰብልን በዛሬው እለት ተመልክተዋል።

ርዕሰ መሰተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ አካባቢው የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል የመልማት አቅም ያለው ነው። የፎገራ ሩዝ ሰብል ቁመናም በምግብ ራሳችን ለመቻል አበረታች ውጤት የታየበት ነው ብለዋል።

አርሶ አደሮች ምርታማነትን የሚያሳድግ አዳዲስ የቴክኖሎጅ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ማድረግ ይኖርብናል። የፎገራ ወረዳን ጨምሮ በኩታ ገጠም እርሻ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች የምርት መሰብሰቢያ ማሽን ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio
"ወደ ትግራይ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እርዳታ በብዛት እየገባ ነው"
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ወዳሉ የትግራይ አካባቢዎች ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እርዳታ በብዛት እየገባ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እና የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።
70 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ክልል በመከላከያ ስር እንደሆነና ወደእነዚህ አካባቢዎች እርዳታ በብዛት እየገባ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን አስታውቀዋል።
በ35 ተሽከርካሪዎች የተጫነ ምግብ እና 3 ተሽከርካሪዎች መድኃኒት ተጭኖ ሽሬ ገብቷል ብለዋል።
ወደ ክልሉ በረራ ተፈቅዷል፤ የተቋረጡ አገልገሎቶች እየተመለሱ ነው ለዚህ ደግሞ የሰላም ስምመነቱ አስተዋጾ አድርጓል ነው ያሉት።
ዕርዳታን በተመለከተ ምንም ዓይነት መሰናክል አይፈጠርም ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ አንዳንድ አካላት የአፍሪካውያን ጥበብ በፕሪቶሪያ ያመጣውን ስኬት ለማወክ ሲጥሩ ይታያሉ ሲሉም ገልጸዋል።
በወረቀት ዋጋ መናር እና በተደራራቢ ታክስ ምክንያት የኅትመት ዘርፉ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከወረቀት ዋጋ መናርና በተደራራቢ ታክሶች ምክንያት የኅትመት ዘርፉ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን የኢትዮጵያ አሳታሚዎችና አታሚዎች ማህበር አስታወቀ። በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥም ማህበሩ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ አሳታሚዎችና አታሚዎች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ዘነበ ደነቀ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ሲካሄድ እንደገለጹት፤ የወረቀት ዋጋ በየጊዜው እየናረ መሄድና ተደራራቢ ታክሶች የዘርፉ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል።
በወረቀት ዋጋ መናርና በሌሎችም የሕትመት ጥሬ እቃዎች ላይ የተጣለው ተደራራቢ ግብር ዘርፉን በእጅጉ እየፈተነው ነው ያሉት አቶ ዘነበ፤ በአንጻሩ ከውጭ ታትመው በሚገቡ መጽሐፍት ላይ የሚከፈለው ግብር አነስተኛ መሆን ችግሩን ‹‹በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› ይሉት አይነት አድርጎታል ብለዋል።
በመጻሕፍት ዝግጅት አታሚዎችንና አሳታሚዎችን እንደ ባለድርሻ ቆጥሮ አለማወያየት፣ የሕትመት ግብዓቶች እጥረት፣ የሰለጠነ የሰው ሀብት እጥረት፣
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85498
በመዲናዋ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመር እድሳት ተከናውኗል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ10 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ማደስ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ገበየሁ ሊካሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመዲናዋ ወደ ሁለት ሺህ ኪሎ ሜትር የመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመር አለ።
በአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመሮችን ለማደስ በአራት ምዕራፍ ተከፋፍሎ እየተሠራ ሲሆን ባለፉት የሥራው ሁለት ምዕራፎች ከ10 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሆነው ታድሷል።
ይህም የሚያሳየው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመር መልሶ ግንባታ አኳያ ሲሰላ 50 በመቶ የመካከለኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሥመር መልሶ ግንባታ ተጠናቋል የሚለውን ነው ብለዋል።
የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ጥገናው ለመዲናዋ ነዋሪዎች የማይቆራረጥና አስተማማኝ የሆነ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85485
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለማጓጓዝ ተዘጋጅቷል
***************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ረዥም ጊዜ የማይቆዩና ማቀዝቀዣ የሚፈልጉ ምርቶችን ለማጓጓዝ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ እንደገለጹት፤የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የአገሪቷን ገቢ በመጨመር በኩል አወንታዊ ሚና እያበረከተ ነው። በተለይም ወሳኝ የሆኑ ምርቶች በማጓጓዝ በኩል ውጤታማ ስራ አከናውኗል።
ለአብነትም ባለፈው በጀት ዓመት የአገሪቷ ዋነኛ የወጪ ምርት የሆነው ቡና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተጓጓዘው በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር በኩል መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም 55 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ማጓጓዝ መቻሉን ጠቅሰው፤ የአፈር ማዳበሪያን ሎጂስቲክስ በማሳለጥ ረገድም የተሻለ ስራ ተከናውኗል ነው ያሉት። በዚህም ለሎጅስቲክስ ይወጣ የነበረን 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85496
መንግሥት በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ለትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራል መንግሥት በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች 500 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የተለያዩ ድጋፎች እያቀረበ ይገኛል።
በሽራሮ፣ ሽሬ፣ አክሱምና አድዋ አካባቢዎች በጦርነቱ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የስንዴና የአልሚ ምግብ እየተከፋፈለ መሆኑን ገልጸዋል።
ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት በኋላ የተሻለ መረጋጋት በታየባቸው ተጨማሪ የትግራይ አካባቢዎች ላይም መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፉን ለማከፋፈል ዝግጅት ማድረጉን ጠቁመዋል።
በመጪው ሳምንት መጀመሪያ ላይ መንግሥት ተጨማሪ ድጋፍ ለማቅረብ አርባ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ወደትግራይ ያጓጉዛል ያሉት አምባሳደር ሽፈራው፤ በዚህም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ ድጋፎች ለህብረተሰቡ እንደሚከፋፈሉ አስታውቀዋል።
በቀጣይነትም ድጋፎቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ በየብስ መስመሮች ከሚደረገው የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በተጨማሪ በአየር
ሙሉውን ለማንበበ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85559
በሽሬ ዲስትሪክት ስር የነበሩ ሰባት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ስራ ጀመሩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ሽሬ ዲስትሪክት ስር የነበሩት የማይካድራ፣ ሁመራ፣ ቃፍታ ፣ አውሮራ፣ ዳንሻ፣ አዲ ረሚጥ እና ከተማ ንጉስ ቅርንጫፎች ስራ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ። በማይጸብሪ፣ በአይካል እና በአዲሄርዲ የነበሩ ቅርንጫፎችም በቅርቡ ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሽሬ ዲስትሪክት ስር ተጠቃሚ የነበረው ማህበረሰብ እንዳይቸገር ሲባል ለጊዜው በጎንደር ዲስትሪክት ስር ታቅፈው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ገልጸዋል።
እንደ አቶ አልሰን ገለፃ፤ የሽሬ ዲስትሪክት ሁሉም ቅርንጫፎች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እስከሚጀምሩ ድረስ ነው በጎንደር ዲስትሪክት አክሰስ አገልግሎት በመሰጠት ላይ የሚገኘው።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት በሽሬና መቀሌ ዲስትሪክቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አቁሞ እንደነበር ያወሱት አቶ አልሰን፤ ባንኩ ቀደም ሲል በጦርነቱ ምክንያት አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ዳግም ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ባንኩ ባደረገው ጥረት ተከዜ፣ አዲ ጎሹ፣ ቆራሪት፣ ማይጋባ፣ ሰቲት እና አደባይ ቅርንጫፎች ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85560
በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ያሉ አርሶ አደሮች ከተፈጥሮ ማዳበሪያ የምርት ጭማሬ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ
*****************;
(ኢ.ፕ.ድ)
በምዕራብ ጎጃም ዞን የደቡብ ሜጫ ወረዳ ፈለገህይወት ቀበሌ ግብርና ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ አትንኩት አላምረው፤ የውሃና መሬት ሀብት ማዕከል ጐርፍን ለማስቀረት፣ የተራቆተውን መሬት ለማልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከምርምር ጋር በማያያዝ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በዘረጋው “የመማሪያ ተፋሰስ” ፕሮጀክት የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
አርሶ አደሩ በተሰጠው የግንዛቤ ሥራ ወደ አገር በቀል ሥራ እንዲያዘነብል በመደረጉ የምርት ጭማሬንና የመሬትን ለምነት ከፍ ማድረግ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡
እንደ አገር ባጋጠመው የማዳበሪያ ግብዓት እጥረትና የዋጋ ንረት ምክንያት የአካባቢው....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85588
ጊዜና ወቅት ያልገደበው የበጎ አገልግሎት
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ድህነት ጥላውን ላጠላባቸው ነፍሶች ቤት ከመጠለያም በላይ ነው። ቤት ገመናን ሸፋኝ፣ የዘመናት እንባን አባሽ፣ ሀዘንን መርሻ፣ ዞሮ መግቢያ ነው። የክረምቱን መግባት ተከትሎ በበጎ ፈቃድ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የአረጋውያንን እና የአቅመ ደካሞችን ቤቶች ማደስ አንዱ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድሃኒት፣ የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንም በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የብዙዎችን ቤት ጎብኝቷል።ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ዝቅ ብሎ እጃቸው ላጠረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤታቸውን አድሶ ለባለቤቶቹ አስተላልፏል።
ወይዘሮ አብነት ቢሻው ይባላሉ፤ የመኖሪያ ጎጇቸውን በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ቀልሰዋል። ቤታቸው ወደ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85575