Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሽሬ ዲስትሪክት ስር የነበሩ ሰባት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ስራ ጀመሩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ሽሬ ዲስትሪክት ስር የነበሩት የማይካድራ፣ ሁመራ፣ ቃፍታ ፣ አውሮራ፣ ዳንሻ፣ አዲ ረሚጥ እና ከተማ ንጉስ ቅርንጫፎች ስራ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ። በማይጸብሪ፣ በአይካል እና በአዲሄርዲ የነበሩ ቅርንጫፎችም በቅርቡ ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሽሬ ዲስትሪክት ስር ተጠቃሚ የነበረው ማህበረሰብ እንዳይቸገር ሲባል ለጊዜው በጎንደር ዲስትሪክት ስር ታቅፈው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ገልጸዋል።
እንደ አቶ አልሰን ገለፃ፤ የሽሬ ዲስትሪክት ሁሉም ቅርንጫፎች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እስከሚጀምሩ ድረስ ነው በጎንደር ዲስትሪክት አክሰስ አገልግሎት በመሰጠት ላይ የሚገኘው።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተከስቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት በሽሬና መቀሌ ዲስትሪክቶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አቁሞ እንደነበር ያወሱት አቶ አልሰን፤ ባንኩ ቀደም ሲል በጦርነቱ ምክንያት አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ዳግም ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ባንኩ ባደረገው ጥረት ተከዜ፣ አዲ ጎሹ፣ ቆራሪት፣ ማይጋባ፣ ሰቲት እና አደባይ ቅርንጫፎች ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85560
በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ያሉ አርሶ አደሮች ከተፈጥሮ ማዳበሪያ የምርት ጭማሬ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ
*****************;
(ኢ.ፕ.ድ)
በምዕራብ ጎጃም ዞን የደቡብ ሜጫ ወረዳ ፈለገህይወት ቀበሌ ግብርና ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ አትንኩት አላምረው፤ የውሃና መሬት ሀብት ማዕከል ጐርፍን ለማስቀረት፣ የተራቆተውን መሬት ለማልማት የተፈጥሮ ሀብትን ከምርምር ጋር በማያያዝ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በዘረጋው “የመማሪያ ተፋሰስ” ፕሮጀክት የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
አርሶ አደሩ በተሰጠው የግንዛቤ ሥራ ወደ አገር በቀል ሥራ እንዲያዘነብል በመደረጉ የምርት ጭማሬንና የመሬትን ለምነት ከፍ ማድረግ እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡
እንደ አገር ባጋጠመው የማዳበሪያ ግብዓት እጥረትና የዋጋ ንረት ምክንያት የአካባቢው....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85588
ጊዜና ወቅት ያልገደበው የበጎ አገልግሎት
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ድህነት ጥላውን ላጠላባቸው ነፍሶች ቤት ከመጠለያም በላይ ነው። ቤት ገመናን ሸፋኝ፣ የዘመናት እንባን አባሽ፣ ሀዘንን መርሻ፣ ዞሮ መግቢያ ነው። የክረምቱን መግባት ተከትሎ በበጎ ፈቃድ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የአረጋውያንን እና የአቅመ ደካሞችን ቤቶች ማደስ አንዱ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድሃኒት፣ የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንም በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የብዙዎችን ቤት ጎብኝቷል።ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው ዝቅ ብሎ እጃቸው ላጠረባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤታቸውን አድሶ ለባለቤቶቹ አስተላልፏል።
ወይዘሮ አብነት ቢሻው ይባላሉ፤ የመኖሪያ ጎጇቸውን በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ቀልሰዋል። ቤታቸው ወደ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=85575
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽንን ለማቋቋም በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በተደራጀ ኃይል ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ፣ በአገሪቱ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲሳተፉ ለማስቻል ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
2. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው በመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የአገርን ሉአላዊነትና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ተልዕኮውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲወጣ የሚያስችል የሪፎርም ስራ ውስጥ እንደሚገኝ፣ በዚህም አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህንን ሪፎርም የበለጠ ለማጎልበት እና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ከመከላከያ ሠራዊቱ ወቅታዊ እና የወደፊት ግዳጆች ጋር የሚጣጣም የህግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ በሥራ ላይ ያለውን አዋጅ የሚተካ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
3. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲፋጠን ችግር ፈቺ የአቅም ግንባታ፣ የፋይናንስ፣ የማምረቻ መሳሪያ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምክር አገልግሎት፣ የማምረቻ ቦታና መሰረተ-ልማት፣ የግብዓትና የገበያ ትስስር ድጋፎች በመስጠት ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን የማስፋፋትና የማሸጋገር ተልዕኮ ያለው ተቋም በማስፈለጉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡