ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የታሸገ ውሃ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ውጭ ሊልኩ ነው
*******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ካሉ የታሸገ ውሃ አምራች ፋብሪካዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የታሸገ ውሃ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ውጭ ሊልኩ ዝግጅት ማድረጋቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር የተገነባውና የታሸገ ውሃ ወደ ውጭ ለመላክ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ስፖርት ውሃ ፋብሪካ ተመርቋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ፋብሪካውን ትናንት መርቀው ሲከፍቱ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች 110 የታሸገ ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ፈቃድ አውጥተው እየሰሩ ይገኛል ።
አጠቃላይ በአገሪቷ ካሉት የታሸገ ውሃ አምራች ፋብሪካዎች መካከል ወደ ምርት ከገባው ስፖርት ውሃ በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ፋብሪካዎች የታሸገ ውሃ ለውጭ ገበያ ለማቅረብና የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት የሚያስችል ዝግጅት አድርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የውሃ ፋብሪካዎች በዓመት ዘጠኝ ነጥብ 75 ቢሊዮን ሊትር የታሸገ ውሃ እየተመረተ ይገኛል። ምርቱ ግን ካለው የሕዝብ ብዛት አንፃር አነስተኛ የሚባል ደረጃ ላይ ነው ብለዋል።
አገራችን ከራሷ አልፋ ለውጭ ገበያ በተለይም ለአረቡ ዓለምና ለጎረቤት አገራት የሚተርፍ የውሃ ሀብት አላት ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የሚረዱ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉና ከአገር ውስጥ ባለፈ ለውጭው ዓለም እንዲያቀርቡ አስፈላጊው ጥረት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86131

“የመንግሥት ተቋማትን ወደ ግል ማዞሩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው”
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ
******
(ኢ ፕ ድ)
የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ ሆነ በከፊል ወደግል ማዞር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ገለጹ።
ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የመንግሥት ይዞታዎችን ወደግል ማዞር እራሱን የቻለ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ አለው። የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል፤ ተወዳዳሪ ተቋም መገንባትም ያስችላል፡፡
መንግሥት የግሉ ዘርፍ ሊሰራበት የሚችልበትን ዕድል እያስፋፋ መሄድ ይኖርበታል ያሉት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክሩ ውሳኔዎችን በቴሌኮምና በፋይናንስ ጉዳዮች ላይ እያከናወነ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
መንግሥት በግሉ ዘርፍ ሊሸፈኑ በሚችሉ የስራ መስኮች ሁሉ መሰማራት የለበትም ያሉት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ ይልቁንስ መንግሥት የግሉ ዘርፍ ሊሰማራባቸው ባይችልባቸው መስኮች በመሰማራት ውጤታማ ተግባር መስራት ይቻላል ብለዋል፡፡
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ መንግሥት ድርጅቶችን እዚህም እዚያም ለብቻው ሲይዝ ለዘረፋ የመጋለጥ ዕድል ይሰፋል። በማሳያነትም በተወካዮች ምክር ቤት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86134

170 ሺ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ፕሮጀክቶችስራ ጀመሩ
******
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር 170 ሺ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደረጉ የንፁህ መጠጥ ውሃና የንጽህና አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች ስራ መጀመራቸውን ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አስታወቀ።
በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የወሽ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ወንደሰን አድማሱ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፕሮጀክቶቹ የተከናወኑት በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጣዬና ሸዋሮቢት ከተማ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች ውስጥ ነው::
ከአጣዬና ሸዋሮቢት በተጨማሪ በደብረብረሃን ከተማ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችም የንፁህ መጠጥ ውሃና የንፅህና አገልግሎት መስጫ ተቋማትም መገንባታቸውን ማናጀሩ ጠቁመዋል:: በዚህም 170 ሺ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በእነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል::
ፕሮጀክቶቹን አጠናቆ ለማስረከብ ስድስት ወር እንደፈጀ የተናገሩት ማናጀሩ፤ ለግንባታቸውም 70 ሚሊዮን ብር ወጪ መሆኑንና የፕሮጀክቱ ግንባታ ከዩኒሴፍ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደተከናወነም ገልጸዋል።
ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ አስራ ስድስት የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎችን በማህበረሰቡ ውስጥ የማስፋፋት ስራዎችና የመፀዳጃ ቤቶችን በተፈናቃይ መጠለያ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86138

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ለኢትዮጵያ ያመጣል
***
(ኢ ፕ ድ)
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን ለኢትዮጵያ እንደሚያመጣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ገለጸ።
በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ጽህፈት ቤት የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ኃላፊው አቶ ተስመገን ይሁኔ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ ተግባራዊ ያደረገችው ነፃ የንግድ ቀጣና ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን የሚያመጣ ነው። ነፃ ንግድ ቀጣና መኖሩም የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የውጭ ንግድን በማነቃቃት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው እድሎችን ይፈጥራል።
በርካታ የዓለም አገራት ነፃ የንግድ ቀጣና አቋቁመው ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ እንደ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሱማሌ ላንድ ያሉ ጎረቤት አገራት የኢትዮጵያን ገበያ ታሳቢ ያደረገ ነፃ ንግድ ቀጣና እንዳላቸው ተናግረዋል።
በነፃ ንግድ ቀጣናው የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የበለጠ ለማሳደግ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ ፖሊሲውም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል ብለዋል።
የነፃ ንግድ ቀጣና ፖሊሲውም የአሰራር ሥርዓቱን በተሻለ መልኩ በማሳደግ አገልግሎቱን የተሳለጠ እንዲሆን ለማድረግ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ፖሊሲውም በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየት የሚፈቱበትን፣ ኃላፊነትን በሚገባ ለመወጣት እና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር በግልጽ እንዳስቀመጠ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86141

የማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን አባልና የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ይናገራሉ‼️
👉 መንግሥት የኢኮኖሚ ዕድገቱን እንዳይቋረጥ አስፈላጊውን ጥረት አድርጓል፤
👉 ጦርነት እየተደረገ የህዳሴ ግድብ ሲሞላ ነበር።
👉 መንግሥት 500 ዓይነት የግብርና ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በማድረግና አገራዊ አቅማችን እንዲጎለብት ሰርቷል፤
👉 ግብርናና አገልግሎት ዘርፍን ማሳደግ ብቻ ሳይሆን በኑሮ ውድነቱ ሕብረተሰቡ እንዳይጎዳ ጥረት አድርጓል፤
👉 መንግሥት የዋጋ ግሽበቱ ሕብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ባጣ ይሻላል በሚል ውሳኔ የሸቀጣሸቀጥ ዋጋው ከዚህም በላይ እንዳይንር ሰፊ ጥረት አድርጓል፤
👉 ከዚህ ባለፈ በዝቅተኛ ገቢ ላይ ላለው ሕብረተሰብ የምገባ ማዕከላትን በማዘጋጀት፣ በበጎ ፈቃድ ቤት ዕድሳት በማከናወንና በተለያዩ ድጋፎች የኢኮኖሚው ዕድገት ተቋዳሽ እንዲሆን እየተደረገ ነው፤
👉 በዕውቀት ላይ በተመሰረተ የማክሮ ኢኮኖሚ እርምጃዎች የኢኮኖሚው መሰረት የሆነውን ግብርና ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ፣ የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ውጤታማ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ያሳዩት ውጤታማነት በየደረጃው ላለ አመራር ትምህርት ሆኗል፤
👉 በአጠቃላይም በዘርፉ ብዙ ጉዳዮች ላይ በተለይም አገራዊ አቅምን በማሳደግ በተከናወነው ሥራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት ከናይጀሪያና ደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሶስተኛው ትልቅ ኢኮኖሚ መሆን ችሏል፤
👉 ይህን ዕድገት ደግሞ የአገራችንን ሰፊ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ሃይል እንዲሁም ዕውቀት በመጠቀም በቀጣይ ጊዜያትን ማስቀጠል ይኖርብናል፤
ሙሉውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ
https://youtu.be/RRUFwSUMDaU

YouTube
የኢፕድ ቆይታ ከማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን አባላት ጋር
በሠላም ስምምነቱ ላይ ለተሳተፈው ቡድን የምሥጋና ፕሮግራም ተካሄደ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የመከላከያ ሚኒስቴር በደቡብ አፍሪካ እና በኬንያ የተደረገውን የሠላም ስምምነት በስኬት አጠናቀው ለተመለሱ የልዑካን ቡድን አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ-ግብር አድርጎላቸዋል።
በመከላከያ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው መርሃ ግብር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖች፣ ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያን አንድነትና ጥቅም ባስጠበቀ መንገድ የሠላም ንግግሩን አሳክቶ መመለሱን የገለፁት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ስምምነቱ ግቡን እንዲመታ አበክረው አንደሚሠሩም ተናግረዋል።
በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እንዳይሰፍን የጦርነት ነጋሪት የሚጎስሙ ፅንፈኛ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገልፀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በበኩላቸው በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም ለማምጣት ሲባል የልዑካን ቡድኑ አባላት ብስለት በተሞላበት መንገድ ስምምነት እንዲካሄድ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ሥር በደቡብ አፍሪካ እና በኬንያ የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱም ወገኖች በትኩረት እየተሠራ መሆኑም በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘግቧል።