የሕክምና ቁሳቁሶች ሽሬ መድረሳቸውን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገለፀ
****
(ኢ.ፕ.ድ)
ለትግራይ ክልል በአየር እና በየብስ ትራንሥፓርት የተጓጓዙ
አስቸኳይ የህክምና ቁሳቁሶች ሽሬ መድረሳቸውን ዓለም አቀፉ የቀይ መሥቀል ኮሚቴ ዛሬ አስታውቋል።
ሽሬ የገብልው አስቸኳይ የሕክምና ቁሳቁስም 20 ቶን መሆኑን ገልጿል።
አስቸኳይ የሕክምና ቁሳቁሱ በክልሉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ዜጎች የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚውሉ ኮሚቴው በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።

አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የአሜሪካ ኮንግረስ አባሉ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ እንድትመለስ ላቀረቡት ጥያቄ ምስጋና አቀረቡ
****
(ኢ ፕ ድ)
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለአሜሪካ የኮንግረስ አባል ዶን ቤየር ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለአገራቸው መንግስት ላቀረቡት ጥያቄ ምስጋና አቀረቡ።
የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆኑት ዶን ቤየር ለአሜሪካ የንግድ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይ ባጸፉት ደብዳቤ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለአገራቸው መንግስት ጥያቄ አቅርበዋል።
ዶን ቤየር በዚሁ ደብዳቤያቸው የኢትዮጵያ መንግስት ከሕወሓት ጋር የተፈራረመውን ስምምነት ተፈጻሚ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ሴናተሩ በደብዳቤያቸው በስምምነቱ መሠረት መንግስት ሰብአዊ እርዳታን ባልተገደበ መልኩ ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ የመመለስን ጉዳይ በድጋሜ ሊመለከተው ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚ በነበረችበት ወቅት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ እድገት እንዲያሳይ፣ በ10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረና የሁለቱን አገራት የንግድ አጋርነት ለማሳደግ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ተጠቃሚነቷን ስታጣ በአጎዋ ጥላ ስር ምርታቸውን ወደ አሜሪካ ይልኩ የነበሩ ኩባንያዎች የማስፋፋፊያ እቅዳቸውን መተዋቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን መቀነሳቸውን ነው የኮንግረስ አባሉ ለአምባሳደር ካትሪን በጻፉት ደብዳቤ የገለጹት።
ኢትዮጵያን ከአጎዋ የማስወጣት ውሳኔ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ መቀዛቀዝ እንዲታይ ማድረጉንም አመልክተዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነት በድጋሚ መመለስ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት እንዲያደርግ ዶን ቤየር ለአምባሳደር ካትሪን ጥሪ አቅርበዋል።
በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር የተፈረመው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ኢትዮጵያን በፍጥነት ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት ይመልሳታል ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
ይህንን ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ተጠቃሚነት እንድትመለስ ለአገራቸው መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ አሰመልክቶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ሴናተሩን አመስግነዋል።

የ12 አመቱን የኳታር ታላቅ አለም አቀፍ ድግስ በጨረፍታ‼️
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
ሊጀመር ሰአታት የቀሩት 22ኛው የአለም ዋንጫ ብዙ ተብሎለታል። ብዙ ቁም ነገሮች በርካታ ቀልዶችም በዚሁ የእግር ኳስ ድግስ ዙሪያ ተሰምተዋል ተነበዋልም።
ኳታር በቆዳ ስፋት ትንሿ የአለማችን አገር በመሆኗ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ብዙዎችን ፈገግ ያስባለች አንድ ቧልት እንዲህ ትላለች...
"በጨዋታ ወቅት ተጫዋቾች የማእዘን ምት (ኮርና) ለመምታት ሲንደረደሩ ባህሬን ደርሰው ይመለሳሉ"
ቀልዷ ለቀጣይ 28ቀናት የአለም ዋንጫ ተከታታይ ዘገባችን ቅምሻ ትሁነንና ትንሻ አገር ስላሰናዳችው ታላቅ አለም አቀፍ ድግስ አንዳንድ እውነታዎች ከብዙ በጥቂቱ እናካፍላችሁ።
ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ኳታርን ለዓለም ዋንጫ አዘጋጅነት የመረጣት ከ12 ዓመታት በፊት ነበር። ይህን ውሳኔ መላው ዓለም በፀጋ አልተቀበለውም። በተለያዩ መንገዶች የኳታርን መስተንግዶ የሚያጣጥሉና የሚያወግዙ ትችቶች ሲሰራጩ ቆይተዋል።
የመጀመርያው ንትርከ የፊፋ አስተዳደርና አባል አገራቱ አዘጋጅነቱን ለኳታር ለመስጠት ሲወስኑ በሙስና ተደልለዋል የሚለው ነው።
ኳታር ለአዘጋጅነት በተካሄደው ምርጫ የድጋፍ ድምፆችን ለማግኘት መደለያ ክፍያዎች እንደነበሩ ያወሱ ዘገባዎች ነበሩ። ሁሉም አሉባልታዎች በትክክለኛ መረጃዎች ዛሬም ድረስ አልተረጋገጡም እንጂ ።
የኳታር ንጉሳዊ መንግስት ለአዘጋጅነት በተካሄደው ምርጫ የድጋፍ ድምፆችን ለማግኘት እስከ 6 ሚሊዮን ዶላር በተለይ ለአፍሪካ አገራት ፌደሬሽኖች ማከፋፈሉን ያወሱ ዘገባዎች ነበሩ። ይሁንና ሁሉም አሉባልታዎች በትክክለኛ መረጃዎች ዛሬም ድረስ አልተረጋገጡም።
አንዳንድ የኤስያ አገራትና በተለይ ደግሞ አሜሪካ የዓለም ዋንጫውን ለማዘጋጀት ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበራቸው መሰል ዘገባዎች ተሰራጭተዋል። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር በ2010 እኤአ ላይ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያካሂድ በ2018 እኤአ ላይ ራሽያ 21ኛውን የዓለም ዋንጫ እንድታስተናግድ ከመረጠ በኋላ በ2022 እኤአ ላይ ደግሞ ኳታር 22ኛውን ዓለም ዋንጫ እንድታዘጋጅ ወስኗል።
በተለይ ለ22ኛው የዓለም ዋንጫ አሜሪካ፤ አውስትራሊያ፤ ጃፓንና ደቡብ ኮርያ ለመስተንግዶው ፉክክር አድርገው አልተሳካላቸውም።
ፊፋና የዓለም ዋንጫው አዘጋጅ ኳታር በውድድሩ ታሪክ ዘላቂ የስፖርት ልማቶች በመገንባት፤ ከካርቦን ልቀት የነፃ መስተንግዶ በማካሄድ፤ በዘመናዊ ዝግጅት የተሟላ እንደሚሆን እምነት ማሳደራቸው የሙስናውን ወሬ አደብዝዞታል።
በሌላ በኩል የዓለም ዋንጫው የሚካሄድበት ወቅት ከተለመደው መርሃ ግብር እንዲቀየር መደረጉንም ያማረሩ አልጠፉም። ኳታር በሙቀታማ አየር ንብረቷ ሳቢያ ዓለም ዋንጫው የፈረንጆች አዲስ አመት ዋዜማ ባለው ወር እንዲካሄድ አድርጋለች።
በመደበኛው የዓለም ዋንጫ ወቅት የአየሩ ሙቀት ከ50 ዲግሪ ሴንትግሬድ በላይ ይሆናል። አዲስ በታቀደው የዓለም ዋንጫ ወር ግን የኳታር አየር ንብረት እስከ 29 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መውረዱ ውሳኔውን አፅንቶታል።
ኳታር የዓለም ዋንጫን የሚያስተናግዱ ስምንት ስታድዬሞች ከሙቀቱ ጋር ለማመጣጠን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመስራት ከአየቅጣጫው የመጡትን ትችቶች አብርዳለች።
የኳታር ዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰፋ ያለ ጥናትና ምርምር ካደረገ በኋላ በተጨዋቾች፤ በደጋፊዎች እና በአጠቃላይ በስታድዬም ውስጥ ቀዝቃዛ አየር የሚያነፍስ ዘመናዊ የማቀዝቀዣ ቴክኖሎጂ በመፍጠር ተግባራዊነቱን አረጋግጧል።
አስደናቂዎቹ የዓለም ዋንጫ ስምንት ስታድዬሞች በዚህ ረገድ ስኬታማ ውድድር ለማስተናገድ እስከ 7 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ሆኖባቸዋል።
ኳታር ለዝግጅቱ ያወጣችው ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ
ሲሆን፤ ለዓለም ዋንጫ እስካሁን ያልወጣም ብቻ ሳይሆን ወደፊትም በቅርብ አመታት ውስጥ ሊወጣ የማይችል ገንዝብ ነው።
ቦጋለ አበበ

ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የታሸገ ውሃ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ውጭ ሊልኩ ነው
*******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ካሉ የታሸገ ውሃ አምራች ፋብሪካዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የታሸገ ውሃ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ውጭ ሊልኩ ዝግጅት ማድረጋቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር የተገነባውና የታሸገ ውሃ ወደ ውጭ ለመላክ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ስፖርት ውሃ ፋብሪካ ተመርቋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ፋብሪካውን ትናንት መርቀው ሲከፍቱ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች 110 የታሸገ ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ፈቃድ አውጥተው እየሰሩ ይገኛል ።
አጠቃላይ በአገሪቷ ካሉት የታሸገ ውሃ አምራች ፋብሪካዎች መካከል ወደ ምርት ከገባው ስፖርት ውሃ በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ፋብሪካዎች የታሸገ ውሃ ለውጭ ገበያ ለማቅረብና የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት የሚያስችል ዝግጅት አድርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የውሃ ፋብሪካዎች በዓመት ዘጠኝ ነጥብ 75 ቢሊዮን ሊትር የታሸገ ውሃ እየተመረተ ይገኛል። ምርቱ ግን ካለው የሕዝብ ብዛት አንፃር አነስተኛ የሚባል ደረጃ ላይ ነው ብለዋል።
አገራችን ከራሷ አልፋ ለውጭ ገበያ በተለይም ለአረቡ ዓለምና ለጎረቤት አገራት የሚተርፍ የውሃ ሀብት አላት ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የሚረዱ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉና ከአገር ውስጥ ባለፈ ለውጭው ዓለም እንዲያቀርቡ አስፈላጊው ጥረት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86131

“የመንግሥት ተቋማትን ወደ ግል ማዞሩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው”
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ
******
(ኢ ፕ ድ)
የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ ለሙሉ ሆነ በከፊል ወደግል ማዞር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ገለጹ።
ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የመንግሥት ይዞታዎችን ወደግል ማዞር እራሱን የቻለ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ አለው። የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል፤ ተወዳዳሪ ተቋም መገንባትም ያስችላል፡፡
መንግሥት የግሉ ዘርፍ ሊሰራበት የሚችልበትን ዕድል እያስፋፋ መሄድ ይኖርበታል ያሉት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክሩ ውሳኔዎችን በቴሌኮምና በፋይናንስ ጉዳዮች ላይ እያከናወነ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል።
መንግሥት በግሉ ዘርፍ ሊሸፈኑ በሚችሉ የስራ መስኮች ሁሉ መሰማራት የለበትም ያሉት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ ይልቁንስ መንግሥት የግሉ ዘርፍ ሊሰማራባቸው ባይችልባቸው መስኮች በመሰማራት ውጤታማ ተግባር መስራት ይቻላል ብለዋል፡፡
እንደ ባለሙያው ገለጻ፤ መንግሥት ድርጅቶችን እዚህም እዚያም ለብቻው ሲይዝ ለዘረፋ የመጋለጥ ዕድል ይሰፋል። በማሳያነትም በተወካዮች ምክር ቤት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86134

170 ሺ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውሃ ፕሮጀክቶችስራ ጀመሩ
******
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር 170 ሺ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደረጉ የንፁህ መጠጥ ውሃና የንጽህና አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክቶች ስራ መጀመራቸውን ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አስታወቀ።
በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የወሽ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ወንደሰን አድማሱ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፕሮጀክቶቹ የተከናወኑት በሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አጣዬና ሸዋሮቢት ከተማ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች ውስጥ ነው::
ከአጣዬና ሸዋሮቢት በተጨማሪ በደብረብረሃን ከተማ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችም የንፁህ መጠጥ ውሃና የንፅህና አገልግሎት መስጫ ተቋማትም መገንባታቸውን ማናጀሩ ጠቁመዋል:: በዚህም 170 ሺ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በእነዚህ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል::
ፕሮጀክቶቹን አጠናቆ ለማስረከብ ስድስት ወር እንደፈጀ የተናገሩት ማናጀሩ፤ ለግንባታቸውም 70 ሚሊዮን ብር ወጪ መሆኑንና የፕሮጀክቱ ግንባታ ከዩኒሴፍ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደተከናወነም ገልጸዋል።
ከፕሮጀክቶቹ ውስጥ አስራ ስድስት የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎችን በማህበረሰቡ ውስጥ የማስፋፋት ስራዎችና የመፀዳጃ ቤቶችን በተፈናቃይ መጠለያ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86138

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ለኢትዮጵያ ያመጣል
***
(ኢ ፕ ድ)
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን ለኢትዮጵያ እንደሚያመጣ የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ገለጸ።
በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ጽህፈት ቤት የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ኃላፊው አቶ ተስመገን ይሁኔ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ ተግባራዊ ያደረገችው ነፃ የንግድ ቀጣና ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን የሚያመጣ ነው። ነፃ ንግድ ቀጣና መኖሩም የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የውጭ ንግድን በማነቃቃት እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው እድሎችን ይፈጥራል።
በርካታ የዓለም አገራት ነፃ የንግድ ቀጣና አቋቁመው ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ እንደ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ሱማሌ ላንድ ያሉ ጎረቤት አገራት የኢትዮጵያን ገበያ ታሳቢ ያደረገ ነፃ ንግድ ቀጣና እንዳላቸው ተናግረዋል።
በነፃ ንግድ ቀጣናው የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የበለጠ ለማሳደግ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን ጠቁመው፤ ፖሊሲውም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል ብለዋል።
የነፃ ንግድ ቀጣና ፖሊሲውም የአሰራር ሥርዓቱን በተሻለ መልኩ በማሳደግ አገልግሎቱን የተሳለጠ እንዲሆን ለማድረግ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ፖሊሲውም በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየት የሚፈቱበትን፣ ኃላፊነትን በሚገባ ለመወጣት እና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር በግልጽ እንዳስቀመጠ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=86141

የማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን አባልና የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ይናገራሉ‼️
👉 መንግሥት የኢኮኖሚ ዕድገቱን እንዳይቋረጥ አስፈላጊውን ጥረት አድርጓል፤
👉 ጦርነት እየተደረገ የህዳሴ ግድብ ሲሞላ ነበር።
👉 መንግሥት 500 ዓይነት የግብርና ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በማድረግና አገራዊ አቅማችን እንዲጎለብት ሰርቷል፤
👉 ግብርናና አገልግሎት ዘርፍን ማሳደግ ብቻ ሳይሆን በኑሮ ውድነቱ ሕብረተሰቡ እንዳይጎዳ ጥረት አድርጓል፤
👉 መንግሥት የዋጋ ግሽበቱ ሕብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ባጣ ይሻላል በሚል ውሳኔ የሸቀጣሸቀጥ ዋጋው ከዚህም በላይ እንዳይንር ሰፊ ጥረት አድርጓል፤
👉 ከዚህ ባለፈ በዝቅተኛ ገቢ ላይ ላለው ሕብረተሰብ የምገባ ማዕከላትን በማዘጋጀት፣ በበጎ ፈቃድ ቤት ዕድሳት በማከናወንና በተለያዩ ድጋፎች የኢኮኖሚው ዕድገት ተቋዳሽ እንዲሆን እየተደረገ ነው፤
👉 በዕውቀት ላይ በተመሰረተ የማክሮ ኢኮኖሚ እርምጃዎች የኢኮኖሚው መሰረት የሆነውን ግብርና ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ፣ የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ውጤታማ በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ያሳዩት ውጤታማነት በየደረጃው ላለ አመራር ትምህርት ሆኗል፤
👉 በአጠቃላይም በዘርፉ ብዙ ጉዳዮች ላይ በተለይም አገራዊ አቅምን በማሳደግ በተከናወነው ሥራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት ከናይጀሪያና ደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሶስተኛው ትልቅ ኢኮኖሚ መሆን ችሏል፤
👉 ይህን ዕድገት ደግሞ የአገራችንን ሰፊ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ሃይል እንዲሁም ዕውቀት በመጠቀም በቀጣይ ጊዜያትን ማስቀጠል ይኖርብናል፤
ሙሉውን ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ
https://youtu.be/RRUFwSUMDaU

YouTube
የኢፕድ ቆይታ ከማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን አባላት ጋር