Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል።
የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት ተፈፅሟል።
ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ በአለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።
ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ አይዘነጋም።
በዳግማዊት ግርማየድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የድምጻዊት ሂሩት በቀለ የቀብር ስነስርአት ዛሬ ተፈጽሟል።
የድምጻዊቷ የቀብር ስነስርዓት ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የጥበብ አፍቃሪያን በተገኙበት ተፈፅሟል።
ድምፃዊቷ ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ በአለማዊ ሙዚቃና በመንፈሳዊ መዝሙሮች አገሯንና ህዝቧን ማገልገሏ በህይወት ታሪኳ ላይ ተገልጿል።
ድምጻዊቷ የሰባት ልጆች እናት የአስር ልጆች አያትና የሰባት ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
ድምፃዊቷ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ባሳለፍነው ግንቦት አራት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ አይዘነጋም።
በዳግማዊት ግርማ
#ከኢፕድ_ማህደር‼️
አዲሱን የለቅሶ ዜማ የመንደር አልቃሾች ተቃወሙ
የቤተሰብን ጤንነትና አካል እንዲጠብቅ ተብሎ በፀሎት መልክ የቀረበውን አዲሱን የሀዘን ዜማ አንዳንድ የመንደር አልቃሾች መቃወማቸውን አቶ አብረሃም መኮንን በኢትዮጵያ መንበረ ፓትሪያርክ የወጣቶች አንድነት ማዕከላዊ ፅ/ቤት ዋና ፀሐፊ አስረዱ፡፡
አዲሱን የለቅሶ ዜማ የመንደር አልቃሾች ኮርስ ወስደው እዲያጠኑ ተጠይቀው ፍቃደኞች አለመሆናቸውን ዜና ሰጪው ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ዜማ አንድ ሰው ሲሞት በህብረት ዝማሬ እየተዜመ ሙታንን ለመሸኘት የሚያስችል ነው፡፡
በተለይ አንድ ሰው በሞተ ጊዜ የሟች ቤተሰቦች ደረት በመደለቅ፣ ከመሬት በመፈጥፈጥ፣ ፊትበመንጨት የሚደርስባቸውን ከባድ ጉዳት የሚያስወግድና ስርአትና መልክ ያለው መሆኑን አቶ አብረሃም ገልጠዋል፡፡
በዚህ መሰረት ሰባት ዓይነት ልዩልዩ በህብረት የሚዜሙ የለቅሶ ዜማዎች ተዘጋጅተውና ተፈልስፈው ይገኛሉ፡፡
ዜማዎቹን የደረሱት አቶ አብረሃም ሲሆኑ እነዚህኑ ዜማዎች በኮርስ መልክ የመንደር አልቃሾች እንዲያጠኑ 8 ያህል አልቃሾች ማነጋጋራቸውን ዜና ሰጪው ተናግረዋል፡፡
ከስምንቱ አልቃሾች ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ ጥቂቶቹ አልቃሾች ዜማውን ለማጥናት ኮርስ ከገባን ዜናውን እስክናጠናክው ድረስ በወር 25 ብር ክፈሉን በማለት አቶ አብረሃምን የጠየቁ መሆናቸውን ዜና ሰጪው አስረዱ፡፡
ቀጥለውም ‹‹ካነጋገርኳቸው ጥቂቶቹ የመንደር አልቃሾች ዘንድ ብዙ ወቀሳ ደርሶብኛል፡፡ ብላችሁ ብላችሁ በእንጀራችን ገባችሁ አሉኝ፡፡ ቄሶች በአንድ በኩል ያወግዛሉ፡፡ እኛ ስራችን ነው በማለት ተቃውሟቸውን ገለጡ፡፡ ኮርስ ግቡና በወር 5 ብር ልክፈላችሁ አልኳቸው 25 ብር ካልሆነ ብለው ሀሳቤን ሳይቀበሉ ቀሩ›› ሲሉ አቶ አብረሃም ተናግረዋል፡፡
አዲሱ የልቅሶ ዜማ ሙታንን እንዴት መሸኘት እንደሚገባ ትምህርትና ምክር የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም ዜማ ካሁን በፊት በደብረ ገሊላ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ዜማውን ባጠኑ ተማሪዎች በቴያትር መልክ ተዘምሮ ታይቷል፡፡ በሁለቱም ቀኖች የተገኘው ህዝብ በብዛት የሚቆጠር መሆኑንና በተመለከተው ህዝብ መደገፉን አቶ አብረሃም ተናግረዋል፡፡ አሁን የመንደር አልቃሾች ዜማ ግን ሥርዓት የሌለው ነው ሲሉ ነቅፈዋል፡፡
አቶ አብረሃም የመጨረሻ ማብራሪያቸውን ሲሰጡ ‹‹ያሁኑ የአልቃሾች ዜማ ወንዱና ሴቱ ተለይቶ አይነገርበትም፡፡ የሞተችው ሴት የሆነች እንደሆነ ለወንድ ያለቅሱበታል፤ ሟች አርበኛ የሆነ እንደሆነም አቶ እገሌ እህል ሲያመርት፤ እርፍ ሲይዝ እንዲህ አልነበረም ተብሎ ሙሾ ይቆምበታል፡፡ በጠቅላላ ዜማው ሥርዓት የሌለው ነው፡፡ ነገር ግን በህብረት እየተዘመረ የሚዜመውን አዲሱን የለቅሶ ዜማ በአልቃሾች ቢጠና ጥቅሙ እንደሚያመዝን አንጠራጠርም›› ብለዋል፡፡
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መስከረም 7 ቀን 1963 ዓ.ም የታተመ
በኃይማኖት ከበደ
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
በ2014 እና በ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት በበጎ ፈቃድ ስራዎች ከጎናችን ለተሰለፉ በጎ ፍቃደኞች እውቅና ሰጥተናል። በነዋሪው ስም ስለበጎነታቸውም አመስግነናቸዋል።
በበጎ ፍቃድ ስራዎቻችን የበርካቶችን እንባ አብሰናል፤ የኑሮ ጫናዎቻቸውን አቅልለን የጨለመ በመሰለው ኑሯቸው የተስፋ ጮራ ፈንጥቀናል።
ለሀገር ባለውለታዎችና አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ከከተማቸን ዕድገት ፍትሀዊ ተጠቃሚ በማድረግ ማህበራዊ ፍትህ የማንገስ ታላቅ ስራ ሰርተናል። በዚህ ታላቅ የበጎነት ተግባር በቀናነት ለተባበራችሁንና ላስተባበራችሁ እንዲሁም በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
ለከተማችን ታላቅነት የላቀ አስተዋጽዖ ያላቸውን ታላላቅ ፕሮጀክቶች በገባነው ቃል መሠረት በጥራትና በጊዜ እየገነባን የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ሸክም የሚያቀልሉ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሠራን ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማን መገንባታችንን እንቀጥላለን።
ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የግንባታ ሒደትን ተመለከቱ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በዛሬ እለት የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ቀሪ የግንባታ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
በመረሃ ግብሩ ላይ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የማሕበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳን ጨምሮ ሌሎች የክልል አፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዝቅተኛውን የፊፋ መስፈርት ማሟላት የሚያስችለውን የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃ ከፋለ የግንባታ ሒደቱ አበረታች ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ቀሪ ስራዎችን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ የሰው ኃይልና አስፈላጊ ግብአት ማሟላት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ርእሰ መስተዳድሩ አክለውም የስታዲየሙ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ተፈላጊውን አገልግሎት እንዲሰጥ የምናደርገውን ክትትል አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከክልሉ የብልጽግና ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በጅማ እና አዳማ ከተሞች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የኮሚሽኑ አባላት የሀገራዊ ምክክር ፅንሰ ሀሳብን ያብራሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ሀጋራዊ ምክክርን ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎችን አቅርበዋል ፡፡
ከቀረቡት የዝግጅት ስራዎች ውስጥ ተሳታፊዎችን ለመለየት የተደረጉ ዝግጅቶች ዋናውን ቦታ የሚይዙ ሲሆን በቀጣይ ሊሰሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ ውይይትና ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡
በውይይቱም ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን የኮሚሽኑ አባላት ለተነሱት ጥያቄዎች መልሶችንና ማብራርያዎችን መስጠታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለተለያዩ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለተለያዩ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሠረት፦

❶ አቶ አሰፋ ጥላሁን በየነ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣
❷ አቶ በቀለ ወርቁ መንገሻ የሰሜን ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ፣

❸ አቶ ዳኛቸው ፈንታሁን ቁምላቸው የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳድር የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዋና አማካሪ፣
❹ አቶ በለጠ ጥጋቡ ዘውዴ የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳድር ህዝብ ግንኙነት አማካሪ፣
❺ ወይዘሮ ሐብታም አውደው ገበያው የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳድር የአደረጃጀት አማካሪ፣

❻ አቶ ኑረዲን ሰይድ ኡመር የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳድር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣

❼ አቶ አንተነህ ታደሰ ከበደ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳድር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥተዋል።
“የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ የሚመራና የሚተዳደር ማድረግ ተችሏል”
- ሙፈሪሃት ካሚል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በበጀት አመቱ ቴክኖሎጂ መር የሆኑ ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ የሚመራና የሚተዳደር ማድረግ መቻሉን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99583
ዩኒቨርሲቲው በ60 ሚሊዮን ብር በጀት ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ይገኛል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶች በማከናወን ላይ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች የማህበረሰቡን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉፕሮጀክቶች ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99608
በትግራይ ክልል እየተካሄደ ላለው የመልሶ ግንባታ ስራ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ
******************
(ኢ ፕ ድ )
በሰሜኑ ጦርነት በትግራይ ክልል የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99602
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል አገራዊ ንቅናቄ ሊካሄድ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልን ዓላማ ያደረገ አገራዊ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
አገር አቀፍ የትምህርት ምዘና ውጤትና የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትና የጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ትናንት በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99587