Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝን ዛሬ አግኝቻቸዋለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋት አብረን እንሠራለን።
የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 13 2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሰታወቀ።
የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱም ተገልጿል ።
በ2014 ዓ.ም የህግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

በተቋማዊ አሠራር ላይ ያለውን ሂደት ለመገምገም ባለን ቁርጠኝነት ዛሬ የሚኒስትሮችን የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ግምገማ ጀምረናል። የግምገማ ሂደቱም በአጠቃላይ የዘጠኝ ወር የማክሮ ኢኮኖሚውን እና የሴክተሮች ልዩ አፈጻጸምንም ይዳስሳል።
የአርባምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያነቃቃል
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በአርባ ምንጭ የሚገነባው የ«ገበታ ለትውልድ» ፕሮጀክት የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ በማነቃቃት የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግ በደቡብ ክልል የጋሞ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋ ከተደረጉ ስምንት የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች መካከል በአርባምንጭ የሚገነባው የቱሪዝም መዳረሻ አንዱ ነው።

በአርባ ምንጭና አካባቢው ያሉትን የአባያና ጫሞ ሐይቆች፣ ነጭሳር ብሔራዊ ፓርክ፣ የከተማዋ መጠሪያ የሆኑት 40ዎቹ ምንጮች እንዲሁም በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙት ተራሮችን ይበልጥ ለቱሪዝም ምቹ በማድረግ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።
https://www.press.et/?p=99782
ክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየሠራ ነው

👉 ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች ተመልሰው ተቋቁመዋል
********************
(ኢ ፕ ድ)

የአማራ ክልል ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስና በዘላቂነት ለማቋቋም እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤
በተያዘው በጀት ዓመት 939 ሺህ 657 ዜጎች በጦርነቱና በእርስ በርስ ግጭት ተፈናቅለው በክልሉ ሲረዱ እንደነበር የገለጹት አቶ ግዛቸው፤ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት ከ309 ሺህ 271 ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ተሠርቷል ብለዋል። https://www.press.et/?p=99840
በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር እስካሁን ከ25 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

"አረንጓዴ አሻራችን ለዘላቂ ልማታችን" በሚል መሪ ሀሳብ አረንጓዴ አሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።

መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ አንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በቂ መሬት፣ አመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞችና አምራች ሃይል እያላት ለምግብ እህል ግዢ ቢሊዮን ዶላሮችን ስታወጣ ቆይታለች። ይህን ሁኔታ ለመቀየር የአረንጋዴ ልማት ስትራቴጂ ተቀርጾ እየተተገበረ ይገኛል።

ከዚህ ጋር በተያያዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በተጀመረው አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከ2011እስከ 2014 ባሉት ዓመታት 20 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ በተከናወነው የአረንጋዴ አሻራ መርሃግብር ከ25 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል፤ አቶ አደም።

አረንጓዴ አሻራ የተሻለች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን ለማውረስ የምንሰራበት እሳቤ ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ በአረንጋዴ አሻራ የተገኘው ውጤት ከአባይ ግድብ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ታላላቅ ፕሮጀክቶን አቅዳ መፈጸም እንደምትችል ያረጋገጠችበት ነው ብለዋል።

የእስካሁኑ የአረንጋዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት መጠናቀቁን አመልክተው፤ ለዘንድሮው ዓመት በሚጀመረው ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርም እስካሁን የተገኙ ልምዶችን ቀምሮ አገርንና ሕዝብን በሚጠቅም መልኩ በላቀ መልኩ ለመተግበር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህ መርሃግብር ስኬትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት በተከናወነው አረንጋዴ አሻራ ኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።

ይህን መልካም ተሞክሮ ወደ ጎረቤት ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸውን እንዲሁም ኢትዮጵያ ልምድ እንድታካፍላቸው በይፋ ልምድ የጠየቁ አገራት መኖራቸውንም ገልጸዋል።

ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወነው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ900ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ተፈጥሯል ነው ያሉት።

ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ሰባት ቢሊዮን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ግብርና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል።

በፋንታነሽ ክንዴ