Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን ማዘጋጀት ትችላለች
*******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ግንባታ በ2016 ዓ.ም ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን ማዘጋጀት እንደምትችል ተገለጸ። በአሁኑ ጊዜም የማዕከሉ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ አፈጻጸም 76 በመቶ መድረሱን ተመልክቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99984
በስልጤ ዞን 15 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ነው
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሚገኘው የስልጤ ዞን ከ 15 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ፍራፍሬ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን ለኢትዮጵ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዞኑ የፍራፍሬ ምርትን በስፋት ለገበያ ለማቅረብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።በዚህም በአሁኑ ጊዜም ከ 15 ሺ በላይ ሄክታር መሬት በፍራፍሬ እየለማ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99977
አውደ ርዕዩ በግብርና ዘርፉ የመጣውን ተጨባጭ ውጤት ማሳያ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 30 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የግብርናና ሳይንስ ዐውደ ርዕይ በግብርና ዘርፍ የተገኘው ተጨባጭ ውጤት ማሳያ መሆኑን ተሳታፊዎችና ጎብኚዎች ተናገሩ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ስራ አስፈጻሚ ስር የጥራጥሬ ሰብሎችና ድህረ ምርት አያያዝ ዴስክ ኃላፊ አቶ ስብሀት ተመስገን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አውደ ርዕዩ መንግሥት በተለያዩ ሚዲያዎች የሚናገረውን የልማት ስራዎችን እንደማሳያ ማቅረቡ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠውና በተጨባጭም በዘርፉ ምን ምን ስራዎች እንደተሰሩ ግልጽ ማሳያ ነው፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ አካላት እርስ በእርስ የገበያ ትስስት በመፍጠር የተሻለ ምርታማነት እንዲኖር፣ የግል ባለሀብቶች ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100000
የኢፕድ የስራ ማስታወቂያዎች፤ መልካም ዕድል ‼️
የማህበረ ቅዱሳን ብሮድክስቲንግ አገልግሎት ቴሌቪዥን ፈቃድ በጊዜያዊነት መታገዱን ባለስልጣኑ አስታወቀ
*******
(ኢ.ፕ.ድ)

የማህበረ ቅዱሳን ብሮድክስቲንግ አገልግሎት ቴሌቪዥን ፈቃድ በጊዜያዊነት መታገዱን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ።

ባላስልጣኑ ዛሬ ለተቋሙ በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው፤ የቴሌቪዥን ጣቢያው ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ሰበር ዜና በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሚና ወጪ በሆነ አግባብ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያካሂደውን ስብሰባ የሚያውክና ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት ማሰራጩቱ ተረጋግጧል።

ይህም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን የሚተላለፍና በሀገር ሁለንተናዊ ሰላም ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ነው ብሏል ባለስልጣኑ።

"በመሆኑም ከጉዳዩ አጣዳፊነትና ሊያስከትለው ከሚችለው ጉዳት አንጻር በቀጣይ በባለስልጣኑ ቦርድ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ የጣቢያው ፈቃድ በጊዜያዊነት የታገደ መሆኑን እናሳውቃለን" ብሏል ባለስልጣኑ።
የቆዳ ዘርፍ ፈተናዎችና መልካም እድሎች
************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን የቀንድ ከብት፣ 53 ሚሊዮን ፍየሎችና 43 ሚሊዮን የበግ ሀብት እንዳላት እኤአ በ2021 ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱም በቀንድ ከብት ሀብት ብዛት ከአፍሪካ በቀዳሚነት ስትመራ፤ በዓለም አቀፍ 6ኛ ደረጃን ይዛለች።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=100040
ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ 284 ቦታዎች ተለይተው የመከላከል ስራ እየተከናወነ ይገኛል
************
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ 284 ቦታዎች በጥናት ተለይተው የቅድመ አደጋ መከላከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=100048
(ፎቶ ፋይል)
በግብርና ዘርፍ ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በግብርና ዘርፉ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ጥረት እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የግብርና ሳይንስ አውደርዕይን ጎብኝተዋል።
በወቅቱ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንለኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=100055
የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት አሰባሰብ በመጠናቀቅ ላይ ነው
*************
(ኢ ፕ ድ)
የዘንድሮ ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት አሰባሰብ እየተጠናቀቀ እንደሆነ የኢትዮጵያ ግብርና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ከ70 በመቶ በላይ የሆነው ምርት የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪው በተያዘው ወር ተሰብስቦ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጿል።
በኢትዮጵያ ግብርና ኢንስቲትዩት የመስኖ ስንዴ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=100051
(ፎቶ ፋይል)
በአስር ወራት ውስጥ ከቡና ሽያጭ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአስር ወራት ውስጥ ከቡና ሽያጭ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ በዚህ ዓመት ...
https://www.press.et/?p=100074
(ፎቶ ፋይል)
የጎዳና ተዳዳሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
ከ22 ሺህ በላይ የጎዳና ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ፕሮጀክት ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እስታወቀ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶክተር) እንደገለጹት፤ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በጎዳና ላይ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
ፕሮጀክቱ በሀገሪቱ በአዲስ መልክ የተቀረጸ ሲሆን በመጀመሪያው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=100078