Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የሚኒስትሮች የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ 2ኛውን የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ዛሬ ተመልክቷል። በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጣይ ተግባር አቅጣጫዎችን አስቀምጠው የ100 ቀን ግምገማውን ዛሬ ማጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈትቤት አስታውቋል።
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ለኢትዮጵያ የስንዴ ምርት የገበያ መዳረሻዎችን አስመልክተው ይናገራሉ‼️

👉 ኢትዮጵያ በመስኖ ለምታለማው የስንዴ ምርት ግብጽን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገራት የገበያ መዳረሻ ናቸው፣

👉 ኢትዮጵያ ስንዴ በማምረቱም ሆነ በገበያው ብዙ ዕድሎች ስላሏት የአፍሪካ ሀገሮች የገበያዋ መዳረሻ ይሆናሉ፤

👉 53ቱ የአፍሪካ አገራት ለኢትዮጵያ የስንዴ ምርት የገበያ መዳረሻ ናቸው፣

👉 ኢትዮጵያ ለስንዴ ተስማሚ የሆነ አየር ንብረት አላት፤ ሀገሪቱ በክረምትም ሆነ በበጋ ማምረት ትችላለች፣

👉 በሌላ አገር የሚመረተው አንዴ ነው፤ በበረዶ የተሸፈነ ስለሚሆን በረዶው እስከሚያልፍ ይጠብቃሉ፣ ትልልቅ አምራች የሚባሉት እንደ ራሺያ፣ ዩክሬን፣ ጀርመን የመሳሰሉት በዚህ የታጠሩ ናቸው፣

👉 የሌላውን አገር ትተን አፍሪካን ብቻ ብንመለከት ከእኛ የተሻለ ስንዴ ምርት ያላት ግብጽ ብቻ ናት፣ ኢትዮጵያ ወደ 82 ሚሊዮን ኩንታል እንናመርታለን፤ ግብጽ ወደ 100 ሚሊዮን ታመርታለች፣

👉 ትኩረት ሰጥን በፕሮግራም ደረጃ የያዝናቸው የገቢ ምንጮች አሉ፤ ስንዴ፣ ሩዝ፣ የአኩሪ አተር ሰብሎች ይጠቀሳሉ፣

👉 አኩሪ አተር ወደ ኢንዱስትሪ ይሄዳል፤ ዘይት ይወጣዋል፤ ተረፈ ምርቱ ለዶሮ ወይም ለከብቶች ምግብ ይሆናል፣

👉 በመስክ ሥራ ከአርሶ አደሩ ጋር አብሮ ይሰለፋል፤ ሥራውን በተግባር እየሠራም ያሳያል፤ ወደ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆን የአርሶ አደር ቤተሰቦች ይዟል፣

👉 እነዚህ አርሶ አደሮች ውስጥ 85 ሺህ ኩታ ገጠም እርሻዎች አሏቸው፣

👉 ለአብነት ያህል ሲዳማ ክልል ውስጥ ለአቡካዶ እርሻ በኩታ ገጠም የተደራጁ አርሶ አደሮች አሉ፤ እነሱን አቡካዶን ለግብዓትነት ከሚፈልጉ ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር ፈጥረዋል፣

👉 አንድ ኩታ ገጠም እርሻ ቢያንስ 30 ሔክታር ይሆናል፤ ለኩታ ገጠም እርሻዎች 10 የመካናይዜሽን ማዕከላት ተቋቁመዋል፣

👉 የተለያዩ የእርሻ ማሸነሪ አንቀሳቃሾችን በኦፕሬተርነት ያሰለጥናል፣

👉 የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትዩትነት በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጥናት የማድረግ ኃላፊነት ተጨምሮለታል፣

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለምልልሱን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ  https://www.press.et/?p=99932
ጽንፈኝነት ምንጩ፣ ጉዳቱ እና አደጋው
*************
(ኢ ፕ ድ)

አሁን አሁን ጽንፈኝነት በአገራችን ከሃሳብ አልፎ ጉዳቱ በተግባር እየታየ መምጣቱን ብዙዎች ይስማማሉ።ጽንፈኝነት በብሔር ወይም በሃይማኖት ዋሻ በመደበቅ የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ለማሳካት የሚፈልጉ ኃይሎች መሰባሰቢያም ነው።

ጽንፈኝነት ለሌላው አመለካከት ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ አብሮ የመኖርን እና በመነጋገር ችግሮችን ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99975
የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን ማዘጋጀት ትችላለች
*******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ግንባታ በ2016 ዓ.ም ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን ማዘጋጀት እንደምትችል ተገለጸ። በአሁኑ ጊዜም የማዕከሉ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ አፈጻጸም 76 በመቶ መድረሱን ተመልክቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99984
በስልጤ ዞን 15 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ነው
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሚገኘው የስልጤ ዞን ከ 15 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ፍራፍሬ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙርሰል አማን ለኢትዮጵ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዞኑ የፍራፍሬ ምርትን በስፋት ለገበያ ለማቅረብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።በዚህም በአሁኑ ጊዜም ከ 15 ሺ በላይ ሄክታር መሬት በፍራፍሬ እየለማ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=99977
አውደ ርዕዩ በግብርና ዘርፉ የመጣውን ተጨባጭ ውጤት ማሳያ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 30 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የግብርናና ሳይንስ ዐውደ ርዕይ በግብርና ዘርፍ የተገኘው ተጨባጭ ውጤት ማሳያ መሆኑን ተሳታፊዎችና ጎብኚዎች ተናገሩ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ስራ አስፈጻሚ ስር የጥራጥሬ ሰብሎችና ድህረ ምርት አያያዝ ዴስክ ኃላፊ አቶ ስብሀት ተመስገን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አውደ ርዕዩ መንግሥት በተለያዩ ሚዲያዎች የሚናገረውን የልማት ስራዎችን እንደማሳያ ማቅረቡ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠውና በተጨባጭም በዘርፉ ምን ምን ስራዎች እንደተሰሩ ግልጽ ማሳያ ነው፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ አካላት እርስ በእርስ የገበያ ትስስት በመፍጠር የተሻለ ምርታማነት እንዲኖር፣ የግል ባለሀብቶች ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100000
የኢፕድ የስራ ማስታወቂያዎች፤ መልካም ዕድል ‼️