Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
በዴንቨር ቆይታዬ ከኮሎራዶ የጥቁር ሴቶች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፕሬዝዳንት ቢያንካ ኤመርሰን ጋር የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎን ማሳደግ እና ማብቃት ላይ በትብብር ለመስራት ተወያይተናል።
በዘጠኝ ወራት ከ8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ተኪ ምርት ተመርቷል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ስምንት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ተኪ ምርት ማምረት እንደተቻለ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወደ ዉጪ ከተላኩ የኢንዱስትሪ ምርቶችም ከ260 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን ጠቁሟል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለጹት፤ የወጪ ምርት ገቢ እና የተኪ ምርት ማሳደግ ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሠራ ቆይቷል። በዚህም በዘጠኝ ወራት ወደ 124 ሺህ 636 ቶን ምርት ወደውጭ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100455
“በአዲስ አበባ ከተማ የሚሠሩ መሠረተ ልማቶች አረንጓዴ ልማትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው”
- አቶ ጥራቱ በየነ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ
******************************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የሚሠሩ መሠረተ ልማቶች አረንጓዴ ልማትን ማዕከል ባደረገ መልኩ መሆኑን የከተማዋ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገለጹ:: የአዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ ልማት ሽፋን ከአራት በመቶ ወደ 15 በመቶ ከፍ ብሏል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ባለፈው ሳምንት ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100457
ለኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት የቱሪዝም ዘርፉን ሚና ማሳደግ ይገባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ለኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት የቱሪዝም ዘርፉን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ትናንት ተጀምሯል፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ እንደተናገሩት፤ የቱሪዝም ዘርፉ ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ በስፋት ሊሰራበት ይገባል።
ቱሪዝም ዘርፈ ብዙ ሀብቶቻችን ላይ አተኩሮ የሚሰራ በመሆኑ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100469
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቻይናው አቻቸው ቺን ጋንግ ጋር ተወያዩ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና የመንግስት ምክር ቤት አባል እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ለ5 ቀናት ይፋይዊ የስራ ጉብኝት ቻይና የገቡት አቶ ደመቀ መኮንን በውይይታቸው ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ሁለትዮች ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል፡፡
የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ላይ ቻይና ትልቅ ሚና እየተጫወተች መሆኗን የገለፁት ሚንስትሩ፤ የቻይና ህዝብ እና መንግስት ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት እና ለአፍሪካ እንደ አጠቃላይ ታማኝ ወዳጅ ናቸው ብለዋል፡፡
የቻይናው አቻቸው በበኩላቸው ኢትዮጵያ ታማኝ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ የቻይና መንግስት አዳዲስ ለውጦች በጋራ ለማስመዝገብ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች በሚደረጉ የመልሶ ግንባታ እና የማቋቋም ስራዎች ላይ ሀገራቸው አስተዋፅኦ እንደምታደርግ መጠቆማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ፡፡
#የአፍሪካ_ቀን‼️
አፍሪካዊያን በጋራ የመሠረቱት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ አፍሪካ ህብረት ከተመሠረተ 60 ዓመታትን አስቆጠረ።
ይህንን በዓል በማስመልከት የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ዛሬ ይታያልል።
በፎቶግራፍ አውደ ርዕዩ የትናንቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የዛሬው የአፍሪካ ህብረት ባለፉት 60 አመታት የተጓዘውን ጉዞ የሚያሳዩ ታሪካዊ ፎቶግራፎች ለእይታ ቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እለታዊ መረጃን እየዘገበ ታሪክ በመሰነድ 82 አመታት ‼️
የአፍሪካ ህብረት 60ኛ አመት በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)
የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት 60ኛ አመት የምስረታ በአል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሐማት፣ የወቅቱ የሕብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በተገኙበት “የእኛ አፍሪካ የወደፊት ዕጣችን” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።

በዚሁ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትረ ዐቢይ አህመድ፤ "አፍሪካ ባላት የህዝብ ብዛት ልክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በወቅቱ ነጻነታቸውን በተጐናጸፉ 32 ሀገራት መመስረቱን አስታውሰው፤ ለአፍሪካ ብልጽግና በጋራ በመስራት የመስራች አባቶቻንን አላማ ማሳካት ያስፈልጋል ብለዋል።

አሁን አፍሪካን ወደ አንድነትና ወደ ብልጽግና ለማሻገር ባላት የህዝብ ብዛት ልክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል ሲሉም ነው የተናገሩት።

ጠንካራ አህጉራዊ ሚዲያ ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እንደ ረሃብና ግጭት ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት ይገባል፤ አህጉሪቷ በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት ተጠቅሞ ለዜጐቿና ለኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ ማድረገ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በሙስና፣ በግጭትና በብልሹ አሰራር ምክንያት አብዛኛው ህዝብ በድህነት የሚኖር በመሆኑ ይሄንን ተግዳሮት መቅረፍ የግድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በሞገስ ጸጋዬ