Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ (ሲድካ) ሊቀመንበር ሊዎ ጃወሁይ ጋር ዛሬ በቤጂንግ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት አቶ ደመቀ ቻይና በአገሮች የውስጥ ነጻነት ጣልቃ ሳትገባ የጋራ ተጠቃሚነት መርሆዎች ላይ በመመስረት ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቻይና በደቡብ-ደቡብ የትብብር ማዕቀፍ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኗንም ተናግረዋል፡፡

በቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም ( ፎካክ) የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ ይፋ በተደረጉት ዘጠኙ መርሃ ግብሮች መሰረት እ.ኤ.አ. ከ2022 እስከ 2024 የተያዙ አዳዲስ እና ነባር ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ እስከ ፕሮጀክቶቹ ፍጻሜ ድረስ ተቋሙ ትብብሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው ቻይና ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የመልሶ መቋቋምና ዳግም ግንባታ ድጋፍ እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሊቀመንበር ሊዎ ጃወሁይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ አጋር ብቻ ሳትሆን በአፍሪካ ትልቅ ተፅዕኖ ያላት አገር በመሆኗ ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ በትምህርት፣ በግብርና፣ በተፋሰስ ልማት እና ሌሎችም መስኮች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡
ለፕራይም ቲሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
****************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ለፕራይም ቴሌቪዥን ጣቢያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አሰታወቀ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መገናኛ ብዙኃን በዜጎች መካከል አብሮነትን ከሚሸረሽርና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለአለመተማመን ከሚዳርግ የይዘት ስርጭት እንዲቆጠቡ ግዴታ ይጥላል፡፡

በኢፌድሪ ህገመንግስት፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና በሌሎች ተያያዥ ሕጎችም ፤ የመገናኛ ብዙኃን በተለይም የጋራ እሴቶችን የሚንዱ፣ አለመቻቻል እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ እና ዜጎችን ለግጭት ሊያነሳሱ የሚችሉ ስርጭቶችን ከማስተላለፍ እንዲታቀቡ ይደነግጋሉ፡፡

ፕራይም ቴሌቪዥን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ሕግጋት የሚጥሱ ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን ሲያሰራጭ መቆየቱን በክትትል ሥራችን አረጋግጠናል። ከክትትል ውጤቱም በመነሳት በተደጋጋሚ እርምት እንዲወሰድ ግብረመልስ ተሰጥቶታል፤ በቅርቡም በቀን 4/9/2015ዓ.ም በባለሥልጣ ጽ/ቤት ውይይት ማካሄዱን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ ፕራይም ቴሌቪዥን ስህተቱን በመቀጠል የዜጎችን አብሮነት የሚጎዳ፣ ይልቁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሹ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አሉታዊና ሕግን የሚተላለፉ ይዘቶችን በማሰራጨት ዜጎችን ላልተገባ ውጥረትና አደጋ አስተዋፅኦ የማድረግ አዝማሚያ እንደታየበትም ተጠቁሟል፡፡

ይህም በተለይም ፕራይም ቴሌቪዥን እንደ ንግድ ብሮድካስተር ከገባው የውል ግዴታና ከተቋቋመለት ዓላማ አንጻር ተገቢ ያልሆነ ተግባር እንደሆነ ታምኖበታል ሲልም ባለስልጣኑ ለኢፕድ በላከው መግለጫው አስታውቋል፡፡

ስለዚህም ፕራይም ቴሌቪዥን ከዚህ ድርጊቱ እንዲታረም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማት አሸነፈ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማት አሸንፏል፡፡ አየር መንገዱ ሽልማቱን የተቀዳጀው በምርጥ የበረራ መስተንግዶ፣ መዝናኛ ፣ ምግብና መጠጥ፣ ምቾት እንዲሁም በገመድ ዓልባ የኢንተርኔት “ዋይ ፋይ”አገልግሎት ዘርፎች መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።
አቶ ደመቀ መኮንን በቤጂንግ የተገነባውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መርቀው ከፈቱ
*********************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዲሪ መንግስት በቻይና ርዕሰ መዲና ቤጂንግ ያስገነባውን አዲስ ኤምባሲ እና የመኖሪያ ህንጻ በዛሬው ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት አስመርቋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኤምባሲው አዲስ ገጽታ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የአጋርነት ጠቀሜታ የበለጠ ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ ተጨባጭ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያና የቻይና የቀደመ ግንኙኑት በሁለቱ አገሮች ማካከል ላለው ጥልቅ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ በባህላዊ እና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር መሠረት የጣለ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ለቻይና-አፍሪካ ትብብር ስኬት ተምሳሌት ለመሆን ተግታ ትሰራለች ብለዋል።

አያይዘውም፣ ኢትዮጵያና ቻይና የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማጎልበት በሁለትዮሽ በክልላዊና በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በጋራ እንደሚቆሙ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋን፣ አዲሱ ኤምባሲ መገንባቱ የኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።


የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው፣ የኤምባሲው ህንጻ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቻይና ላደረገላቸው ያላሰለሰ ትብብር አመስግነው፣ አጅግ በረቀቀ መልኩ የተገነቡት የኤምባሲው እና የመኖሪያ ቤቱ ህንጻዎች ለትውልድ የሚተርፍ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ በቻይና የኢፌዲሪ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ባደረጉት ንግግር፣ የኤምባሲው ግንባታ የኢትዮጵያና ቻይና ወዳጅነት ሃውልት ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢፕድ የላከው መረጃ ያመለክታል።
በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ጉድኝት መፍጠርና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ምኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በመገኘት ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ መጽሃፍት መረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቻይና የምርምር ተቋማት ጋር የእውቀት ልውውጥ ማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲተና በቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲት መካከል ያለው የአማርኛ ቋንቋ ትብብር የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ጂያ ዌንጂያን (GIA WENGIAN) በበኩላቸው ቋንቋው በቻይና መሰጠቱ የኢትዮጵያን በህልና ታሪክ ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀቤታ አለው ብለዋል፡፡

በስነስርዓቱ ሶስት የአማርኛ መመሪያ መጽሃፍቶች የተመረቁ ሲሆን ቻይናውያን የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ግጥም አቅርበዋል፡፡
በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ዴሞክራሲን ከአህጉሪቱ ነባር እሴቶች አንጻር ቃኝቶ መተግበር ያስፈልጋል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ዴሞክራሲን ከራሳችን ከአፍሪካውያን ማንነትና እሴት አንጻር ቃኝቶ መተግበር ያስፈልጋል ሲሉ በኢትዮጵያ የአንጎላ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚጉኤል ዶሚንጎስ ቤምቤ (ዶክተር) ገለጹ።
በርካታ የአፍሪካ አገራት የሚጠበቅባቸውን የአባልነት መዋጮ በአግባቡ ባለመክፈላቸው የህብረቱ ኢኮኖሚያዊ ነጻነት ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓልም ብለዋል።
አምባሳደር ሚጉኤል ዶሚንጎስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኅብረቱና...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100525
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መልዕክት‼️
የዚህ ዓመት የበጋ ስንዴ ምርታማነት በጥሩ ሂደት ላይ ይገኛል።
👉“በአፈር ማዳበሪያ እጥረት ምክንያት መሬታችን ፆም እንዳያድር እየሰጋን ነው” -የአማራ ክልል አርሶ አደሮች
👉“በክልሉ የተከሰተውን የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራን ነው” -የክልሉ ግብርና ቢሮ
************************
(ኢ ፕ ድ)
በአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ምክንያት ቀድመው መዘራት ያለባቸው ምርቶችን መዝራት ባለመቻላችን መሬታችን ፆም እንዳያድር ከፍተኛ ስጋት ገብቶናል ሲሉ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ገለጹ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ የተከሰተውን የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራሁ ነው ብሏል።
በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደምበጫ ወረዳ አርሶ አደር አቶ ገደፍ ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በደምበጫ ወረዳ የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት እጥረት በመኖሩ ምክንያት ቀድመው የሚዘሩ ምርቶችን መዝራት አልቻልንም፤ በመሆኑም መሬታችን ፆም እያደረ ነው ብለዋል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100567
ፎቶ ከፋይል