Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በኢትዮጵያ ካሉት 200 የዓሣ ዝርያዎች ስድስቱ ብቻ ለገበያ ይቀርባሉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ካሉት ከ200 በላይ የዓሣ ዝርያዎች ለገበያ የሚቀርቡት ስድስቱ ብቻ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በግብርና ሚኒስቴር የዓሣ ሃብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ፋሲል ዳዊት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በሚገኙ በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ የውሃ አካላት ከ200 በላይ የዓሣ ዝርያዎችን ይዘዋል።
እንደ ዶክተር ፋሲል ገለጻ፣ በሀገሪቷ ለዓሣ እርባታ ምቹ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100777
የቱርኩ ፕሬዝዳንት በድጋሜ በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶኻን በድጋሜ በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልዕክታቸው "በድጋሚ በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያልዎት" ብለዋል።
በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል ያለው የቆየ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ትናንት በቱርክ በተደረገ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በድጋሚ ተመርጠዋል።
ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ ይወሰዳል
******
(ኢ ፕ ድ)

ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሽከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በድሉ ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ መንግሥት ሕገወጥነትን ለመከላከል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ነው።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100799
ግጭቶችን በውይይት መፍታት ባሕል ሊደረግ ይገባል
****
(ኢ ፕ ድ)

በሃገሪቱ የሚከሰቱ ግጭቶችን በውይይት መፍታት ባሕል ሊደረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር መብራቱ ዓለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ የሚከሰቱ ግጭቶችን በውይይት መፍታት ባሕል እንዲሆን በትኩረት ሊሠራ ይገባል።

ከኃይል ርምጃ በተላቀቀ መንገድ ውይይትን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100821
የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ክምችት አወጋገድ እቅድ እንዲዘጋጅ ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ

👉 በአምስት ከተሞች ከአራት ሺህ ቶን በላይ ክምችት መኖሩ በጥናት ተረጋግጧል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)

የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በተቋማት የሚገኙ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ክምችቶች እንዴት፣ መቼና በማን እንደሚወገዱ የሚያሳይ ልዩ እቅድ እንዲያዘጋጅ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።

ቋሚ ኮሚቴው የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የክዋኔ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100822
አስተዳደራዊ በደልን ለመከላከል በተደረገ ቁጥጥር የሕግና አሠራር ክፍተቶች ተገኝተዋል
*****
(ኢ ፕ ድ)

አካል ጉዳተኞች እና ሴቶች ላይ የሚደርሰውን አስተዳደራዊ በደል ለመከላከል በተደረገ ጥናትና ቁጥጥር የተለያዩ የሕግና አሠራር ክፍተቶች መኖራቸውን የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ገለጸ።

ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሴቶች፣ ሕጻናት፣ የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ጉዳይ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰብለወርቅ ታሪኩ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ የሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=100796
የግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
🔥1
#ከአፕድ_ማህደር

ሚስቱን በሴንጢ የገደለው በስቅላት ተቀጣ

የቤት ክዳን ቆርቆሮ በመንኳኳቱ ምክንያት ጠብ ፈጥሮ በለጤ ገበየሁ የተባላች ሚስቱን በአውቶማቲክ ሴንጢ ወግቶ የገደለው በቀለ አረሩ፤ ወንጀሉን በፈፀመበት ቀበሌ በእቴጌ መስክ አቅራቢያ ከቀኑ በአምስት ሰዓት ላይ በስቅላት ተቀጣ፡፡

በቀለ አረሩ በለጤ ገበየሁ የተባለች ሚስቱን የገደለው ጥር 2 ቀን 1956 ዓ.ም ከቀኑ 11 ስዓት ላይ ሲሆን ለወንጀሉ አፈፃፀም መነሻ ያደረገው ከላይ በተጠቀሰው ቀን የቤት ክዳን ቆርቆሮ መንኳኳቱን ነበር፡፡

በዚሁ ጊዜ ቆርቆሮውን የመታሽው አንቺ ነሽ በማለት ስለተቆጣ ሟች ከፍርሃት የተነሳ ሸሽታ አቶ አለማየሁ የተባሉ ሰው ቤት ገብታ እንጀራ መጋጋሪያ ጓዲያ ውስጥ ተደበቀች፡፡ እርሱም ያለችበት ስፍራ ድረስ ተከታትሎ ሄዶ በአውቶማቲክ ሴንጢ ወግቶ ገደላት፡፡

ይህንን አሰቃቂ ወንጀል ከፈፀመ ብኋላ ለማምለጥ ሲሞክር በህዝብ እርዳታ ተከቦ ተያዘ ፡፡ ወዲያውም ክስ ቀርቦበት የፈፀመው ወንጀል በህግ ስለተረጋጋጠ የከፍተኛውና የጠቅላይ ንጉሰ ነገስት ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ በማለት የሰጡትን ፍርድ፤ ግርማዊ ንጉሰ ነገስት ስላፀኑበት ቅጣቱን በስቅላት የተቀበለ መሆኑ የፍርድ ሚኒስቴር የወንጀል ጉዳይ ፅሕፈት ቤት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይህው ሰው ጥር 2 ቀን 1956 ዓ.ም ከላይ የተጠቀሰውን ወንጀል ከመፈፀሙ ሁለት ወር ያህል ቀደም ብሎ በጩቤ ወግቶ አቁስሏት እንደነበርና በዚያን ጊዜ የተለቀቀው እርሷ አልፈልገውም በማለቷ ምክንያት እንደነበር የፍርድ ወንጀለኛ ጉዳይ ፅ/ቤት በተጨማሪ አስረድቷል፡፡

መስከረም 9 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ

በሀይማኖት ከበደ
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከአለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በግብርናው ዘርፍ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ከአለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከአለም ባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በውይይታቸው በአየር ንብረት ለውጥ፣ በምግብና የምግብ ደህንነት፣ በአፈር ጤንነትና በውሃ ሃብት አያያዝና አጠቃቀም፣ በግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት ስራዎች፣ የገጠር የፋይናንስ አቅርቦትና አገልግሎትን ወደ አርሶና አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች ላይ በስፋት ተወያይተዋል፡፡

በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ በግብርናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክትና ፕሮግራሞች ላይ በሚሰሩት ስራ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በጣሊያን ሊጉሪያ፣ ቪያሌ ዲአወስታና ቱስካኒ ክልሎች የሚሸፍን የኢትዮጵያ የክብር ቆንስላ በጄኖአ ከተማ ተከፈተ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ከ150 በላይ የሚሆኑ ከሶስቱ ክልሎችና ከጄኖአ ከተማ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የጄኖአ ከተማ አስተዳደርና አመራሮች፣ ትላልቅ ባለሀብቶችና የጄኖአ ወደብ አመራሮችና ተቆጣጣሪዎች በተገኙበት በጄኖአ ከተማ ስለኢትዮጵያ አሁናዊ ጉዳዮችና የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሄዷል።

በውይይቱ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታና አዲሱ የኢኮኖሚ ሪፎርም እና በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩት በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ እና የክብር ቆንስል ሆነው የተሾሙት አቶ ጃንፔሮ ሱቺ ሲሆኑ፣ በመድረኩ የጣሊያን የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አምባሳደር ጂዩሴፔ ሚስትሬታ የክብር እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል።

በመድረኩ በኢትዮጵያ በሎጂስቲክና ታዳሽ ኃይል ኢንቨስት እያደረጉ ያሉት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስላለው ሰላም አስተማማኝና ሰፊ ገበያ ያለ መሆኑን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

የጣሊያን ንግድ ማህበር የሆነው Confindustria Assafrica ተወካዮች ማንኛውንም የኢንቨስትመንትና ንግድ እንቅስቃሴ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለማጠናከር የሚፈለግባቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።