የቦሌ ሚካኤል ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የሚያሻሽሉ 6 የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድዮችን በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የቦሌ ሚካኤል የመንገድ መጋጠሚያ አንዱ ነው፡፡
የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ከተገነቡ አዳዲስ መንገዶች ጋር ተሳስሮ ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ አቅጣጫ ከሚወስደው የቀለበት መንገድ ጋር በተለያዩ መጋጠሚያዎች የሚያገናኙ የመቃረቢያ መንገዶችን ጨምሮ የቦሌ ሚካኤል የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ፕሮጀክት ግንባታ እውን እንዲሆን ምክንያት ሆኗል፡፡
ፕሮጅክቱ ከ720 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አሰር ኮንስትራክሽን የተባለ የሀገር ውስጥ የሥራ ተቋራጭ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ በሀይ ዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ኩባንያ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ቀደም ሲል 600 ሜትር ርዝመት ያለው የቦሌ ሚካኤል ትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት የተደረገ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ክፍል 3.8 ኪሎ ሜትሩ የመጀመርያ አስፋልት ደረጃ ለብሷል።
በተጨማሪ በቀሪው 200 ሜትር በሚሆነው የመንገዱ ክፍል የአስፋልት ንጣፍ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በድሬዳዋ በመጪው ክረምት ሁለት ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በመጪው ክረምት ሁለት ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የባለሥልጣኑ የደን ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ይመር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ከ10 በላይ የችግኝ ጣቢያዎች የችግኝ ተከላ ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል።
ከሚተከሉት ሁለት ሚሊዮን ችግኞች መካከል ከ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ዝግጁ ተደርገዋል፡፡ በቀሪ ጊዜያት በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የተለያዩ የዛፍ ችግኞች ይዘጋጃሉ ብለዋል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101062
#የሐላላ ኬላ ሪዞርት‼️
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ’ገበታ ለሀገር’ ፕሮጄክት አካል የሆነውና በኮይሻ ፕሮጄክት ክላስተር ሥር የለማውን የሐላላ ኬላ ሪዞርትን ዛሬ በይፋ ተረክቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለ ሀገር’ ፕሮጄክት አካል የሆነው እና በኮይሻ ፕሮጄክት ክላስተር ሥር የለማውን የሐላላ ኬላ ሪዞርት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዛሬ መረከቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አሰታውቋል።
ሪዞርቱን ‘ሐላላ ኬላ ሪዞርት’ በሚል ስያሜ ለማስተዳደር የክልሉ መንግሥት ከፓራዳይዝ ሎጆች፤ ሪዞርቶችና ሆቴሎች ማኔጅመንት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር ስምምነት አድርጓል።

#ከአፕድ_ማህደር
የኔ መኪና የምትጠጣው ውሃ ነው⁉️
ከዲላ- ወናጎ መስመር የሚያገለግሉ የሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች በቤንዚን ሰበብ ያለታሪፍ ማስከፈል ከጀመሩ ዘግየት ብሏል።
ታዲያ ተመላላሹ ሕዝብ እየቸገረው ያለአግባብ እየከፈለ ሲሆን የስምሪት ክፍል ሰራተኞችም ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠታቸው ችግሩ እየተባባሰ ሄዷል። የሕዝቡ ቅን አገልጋይ የነበሩ አንዳንድ ሾፌሮችም..."የኔስ መኪና ውሃ ነው የምትጠጣው ... እያሉ እንደ ሌሎቹ ያለ ታሪፍ ማስከፈል ጀምረዋል።
የመስመሩ ተጠቃሚዎች የሆኑት አብዛኛዎቹ ተማሪዎችና የመንግሥት ስራተኞች በመሆናቸው በትምህርትና በሥራ ሰዓት የትራንስፖርቱ ችግር የሚያስመርር ሆኗል።
የሕዝብ ማላለሻ ኮርፖሬሽን ተጠዋሪዎች ሁኔታውን በቸልታ ባይመለከቱት ችግሩ መፍትሔ ባገኘ ነበር።
ታህሳስ 17 ቀን 1980 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ

“የአዲስ አበባ ፖሊስ ሚዲያ አመራርና ባለሙያዎች ከኢፕድ ስልጠና በማግኘታቸው ትልቅ ክብር ይሰማናል”
- ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስልጠና ማዕከል ለአዲስ አበባ ፖሊስ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡
በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ኢትዮጵያ ባላት በእያንዳንዱ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያለው ተቋም ነው፡፡
ኢፕድ አንጋፋና በአገሪቱ የፕሬስ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና አለው ያሉት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሚዲያ አመራርና ባለሙያዎች በዚህ ተቋም ስልጠና በማግኘታቸውም ትልቅ ክብር ይሰማናል ብለዋል፡፡
የፖሊስ ሥራ የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ መሆኑን አስታውሰው፤ ሚዲያው ይህን ሥራ በማገዝ በኩል ትለቅ ጉልበት አለው፡፡ የአዲስ ፖሊስ ሚዲያ ኅብረተሰቡን በማንቃትና አጋዥ ሆኖ እንዲያገለግል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ የአሁኑ ስልጠናም ለተቋሙ ሚዲያ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ከተማ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለ82 ዓመታት የኢትዮጵያን የየዕለት ሁነት በመዘገብ ታሪክ እየሰነደ የመጣ አንጋፋ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ብዙዎቹ የአገራችን ታዋቂ ደራሲያን በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ውስጥ አገልግለው ያለፉ መሆናቸውን አስታውሰው፤ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃንና ስነጽሑፍ ታሪክ ውስጥም ጉልህ ሚና አለው፡፡
በዓለም ላይ ሉ አንጋፋ መገናኛ ብዙሃን ከሚዲያ ሥራቸው በተጓዳኝ የልህቀት ማዕከል ሆነው ያገለግላሉ ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዚህ ዘርፍ ያለውን ክፍተት ለመሙላትና ልምዱን ለማካፈል የስልጠና ማዕከል ከፍቶ ተከታታይ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ተደራሽነቱን ለማስፋት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች እያከነወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ የስልጠና ማዕከሉም የዚህ ሥራ አንድ አካል ነው፡፡
ፖሊስ በክፍያ የማይተመን ዋጋ እየከፈለ ሃገር እና ሕዝብ የሚጠብቅ ተቋም ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህን ተቋም ሥራው ስኬታማ እንዲሆን ማገዝ ትልቅ እርካታ ይፈጥራል፡፡ እናንተም ቤታችሁ የሆነውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን መርጣችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስልጠና ማዕከል እስካሁን ድረስ በ27 ዙሮች ለ66 የፌዴራልና የክልል ተቋማት፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ስልጠናዎችን ሰጥቷል፡፡
በፋንታነሽ ክንዴ

በስድስት ቋንቋዎች መረጃዎችን እያደረሰ የሚገኘው የኢፕድ አሁን ደግሞ በአፋርኛ ቋንቋ ወደ እናንተ መረጃዎችን እያደረሰ ይገኛል፤ ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን በአፋርኛ ቋንቋ ለማግኘት የፌስቡክ ገጻችንን ይቀላቀላሉ።
👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100092595632078