Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በስድስት ቋንቋዎች መረጃዎችን እያደረሰ የሚገኘው የኢፕድ አሁን ደግሞ በአፋርኛ ቋንቋ ወደ እናንተ መረጃዎችን እያደረሰ ይገኛል፤ ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን በአፋርኛ ቋንቋ ለማግኘት የፌስቡክ ገጻችንን ይቀላቀላሉ።
👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100092595632078
👉 "በተሰጠው የውጭ የትምህርት እድል መስፈርቱን የማያሟሉ ተማሪዎች እንዲካተቱ ተደርጓል"
- በ2014 ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እና ወላጆች
👉 "ለተወሰኑ ቅሬታዎች ምላሽ ሰጥተናል፤ የተቀሩትንም እናጣራለን" - የትምህርት ሚኒስቴር
******
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 ዓመተ ምህረት በ12ተኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች በተሰጠው የውጭ የትምህርት እድል መካተት ያልነበረባቸው ተማሪዎች እንዲካተቱ ተደርጓል ሲሉ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ገለጹ።

ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ለተወሰኑ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠቱን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101130
ለኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ የተጠየቀው የመሬት ካሳ ክፍያ በገለልተኛ አካል እንዲታይ ተወሰነ
👉 በካሳ ክፍያ ምክንያት ግንባታው ሳይጀመር ሦስት ዓመታት አልፈዋል፣
******
(ኢ ፕ ድ)
ለኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታ የተጠየቀው 525 ሚሊዮን ብር የመሬት ካሳ ክፍያ በገለልተኛ አካል ሊታይ መሆኑን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

የደረቅ ወደቡ ማስፋፊያ ግንባታ ሳይጀመር ከሶስት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ባህር፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የወደብና ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101164
የግብርና ኤግዚቢሽኑ 50 ሺህ ጎብኚዎችን አስተናግዷል
***
(ኢ ፕ ድ )
‹ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ›› በሚል መሪ ሃሳብ ከአራት ሳምንት በፊት በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የግብርና ኤግዚቢሽን 50 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎብኘታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ እንደገለጹት፤ ኤግዚቢሽኑ ከተጀመረ አራት ሳምንታት የሆነው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ 50 ሺህ ጎብኚዎችን አስተናግዷል።

አግዚቢሽኑ ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ እንደሚጠናቀቅ ሚኒስትሩ ....
ሙሉውን ለማንበብ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101111
4ኛው ብሩህ ኢትዮጵያ 2015 አገር አቀፍ የስራ ፈጠራ ውድድር ከግንቦት 28 ጀምሮ ለ15 ቀናት ይካሄዳል
***
(ኢ ፕ ድ)
የስራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች፣ ማሰልጠን፣ ማወዳደርና መሸልም አላማው ያደረገው ብሩህ ተስፋ 2015 ውድድር ከግንቦት 28 ጀምሮ ለ15 ቀናት በቡራዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ማእከል እንደሚካሄድ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በ2013 ዓ.ም የተጀመረው ብሩህ ተስፋ የስራ ፈጠራ ውድድር አራተኛ አመቱ ላይ ደርሷል።

ውድድሩ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች በየደረጃው በማወዳዳር ሀሳባቸው የስራ እድል እንዲፍጥር የማድረግ አላማ ያለው ነው ብለዋል።

በዘንድሮው የውድድር በአንድ ሺ 240 ያህል ወረዳዎች፣ በ98 ዞኖች፣ በ50 ዪኒቨርስቲዎች የውድድር ማኑዋል ተዘጋጅቶ ተሰጥቶ።

በዚህም ከአፋርና ደቡብ ም ዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውጪ በ10 ክልሎች በየደረጃው ውድድር እንዲካሄድ ተደርጓል።

በዚህ ዓመት 200 ሀስቦች በተለያዩ ደረጃዎች ቀርበው የሚወዳደሩ ሲሆን ከእነዚህም 70 የሚሆኑት ሀሳቦች ተለይተው በዳኞች አማካኝነት የመጨረሻዎቹን 50 ምርጥ ሀስቦች የስራ መነሻ ካፒታል ለእያንዳንዳቸው አምስት ሺ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው፣ እስካሁን በተካሄዱ ሰባት አገር አቀፍና ክልላዊ ውድድሮች ሁለት ሺ 412 አመልካቾች ተሳትፈው ለ400 ሀሳብ ባለቤቶች ወይም 542 ወጣቶች የቡት ካምፕ ስልጠና ተሰጥቷል።

ለ167 ምርጥ ሀሳቦች የአንድ ሚሊዮን 518 ሺ ዶላር የመነሻ ሀሳብ ካፒታል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ብለዋል።

በሞገስ ተስፋ
የጋምቤላ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግብርና ሳይንስ አውደርዕይን ጎበኙ
*********
(ኢ ፕ ድ)
የጋምቤላ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በግብርና ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ አውደርዕይን ጎበኙ።

የጋምቤላ ክልል አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የቀረቡ የግብርና ውጤቶችን፣ የግብርና ሳይንስ ቴክኖሎጂዎችንና ግብር የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በክልሉ የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋጽኦና ሌሎች የክልሉ ሃብቶች ለዕይታ ቀርበዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን
የግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
#ከአፕድ_ማህደር

ሆድ ወይስ ሻንጣ⁉️

ያገሬ ሰው ነገር ሲገባው "ሆድ አይችለው የለ" ይላል። በእውነትም ሆድ የማይችለው ነገር የለም። የቤልጂግ ተወላጅዋ የወይዘሮ ማግዳሌና ጉዳይ አንድ ሰሞን ብርቅዬ ዜና ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል።

ወይዘሮዋ የተደነቁበት ጉዳይ በበጎ ሥራቸው አይደለም።


ጉዳዩ እንደዚህ ነው። ከዙሪክ ወደ ሚላን በሚጓዘው አውሮፕላን ተሳፍረው ሚላን ይደርሳሉ። መቼም አውሮፕላን ማረፊያው ሲደረስ የማይፈቀድ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በያዙ ሰዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መደረጉ የዘወትር ሥራ ነውና ተጓዦች በሙሉ ይፈተሻሉ።


ከተጓዦች መካከል ወይዘሮ ማግደሌና የተለየ መቅበጥበጥ በማሳየታቸው በባለሥልጣኖች ልዩ ፍተሻ እንዲደረግ ይታዘዛል።


በትዕዛዙም መሠረት በልዩ መመርመሪያ መሣሪያ ሲመረመሩ በሆዳቸው ውስጥ 10ሺህ ዕንቁዎችንና 217 ተመሳሳይ የሆኑ የከበሩ ድንጋዮች ቁርጥራጭ ውጠው ተገኝተዋል።


ይህም በገንዘብ ሲሰላ አንድ ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ ታምኗል። ለመሆኑ ሞት ወይስ በአጭር ጊዜ ሊከበር፤ ምርጫቸው ምን እንደነበረ ለእርሳቸው ትተናል። ቢታለፍስ እንዴት ሆኖ ሊወጣ?

ታህሳስ 10 ቀን 1980 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ

በበሪሁ አረጋ
ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የተሰጠ መግለጫ‼️

ህዝበ ሙስሊሙ ለሀገራችን ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ጽኑ እምነት ያለው፣ ሀገር እየጠበቀ፣ እየገነባና የራሱን ድርሻ እያበረከተ መሆኑ ይታወቃል።

ሰሞኑን መስጅዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም የፀጥታ አካላት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ መስዋዕትነት ከፍለው የከተማውን ሰላም ማረጋጋታቸው የሚታወቅ ነው።

ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስም የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በሰጠው መግለጫ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ መስጅዶች የተካሄደው የጁምአ ሶላት በሰላም ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቶች ያስተላለፉትን ሰላማዊ መልዕክት በመተላለፍ በታላቁ አንዋር መስጅድ የጁምዓ ሶላት በሰላም ተጠናቆ ህዝብ ሙስሊሙ እየተመለሰ ባለበት ሁኔታ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የሴራ ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ለማድረስ በተነሳ ረብሻ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም እስከ አሁን ግምቱ ያልተወቀ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ለፀጥታ ሥራ በተሰማሩ 63 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

ፀረ-ሰላም ኃይሎች የእምነቱ ተከታዮች በህጋዊ መንገድ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጥለፍ የራሳቸውን እኩይ ዓላማ ለማሳካት ረብሻውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት ያደረጉት ጥረት የፀጥታ ኃይሉ፣ ህዝበ ሙስሊሙ እና የሀይማኖቱ አባቶች በጋራ በመሆን ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

ግብረ-ኃይሉ የከተማውን ብሎም የሀገራችንን ሠላምና ደህንነት ለማስከበር የጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እና በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ ውጤቱን ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ሰላም የሁሉም የእምነት ተቋማት የአስተምሮታቸው መሠረት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ የሚያነሳውን ማንኛውንም ጥያቄ በህግ አግባብ በሰላማዊ መንገድ ማስተናገድ የሚቻልበት ሥርዓት መኖሩን በመገንዘብ ለፀረ-ሠላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሳይሆን የፀጥታ አካላት የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ ህዝበ ሙስሊሙ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪውን ያቀርባል።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል
ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የዲጂታል ግብይት ተስፋና ስጋት
*************
(ኢ ፕ ድ)


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የዲጂታል ግብይት/ዲጂታል ፋይናሲንግ/ሥርዓት እየተስፋፋ መጥቷል:: አንዳንድ ግብይቶችም ከወረቀት ገንዘብ ወደ ዲጂታል ሥርዓት እየተቀየሩ ይገኛሉ:: ለመሆኑ የዲጂታል ግብይት ሥርዓት መስፋፋት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ተስፋ ወይስ ስጋት?


በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው ዶክተር ጀማል መሐመድ፤ ዲጂታል ፋይናንስ በዋናነት የፋይናንስ ሥርዓትን በወረቀት ገንዘብ ከማድረግ ይልቅ በዲጂታል መገበያየትና ገንዘብ መላክን የሚመለከት ሥርዓት ነው ይላሉ:: ይህ በሰፊው በአውሮፓና በአሜሪካ እየተተገበረ ያለ እንደሆነም ይጠቅሳሉ::


ባደጉት አገራት ላይ ኢንተርኔትን ጨምሮ መሠረተ ልማቱ የሚመችና የመጠቀም አቅማቸውም ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101191
በክልሉ በመጪው የመኸር እርሻ 97 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል
********************
(ኢ ፕ ድ)

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 97 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡


በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015/16 የመኸር ....


ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101192
ከሰሐራ በታች ባሉት የአፍሪካ ሃገራት ከአስር ልጃገረዶች አንዷ በወር አበባ ምክንያት ትምህርቷን ታቋርጣለች
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ከሰሐራ በታች ባሉት የአፍሪካ ሃገራት ከአስር ልጃገረዶች አንዷ በወር አበባ ምክንያት ትምህርቷን እንደምታቋርጥ ተገለጸ፡፡ ዓለም አቀፍ የወር አበባ ንጽሕና አጠባበቅ ቀን የመንግሥት አካላት፣ አምራቾች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በተገኙበት በትናንትናው ዕለት ተከብሯል፡፡


በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሴቶች ማንቃት ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ ወይንሸት ገለሶ እንደገለጹት፤ በዓለም ላይ ቢያንስ 500 ሚሊዮን ሴቶችና ልጃገረዶች የወርአበባ ንጽሕና መጠበቂያ ማግኘት የማይችሉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ22 ሚሊዮን በላይ ሴቶች በዚህ ችግር ውስጥ ያልፋሉ፡፡


እንደ ወይዘሮ ወይንሸት ገለጻ፤ በሀገራችን የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ ከሚያስፈልጋቸው ሴቶችና ልጃገረዶች ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101198