Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጋምቤላ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የግብርና ሳይንስ አውደርዕይን ጎበኙ
*********
(ኢ ፕ ድ)
የጋምቤላ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በግብርና ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ አውደርዕይን ጎበኙ።

የጋምቤላ ክልል አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የቀረቡ የግብርና ውጤቶችን፣ የግብርና ሳይንስ ቴክኖሎጂዎችንና ግብር የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በክልሉ የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋጽኦና ሌሎች የክልሉ ሃብቶች ለዕይታ ቀርበዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን
የግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
#ከአፕድ_ማህደር

ሆድ ወይስ ሻንጣ⁉️

ያገሬ ሰው ነገር ሲገባው "ሆድ አይችለው የለ" ይላል። በእውነትም ሆድ የማይችለው ነገር የለም። የቤልጂግ ተወላጅዋ የወይዘሮ ማግዳሌና ጉዳይ አንድ ሰሞን ብርቅዬ ዜና ሆኖ ሲሠራ ቆይቷል።

ወይዘሮዋ የተደነቁበት ጉዳይ በበጎ ሥራቸው አይደለም።


ጉዳዩ እንደዚህ ነው። ከዙሪክ ወደ ሚላን በሚጓዘው አውሮፕላን ተሳፍረው ሚላን ይደርሳሉ። መቼም አውሮፕላን ማረፊያው ሲደረስ የማይፈቀድ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በያዙ ሰዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መደረጉ የዘወትር ሥራ ነውና ተጓዦች በሙሉ ይፈተሻሉ።


ከተጓዦች መካከል ወይዘሮ ማግደሌና የተለየ መቅበጥበጥ በማሳየታቸው በባለሥልጣኖች ልዩ ፍተሻ እንዲደረግ ይታዘዛል።


በትዕዛዙም መሠረት በልዩ መመርመሪያ መሣሪያ ሲመረመሩ በሆዳቸው ውስጥ 10ሺህ ዕንቁዎችንና 217 ተመሳሳይ የሆኑ የከበሩ ድንጋዮች ቁርጥራጭ ውጠው ተገኝተዋል።


ይህም በገንዘብ ሲሰላ አንድ ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያወጣ ታምኗል። ለመሆኑ ሞት ወይስ በአጭር ጊዜ ሊከበር፤ ምርጫቸው ምን እንደነበረ ለእርሳቸው ትተናል። ቢታለፍስ እንዴት ሆኖ ሊወጣ?

ታህሳስ 10 ቀን 1980 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመ

በበሪሁ አረጋ
ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የተሰጠ መግለጫ‼️

ህዝበ ሙስሊሙ ለሀገራችን ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ጽኑ እምነት ያለው፣ ሀገር እየጠበቀ፣ እየገነባና የራሱን ድርሻ እያበረከተ መሆኑ ይታወቃል።

ሰሞኑን መስጅዶች ፈርሰዋል በሚል ምክንያት በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም የፀጥታ አካላት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ መስዋዕትነት ከፍለው የከተማውን ሰላም ማረጋጋታቸው የሚታወቅ ነው።

ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስም የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በሰጠው መግለጫ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ መስጅዶች የተካሄደው የጁምአ ሶላት በሰላም ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቶች ያስተላለፉትን ሰላማዊ መልዕክት በመተላለፍ በታላቁ አንዋር መስጅድ የጁምዓ ሶላት በሰላም ተጠናቆ ህዝብ ሙስሊሙ እየተመለሰ ባለበት ሁኔታ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ የሴራ ቡድኖች የሰላቱን ሰላማዊ ሥነ-ሥርዓት ለማስከበር በተሰማሩ የፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ለማድረስ በተነሳ ረብሻ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በንብረት ላይም እስከ አሁን ግምቱ ያልተወቀ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ለፀጥታ ሥራ በተሰማሩ 63 የፖሊስ አመራር እና አባላት ላይ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

ፀረ-ሰላም ኃይሎች የእምነቱ ተከታዮች በህጋዊ መንገድ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጥለፍ የራሳቸውን እኩይ ዓላማ ለማሳካት ረብሻውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት ያደረጉት ጥረት የፀጥታ ኃይሉ፣ ህዝበ ሙስሊሙ እና የሀይማኖቱ አባቶች በጋራ በመሆን ባደረጉት ርብርብ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

ግብረ-ኃይሉ የከተማውን ብሎም የሀገራችንን ሠላምና ደህንነት ለማስከበር የጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለፀ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እና በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ ውጤቱን ለህዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ሰላም የሁሉም የእምነት ተቋማት የአስተምሮታቸው መሠረት በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ የሚያነሳውን ማንኛውንም ጥያቄ በህግ አግባብ በሰላማዊ መንገድ ማስተናገድ የሚቻልበት ሥርዓት መኖሩን በመገንዘብ ለፀረ-ሠላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሳይሆን የፀጥታ አካላት የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ ህዝበ ሙስሊሙ የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪውን ያቀርባል።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል
ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የዲጂታል ግብይት ተስፋና ስጋት
*************
(ኢ ፕ ድ)


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የዲጂታል ግብይት/ዲጂታል ፋይናሲንግ/ሥርዓት እየተስፋፋ መጥቷል:: አንዳንድ ግብይቶችም ከወረቀት ገንዘብ ወደ ዲጂታል ሥርዓት እየተቀየሩ ይገኛሉ:: ለመሆኑ የዲጂታል ግብይት ሥርዓት መስፋፋት ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ተስፋ ወይስ ስጋት?


በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው ዶክተር ጀማል መሐመድ፤ ዲጂታል ፋይናንስ በዋናነት የፋይናንስ ሥርዓትን በወረቀት ገንዘብ ከማድረግ ይልቅ በዲጂታል መገበያየትና ገንዘብ መላክን የሚመለከት ሥርዓት ነው ይላሉ:: ይህ በሰፊው በአውሮፓና በአሜሪካ እየተተገበረ ያለ እንደሆነም ይጠቅሳሉ::


ባደጉት አገራት ላይ ኢንተርኔትን ጨምሮ መሠረተ ልማቱ የሚመችና የመጠቀም አቅማቸውም ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101191
በክልሉ በመጪው የመኸር እርሻ 97 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይሰበሰባል
********************
(ኢ ፕ ድ)

በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን 97 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡


በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015/16 የመኸር ....


ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101192
ከሰሐራ በታች ባሉት የአፍሪካ ሃገራት ከአስር ልጃገረዶች አንዷ በወር አበባ ምክንያት ትምህርቷን ታቋርጣለች
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ከሰሐራ በታች ባሉት የአፍሪካ ሃገራት ከአስር ልጃገረዶች አንዷ በወር አበባ ምክንያት ትምህርቷን እንደምታቋርጥ ተገለጸ፡፡ ዓለም አቀፍ የወር አበባ ንጽሕና አጠባበቅ ቀን የመንግሥት አካላት፣ አምራቾች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በተገኙበት በትናንትናው ዕለት ተከብሯል፡፡


በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሴቶች ማንቃት ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ ወይንሸት ገለሶ እንደገለጹት፤ በዓለም ላይ ቢያንስ 500 ሚሊዮን ሴቶችና ልጃገረዶች የወርአበባ ንጽሕና መጠበቂያ ማግኘት የማይችሉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ22 ሚሊዮን በላይ ሴቶች በዚህ ችግር ውስጥ ያልፋሉ፡፡


እንደ ወይዘሮ ወይንሸት ገለጻ፤ በሀገራችን የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ ከሚያስፈልጋቸው ሴቶችና ልጃገረዶች ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/?p=101198
“የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች ራስ ገዝ መሆናቸው በትምህርት ክፍያ ላይ የሚያሳድረው ሥጋት አይኖርም” ዶክተር ነገሪ ሌንጮ
********************
(ኢ ፕ ድ)

አዲሱ የዩኒቨርስቲዎች ራስ ገዝ አዋጅ የአገሪቱ የሪፎርም አካል ከመሆኑ ባሻገር በትምህርት ክፍያ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሌለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ::


“አዲሱ የዩኒቨርስቲ ራስ ገዝ አዋጅ የአገሪቱን ነባራዊ የኑሮ ሁኔታን ያላገናዘበ በመሆኑ በተለይ ድሃ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከፍለው መማር አይችሉም” በሚል አንዳንድ ሰዎች የሚያነሱትን ቅሬታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከዶክተር ነገሪ ሌንጮ ጋር ቆይታ አድርጓል::


ዶክተር ነገሪ እንደገለጹት፣ የአዋጁ መነሻ አገራዊ ሪፎርሙ አካል ሲሆን የመጨረሻ ግቡ ደግሞ የአገሪቱን ....


ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=101197
የግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
"የኢትዮጵያና ቻይና የሁለትዮሽ ትብብር ሁሉን አቀፍና ስትራቴጂካዊ ነው"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
**************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነትና ትብብር ሁሉን አቀፍና ስትራቴጂካዊ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያና የቻይናን ትብብርና ወዳጅነት ያጸና ብቻ ሳይሆን ወደ ላቀ ስኬታማ ደረጃ ያሸጋገረና በአፍሪካ ቀንድና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ትብብራቸውን ለማጠናከር መግባባት ላይ የተደረሰበት እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም መግለጻቸውን ይታወሳል።

ኢትዮጵያና ቻይና በአፍሪካ ቀንድና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ
ስምምነቶች ማድረጋቸውንም አምባሳደር መለስ በሳምንተዊ መግለጫቸው ጠቁመዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይናው ሲጂቲኤን 'ሃይ ቶክ' ከተሰኘው ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያና የቻይና የሁለትዮሽ ትብብር ጠንካራና ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ነው።

ሁለቱ አገራት ያልተነኩ እድሎችን ለመጠቀም ያላቸው ፍላጎት ግንኙነታቸውን ብሩህ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ከሁለትዮሽ ትብብራቸው ባለፈ የኢኮኖሚ ትስስር ላይ የሚያተኩረው የደቡብ-ደቡብ ትብብር አንዱ ማሳያ ነው ያሉት አቶ ደመቀ ይህ ትብብር የአፍሪካ አህጉር የልማት ሕልሞች ምሳሌ ነው ብለዋል።

የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭንና የቻይና አፍሪካን የትብብር ፎረምን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በቻይና የስራ ጉብኝት ማድረጉ ይታወቃል።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የግንባታ ጥበብ የሚያስቃኝ ቋሚ አውደ ርዕይ በላሊበላ ከተማ ተከፈተ
**************************
(ኢ ፕ ድ)

ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፈረንሳይ ኤምባሲ የዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት ጋር በመቀናጀት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጥበብ የሚያስቃኝ "ላሊበላ በእምነት የታነጸ" ቋሚ ቨርችዋል ሪያሊቲ አውደ ርዕይ በላሊበላ ከተማ ተከፍቷል።

"ላሊበላ በዕምነት የታነፀ" ቨርችዋል ሪያሊቲ አውደርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ ለሕብረተሰቡና ለጎብኚዎች በቋሚነት ክፍት ይሆናል።

የአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ ተወካዮችና የአካባቢው ማህበረሰብ መገኘታቸው ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴታ አቶ ስለሽ ግርማ፣ የቨርችዋል ሪያሊቲ በቴክኖሎጅ የታገዘ ኤግዚቢሽን ተዘጋጅቶ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በእንጦጦ ፖርክ መቅረቡን አሰታውሰው ታሪካዊ ቅርሶቹ መንፈሳዊ ይዘታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ቴክኖሎጅን በመጠቀም ቅርሱን በሰፊው በማስተዋወቅ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሃይሉ በታሪካዊነታቸውና በድንቅ ቅርስነታቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከመስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በእንጦጦ ፓርክ የላሊበላ ቅርሶችን የሚዘክር አውደ ርዕይ ለሁለት ወራት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።