Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
"የኢትዮጵያና ቻይና የሁለትዮሽ ትብብር ሁሉን አቀፍና ስትራቴጂካዊ ነው"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
**************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነትና ትብብር ሁሉን አቀፍና ስትራቴጂካዊ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያና የቻይናን ትብብርና ወዳጅነት ያጸና ብቻ ሳይሆን ወደ ላቀ ስኬታማ ደረጃ ያሸጋገረና በአፍሪካ ቀንድና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ትብብራቸውን ለማጠናከር መግባባት ላይ የተደረሰበት እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም መግለጻቸውን ይታወሳል።

ኢትዮጵያና ቻይና በአፍሪካ ቀንድና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ
ስምምነቶች ማድረጋቸውንም አምባሳደር መለስ በሳምንተዊ መግለጫቸው ጠቁመዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይናው ሲጂቲኤን 'ሃይ ቶክ' ከተሰኘው ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያና የቻይና የሁለትዮሽ ትብብር ጠንካራና ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ነው።

ሁለቱ አገራት ያልተነኩ እድሎችን ለመጠቀም ያላቸው ፍላጎት ግንኙነታቸውን ብሩህ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ከሁለትዮሽ ትብብራቸው ባለፈ የኢኮኖሚ ትስስር ላይ የሚያተኩረው የደቡብ-ደቡብ ትብብር አንዱ ማሳያ ነው ያሉት አቶ ደመቀ ይህ ትብብር የአፍሪካ አህጉር የልማት ሕልሞች ምሳሌ ነው ብለዋል።

የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭንና የቻይና አፍሪካን የትብብር ፎረምን በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በቻይና የስራ ጉብኝት ማድረጉ ይታወቃል።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የግንባታ ጥበብ የሚያስቃኝ ቋሚ አውደ ርዕይ በላሊበላ ከተማ ተከፈተ
**************************
(ኢ ፕ ድ)

ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፈረንሳይ ኤምባሲ የዘላቂ ላሊበላ ፕሮጀክት ጋር በመቀናጀት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጥበብ የሚያስቃኝ "ላሊበላ በእምነት የታነጸ" ቋሚ ቨርችዋል ሪያሊቲ አውደ ርዕይ በላሊበላ ከተማ ተከፍቷል።

"ላሊበላ በዕምነት የታነፀ" ቨርችዋል ሪያሊቲ አውደርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ ለሕብረተሰቡና ለጎብኚዎች በቋሚነት ክፍት ይሆናል።

የአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲና የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ ተወካዮችና የአካባቢው ማህበረሰብ መገኘታቸው ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴታ አቶ ስለሽ ግርማ፣ የቨርችዋል ሪያሊቲ በቴክኖሎጅ የታገዘ ኤግዚቢሽን ተዘጋጅቶ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ በእንጦጦ ፖርክ መቅረቡን አሰታውሰው ታሪካዊ ቅርሶቹ መንፈሳዊ ይዘታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ቴክኖሎጅን በመጠቀም ቅርሱን በሰፊው በማስተዋወቅ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሃይሉ በታሪካዊነታቸውና በድንቅ ቅርስነታቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ለመጠበቅና ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከመስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በእንጦጦ ፓርክ የላሊበላ ቅርሶችን የሚዘክር አውደ ርዕይ ለሁለት ወራት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
"ቻይናና ኢትዮጵያ የሚያደርጉት የባህልና የቋንቋ ልውውጥ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ያጠናክራል"
- በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን
*****
(ኢ ፕ ድ)
በቻይና መንግሥት አመቻቺነት በኢትዮጵያ የቻይና ቋንቋን በዩንቨርሲቲ ደረጃ ከሚያጠኑ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ቻይንኛን አንድ ክፍለ ጊዜ በሚወስዱ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በቻይንኛ የተለያዩ የመድረክ ሥራዎችን አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ በቻይንኛ ቋንቋ ንግግሮች፣ የቻይንኛ ሙዚቃ፣ ስፖርትና ልዩ ልዩ ትዕይንቶችን በውድድር አሳይተዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮጵያና ቻይና በተለያዩ የትብብር መስኮች የሚያደርጉት ግንኙነትና የባህልና የቋንቋ ልውውጥ ለአገራቱ ግንኙነት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

በመድረኩ በትምህርት ሚኒስቴር የዓለም አቀፋዊነትና ስኮላርሺፕ ዴስክ የተወከሉት ተረፈ በላይ በበኩላቸው ሁለቱ አገራት የረዥም ዓመታት ግንኙነት አላቸው ብለዋል።

አገራቱ ያላቸው አጋርነት በተለይም በኢኮኖሚ መስክ ወደ ላቀ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ጠቅሰው በሕዝቦች መካከል የባህል ትስስሩ መጠናከሩ ደግሞ የአገራቱን ሁለንተናዊ አጋርነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል። 

የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠርና ኢኮኖሚያዊ አጋርነቱን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው አብራርተዋል። 

በመድረኩ ላይ ሲሳተፉ የነበሩት ተማሪዎች በበኩላቸው አንዲህ ያለው ተሞክሮ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያደርሰዋል ብለዋል።

ቢሾፍቱ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምርት ቤት ተማሪ የሆነችው ሲያኔ ታደሰ መርሃ ግብሩ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለማጠናከር እድል እንደሚሰጥ ጠቁማለች።

በተለይም ቻይና አሁን ላይ የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆኗን ገልጻ በመሆኑም የቻይና ቋንቋ ማወቅ በዘርፉ ይበልጥ ተባብሮ ለመሥራት እንደሚያግዝ ተናግራለች።

ሌላኛው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ተማሪ ናፍያድ ንጋቱ ቻይንኛ የሚማሩ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸው እንዲሁም አማርኛ የሚማሩ ቻይናውያን መኖራቸው ትስስሩን ያጠናክራል ብሏል። 

በሁለቱ አገራት መካከል ግንኙነቱን ለማጠናከር የባህል ግንኙነቱ ትልቅ ጥቅም አለው ያለው ደግሞ በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ተማሪ በረከት ደመላሽ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።