Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፉት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናችው" -አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በቤተሰብ ደረጃና በማህበራት ተደራጅተው የተሰሩ የሌማት ትሩፋት አብነቶችን ጉብኝት ተካሂዷል።

በጉብኝቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ጌታቸው ጀንበር እና የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ ጆንባ ጨምሮ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ እና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ እንደገለጹት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፉት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው በማለት የተጀመሩ ሥራዎችን በማስፋት የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት እጅግ አበረታች ነው በማለት ተናግረዋል ።

በጉብኝቱም ወቅት በቤተሰብ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት አብነቶች በዶሮ ፣ በወተት ላሞች እና ሱፐር ኦቫ አግሮ ቴክ የተጎበኙ ሲሆን በከተማዋ በልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን የክልሉ መንግሥት የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተሠሩ የሚገኙ ሥራዎችን መመልከታቸው አስደሳች መሆኑን ከሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ህፃናት ቀንን በማስመልከት የአረንጋዴ አሻራ መርሐግብር ተካሄደ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር የአፍሪካ ህፃናት ቀንን በማስመልከት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር ተካሄደ።

"ሰላም ፣ፍቅር እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ህፃናት" በሚል በአፍሪካ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአፍሪካ ህፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በእንጦጦ ፖርክ ተካሄደ።

በመርሀግብሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኢርግጌ ተስፈዬ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሙድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት ማህበራዊ ቢሮ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዎል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኢርግጌ ተስፈዬ በመርሀግብሩ ላይ እንደገለፁት፣ ዘንድሮ "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአፍሪካ የህፃናት ቀን መካሄዱ ለነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህፃናት ዛሬ የምንሰራው ስራ ነገ የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ የሚያስችል መሰረት መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

በማህሌት ብዙነህ