Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ይጠበቃል
***************
(ኢ ፕ ድ)

በመጪው የመኸር ምርት ዘመን ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሩዝ ለመሰብሰብ ማቀዱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ዳይሬክተር አቶ አግደው ሞላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ በመጪው የመኸር የምርት ዘመን ከአምናው የተሻለ የሩዝ ምርት ለማግኘት ከወዲሁ በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡ ከመጪው የመኸር ምርት ዘመንም ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ለማግኘት ታቅዷል፡፡

በክልሉ ባለፈው የመኸር የምርት ዘመን 61ሺ ሄክታር መሬት በሩዝ ልማት መሸፈኑን አስታውሰው፤ ከዚህም በቅድመ ምርት ትንበያ መሠረትም ከሦስት ሚሊዮን በላይ ኩንታል የሩዝ ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ አግደው ገልጻ፤ ክልሉ በመጪው የመኸር የምርት ዘመን ከ100 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102729
የሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም የሰራ ማስታወቂያ‼️
ድርጅቱ የተቋረጠውን የውጭ የሰብዓዊ ድጋፍ ግንኙነት ለመመለስ ተግዳሮት ገጥሞታል
****
(ኢ ፕ ድ)

የክርስቲያን የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ኅብረት ድርጅት ባለፈው ሥርዓት ያጋጠመውን የውጭ አገር የሰብዓዊ ድጋፍ መልሶ ለማግኘት ተግዳሮት እንደገጠመው አስታወቀ፡፡

የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበር ኅብረት ዳይሬክተር ዶክተር ንጉሡ ለገሰ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ድርጅቱ የቋቋመው የሰብዓዊ ድጋፍ ለመሥራት ቢሆንም ያለፈው ሥርዓት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=102731
በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፉት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናችው" -አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በቤተሰብ ደረጃና በማህበራት ተደራጅተው የተሰሩ የሌማት ትሩፋት አብነቶችን ጉብኝት ተካሂዷል።

በጉብኝቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ጌታቸው ጀንበር እና የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ ጆንባ ጨምሮ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ እና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ እንደገለጹት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፉት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ናቸው በማለት የተጀመሩ ሥራዎችን በማስፋት የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት እጅግ አበረታች ነው በማለት ተናግረዋል ።

በጉብኝቱም ወቅት በቤተሰብ ደረጃ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት አብነቶች በዶሮ ፣ በወተት ላሞች እና ሱፐር ኦቫ አግሮ ቴክ የተጎበኙ ሲሆን በከተማዋ በልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን የክልሉ መንግሥት የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተሠሩ የሚገኙ ሥራዎችን መመልከታቸው አስደሳች መሆኑን ከሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ህፃናት ቀንን በማስመልከት የአረንጋዴ አሻራ መርሐግብር ተካሄደ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመተባበር የአፍሪካ ህፃናት ቀንን በማስመልከት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር ተካሄደ።

"ሰላም ፣ፍቅር እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ህፃናት" በሚል በአፍሪካ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአፍሪካ ህፃናት ቀንን ምክንያት በማድረግ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በእንጦጦ ፖርክ ተካሄደ።

በመርሀግብሩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኢርግጌ ተስፈዬ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሙድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት ማህበራዊ ቢሮ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ተገኝተዎል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኢርግጌ ተስፈዬ በመርሀግብሩ ላይ እንደገለፁት፣ ዘንድሮ "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአፍሪካ የህፃናት ቀን መካሄዱ ለነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህፃናት ዛሬ የምንሰራው ስራ ነገ የተሻለች ሀገር እንዲረከቡ የሚያስችል መሰረት መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

በማህሌት ብዙነህ