Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
**********************
(ኢ ፕ ድ)

የዘንድሮው የአፍሪካ ህጻናት ቀን በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ "ሰላም፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ህፃናት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የፓርላማ ተወካዮች፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የህጻናት ፓርላማ ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ተገኝተዋል።

በዓሉ በማርሽ ባንድ አዝናኝ ትርዒቶች የተጀመረ ሲሆን ዕለቱን የተመለከቱ ጠቃሚ መልዕክቶችም በተለያዩ አካላት እየተላለፉ ይገኛል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአፍሪካ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ የአፍሪካ ህብረት በወሰነው መሰረት "The Rights of Child in the Digital Environment" በሚል አህጉራዊ መሪ ቃል ይከበራል።

ሀገራት ህጻናትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደህንነትን በተመለከተ በአፍሪካ የህጻናት መብቶችና ደህንነቶች ቻርተር ላይ የሰፈሩ ድንጋጌዎችን፣ ሌሎች ህጋዊ የአሰራር ማዕቀፎችን እና ሌሎች የአህጉሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ቀኑን አስበው መዋላቸውን ከሴቶች እና ማኅበራዊ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
መልካም እድል🙏
ለወላይታ ዞን ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊ የምርጫ ግብዓቶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ደርሰዋል- ምርጫ ቦርድ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በወላይታ ዞን ነገ በድጋሚ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

በነገው ዕለት በዞኑ በድጋሚ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ቦርዱ ገልጿል፡፡

በዞኑ በ12 የምርጫ ማስተባበሪያ ማዕከላት 1 ሺህ 812 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በእነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች 9 ሺህ 60 የምርጫ አስፈፃሚዎች ወደ ተመደቡበት ጣቢያ መንቀሳቀሳቸው ተመላክቷል።

ከምርጫ አስፈፃሚዎች መካከል 5 ሺህ 212 የሚሆኑት ከአዲስ አበባ እንደመጡ የገለጸው ቦርዱ÷እነዚህም ከዚህ በፊት በሀገራዊ ምርጫ ተሳትፈው የተሻለ አፈጻፀም ያስመዘገቡ መሆናቸውን አንስቷል፡፡

ምርጫውን ለሚያስፈፅሙ አካላትም ቀደም ሲል አስፈላጊው ስልጠና መሰጠቱን ነው የቦርዱ መረጃ ያመላከተው፡፡

በአሀኑ ሰዓት ምርጫ አስፈፃሚዎቹም ሆኑ ሕዝበ ውሳኔውን ማካሄድ የሚያስችሉ ግብዓቶች ወደየምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸውን ቦርዱ አረጋግጧል፡፡

ሕዝበ ውሳኔው 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት የሚደረግ ሲሆን÷በወላይታ ዞን ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ በተፈፀሙ የሕግ ጥሰቶች ሳቢያ መሰረዙ የሚታወስ ነው ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የአፋር ልማት ማህበር ልዑካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቤታቸው ተቀበለው አነጋገሩ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በጅቡቲ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ልዩ-መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በዛሬው ዕለት በአቶ ጎልቤ ሲሌ ጎልቤ የአፋር ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽህፈጽ ቤት ኃላፊ እና የአፋር ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ የሚመራውን ልዑካን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱም ክቡር አምባሳደሩ የአፋር ልማት ማህበር ልዑካን በጅቡቲ የሚገኘውን የአፋር ልማት ማህበር አባላትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት ለማድረግ ወደ ጅቡቲ በመምጣታቸው አመስግነው፤ ልዑካን ቡድኑ የማህበሩ አባላትን ውይይት እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው እና ኤምባሲው የልዑካን ቡድኑ የመጣበትን ዓላማ እንዲያሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው አምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ መሪ የሆኑት አቶ ጎልቤ ሲሌ ጎልቤ በበኩላቸው ኤምባሲው ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ በቀጣይ በጅቡቲ የአፋር ልማት ማህበርን ለማጠናከር ከአባላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ገልፀው፤ በነገው እለት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ አጠቃላይ ከማህበሩ አባላት እና ከክልሉ ተወላጆች ጋር ውይይት እንዲሚያደርጉም ገልጸዋል ሲል ኤምባሲው ዘግቧል።
ዩኒቨርሲቲዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫና የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጁ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እና የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር መገርሳ ቃሲም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መውጫ ፈተናን በተሟላ መልኩ ለመስጠት የሚያስችለውን አቅም ከአምናው ልምድ በመቅሰም የዘንድሮውን ፈተና በብቃት ለመወጣት በርካታ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በዚህም ለተፈታኝ ተማሪዎች ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የምግብ፣ የጤና እና የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ጠንካራ ሥራዎች ተሰርተዋል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ ፈተናው ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102880
“አማራ እና ትግራይ ሁለት ስም ያለው አንድ ህዝብ ነው” -አቶ ጊደና መድሕን
የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ አስተባባሪ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የትግራይ እና የአማራ ህዝብ ሁለት ስም ያለው አንድ ህዝብ ነው ሲሉ የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ መስራችና አስተባባሪ አቶ ጊደና መድሕን ተናገሩ።

አቶ ጊደና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በአማራ ክልል ተገኝተው ከርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጋር የተጀመረውን ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102886
በክልሉ በ150 ሚሊዮን ብር ወጪ የመጻሕፍት ህትመት እየተከናወነ ነው
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

👉 ከ133 ሺህ በላይ መጻሕፍት ተሰራጭቷል

በአፋር ክልል 150 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ያደረጉ ከ730 ሺህ በላይ የመማሪያ መጻሕፍት ህትመት እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። ከ133 ሺህ በላይ መጻሕፍት ለተማሪዎች መሰራጨቱ ተገልጿል፡፡

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት አተገባበር በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜም 150 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102889
"የቀላል ባቡር ትራንስፖርት የመዘግየትና ከልክ በላይ የመጫን ችግር አለበት"
👉 ተጠቃሚዎች
"የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራን ነው"
👉 የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

በመዲናዋ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት እየሰጠ ያለው አገልግሎት ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም የመዝገየትና ከልክ በላይ የመጫን ችግር አለበት ሲሉ ተጠቃሚዎች ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ተጨማሪ ባቡሮችን ወደስራ ለማስገባት እና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ገነት ገብረእግዛብሔር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለማህበረሰቡ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102896
በመዲናዋ አምስቱም የመግቢያ በሮች አዳዲስ የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ ነው
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በአምስቱም የከተማዋ መግቢያ በሮች ባሉ አካባቢዎች አዳዲስ የገበያ ማዕከላትን የመገንባትና ነባሩን የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከተማው ላይ ያለውን የዋጋ ንረትና የምርት አቅርቦት እጥረት ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ቦታዎች የገበያ ማስፋፋት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102902