Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ መርሃ- ግብር እየተካሄደ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ- ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ፤ የሚተከሉት ችግኞች ዓለምን በከፍተኛ ደረጃ እያስጨነቀ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ለማስቀረትና እራስን በምግብ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በከተማ አስተዳደሩ ከ 41 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መትከል ተችሏል ያሉት ከንቲባዋ፤ በዘንድሮ ክረምት እስከ 17 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባዋ አክለውም የሐይማኖት ተቋማት ከላቸው ሰፊ ቦታ አኳያ ግንባር ቀደም በመሆን ችግኞች እንዲያስተክሉ ለሐይማኖት አባቶች ጥሪ አድርገዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው ሀገራት የሚያደርጉት ልማት ዘላቂ ከሚሆኑባቸው አብይ ጉዳዮች መካከል አካባቢን ያልበከለና ጽድ አካባቢ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

የሀገሪቱ በጣም ዝቅተኛ ከነበረበት የደን ሽፋን በመነሳት በሀገር አቀፍ ደረጃ 17 በመቶ መድረሱን የጠቀሙት ሚኒስትሩ፤ በዘንድሮ እንደሀገር ከስድስት ቢሊየን በላይ ችግኝ እንደሚተከል ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብርሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ፣ የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ የፌደራልና የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

እንደ አዲስ አበባ ከተማ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ካራ የተካሄደ ሲሆን፤ ከአምስት ሺህ በላይ ችግኞች ተተክለዋል፡፡

<<ነገን ዛሬ እንትከል>> በሚል መሪ ሃሳብ የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡
በልጅዓለም ፍቅሬ
የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
**********************
(ኢ ፕ ድ)

የዘንድሮው የአፍሪካ ህጻናት ቀን በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ "ሰላም፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ህፃናት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ የፓርላማ ተወካዮች፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የህጻናት ፓርላማ ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ተገኝተዋል።

በዓሉ በማርሽ ባንድ አዝናኝ ትርዒቶች የተጀመረ ሲሆን ዕለቱን የተመለከቱ ጠቃሚ መልዕክቶችም በተለያዩ አካላት እየተላለፉ ይገኛል።

የዘንድሮው የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአፍሪካ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ የአፍሪካ ህብረት በወሰነው መሰረት "The Rights of Child in the Digital Environment" በሚል አህጉራዊ መሪ ቃል ይከበራል።

ሀገራት ህጻናትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደህንነትን በተመለከተ በአፍሪካ የህጻናት መብቶችና ደህንነቶች ቻርተር ላይ የሰፈሩ ድንጋጌዎችን፣ ሌሎች ህጋዊ የአሰራር ማዕቀፎችን እና ሌሎች የአህጉሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ቀኑን አስበው መዋላቸውን ከሴቶች እና ማኅበራዊ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
መልካም እድል🙏
ለወላይታ ዞን ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊ የምርጫ ግብዓቶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ደርሰዋል- ምርጫ ቦርድ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በወላይታ ዞን ነገ በድጋሚ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

በነገው ዕለት በዞኑ በድጋሚ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ቦርዱ ገልጿል፡፡

በዞኑ በ12 የምርጫ ማስተባበሪያ ማዕከላት 1 ሺህ 812 የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በእነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች 9 ሺህ 60 የምርጫ አስፈፃሚዎች ወደ ተመደቡበት ጣቢያ መንቀሳቀሳቸው ተመላክቷል።

ከምርጫ አስፈፃሚዎች መካከል 5 ሺህ 212 የሚሆኑት ከአዲስ አበባ እንደመጡ የገለጸው ቦርዱ÷እነዚህም ከዚህ በፊት በሀገራዊ ምርጫ ተሳትፈው የተሻለ አፈጻፀም ያስመዘገቡ መሆናቸውን አንስቷል፡፡

ምርጫውን ለሚያስፈፅሙ አካላትም ቀደም ሲል አስፈላጊው ስልጠና መሰጠቱን ነው የቦርዱ መረጃ ያመላከተው፡፡

በአሀኑ ሰዓት ምርጫ አስፈፃሚዎቹም ሆኑ ሕዝበ ውሳኔውን ማካሄድ የሚያስችሉ ግብዓቶች ወደየምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸውን ቦርዱ አረጋግጧል፡፡

ሕዝበ ውሳኔው 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት የሚደረግ ሲሆን÷በወላይታ ዞን ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ በተፈፀሙ የሕግ ጥሰቶች ሳቢያ መሰረዙ የሚታወስ ነው ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የአፋር ልማት ማህበር ልዑካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቤታቸው ተቀበለው አነጋገሩ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በጅቡቲ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ልዩ-መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በዛሬው ዕለት በአቶ ጎልቤ ሲሌ ጎልቤ የአፋር ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽህፈጽ ቤት ኃላፊ እና የአፋር ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ የሚመራውን ልዑካን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱም ክቡር አምባሳደሩ የአፋር ልማት ማህበር ልዑካን በጅቡቲ የሚገኘውን የአፋር ልማት ማህበር አባላትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት ለማድረግ ወደ ጅቡቲ በመምጣታቸው አመስግነው፤ ልዑካን ቡድኑ የማህበሩ አባላትን ውይይት እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው እና ኤምባሲው የልዑካን ቡድኑ የመጣበትን ዓላማ እንዲያሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው አምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ መሪ የሆኑት አቶ ጎልቤ ሲሌ ጎልቤ በበኩላቸው ኤምባሲው ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ በቀጣይ በጅቡቲ የአፋር ልማት ማህበርን ለማጠናከር ከአባላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ገልፀው፤ በነገው እለት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ አጠቃላይ ከማህበሩ አባላት እና ከክልሉ ተወላጆች ጋር ውይይት እንዲሚያደርጉም ገልጸዋል ሲል ኤምባሲው ዘግቧል።