Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የአፋር ልማት ማህበር ልዑካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቤታቸው ተቀበለው አነጋገሩ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በጅቡቲ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ልዩ-መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በዛሬው ዕለት በአቶ ጎልቤ ሲሌ ጎልቤ የአፋር ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽህፈጽ ቤት ኃላፊ እና የአፋር ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ የሚመራውን ልዑካን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱም ክቡር አምባሳደሩ የአፋር ልማት ማህበር ልዑካን በጅቡቲ የሚገኘውን የአፋር ልማት ማህበር አባላትን ለማጠናከር ያለመ ውይይት ለማድረግ ወደ ጅቡቲ በመምጣታቸው አመስግነው፤ ልዑካን ቡድኑ የማህበሩ አባላትን ውይይት እንዴት ማድረግ እንዳለባቸው እና ኤምባሲው የልዑካን ቡድኑ የመጣበትን ዓላማ እንዲያሳካ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው አምባሳደሩ ገልፀውላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ መሪ የሆኑት አቶ ጎልቤ ሲሌ ጎልቤ በበኩላቸው ኤምባሲው ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ በቀጣይ በጅቡቲ የአፋር ልማት ማህበርን ለማጠናከር ከአባላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ገልፀው፤ በነገው እለት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ አጠቃላይ ከማህበሩ አባላት እና ከክልሉ ተወላጆች ጋር ውይይት እንዲሚያደርጉም ገልጸዋል ሲል ኤምባሲው ዘግቧል።
ዩኒቨርሲቲዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫና የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጁ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እና የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር መገርሳ ቃሲም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መውጫ ፈተናን በተሟላ መልኩ ለመስጠት የሚያስችለውን አቅም ከአምናው ልምድ በመቅሰም የዘንድሮውን ፈተና በብቃት ለመወጣት በርካታ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በዚህም ለተፈታኝ ተማሪዎች ምቹ አገልግሎት ለመስጠት የምግብ፣ የጤና እና የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ጠንካራ ሥራዎች ተሰርተዋል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ ፈተናው ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102880
“አማራ እና ትግራይ ሁለት ስም ያለው አንድ ህዝብ ነው” -አቶ ጊደና መድሕን
የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ አስተባባሪ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የትግራይ እና የአማራ ህዝብ ሁለት ስም ያለው አንድ ህዝብ ነው ሲሉ የትንሳኤ 70 እንደርታ ፓርቲ መስራችና አስተባባሪ አቶ ጊደና መድሕን ተናገሩ።

አቶ ጊደና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ በአማራ ክልል ተገኝተው ከርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጋር የተጀመረውን ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102886
በክልሉ በ150 ሚሊዮን ብር ወጪ የመጻሕፍት ህትመት እየተከናወነ ነው
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

👉 ከ133 ሺህ በላይ መጻሕፍት ተሰራጭቷል

በአፋር ክልል 150 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ያደረጉ ከ730 ሺህ በላይ የመማሪያ መጻሕፍት ህትመት እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። ከ133 ሺህ በላይ መጻሕፍት ለተማሪዎች መሰራጨቱ ተገልጿል፡፡

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት አተገባበር በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ጊዜም 150 ሚሊዮን ብር ተመድቦ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102889
"የቀላል ባቡር ትራንስፖርት የመዘግየትና ከልክ በላይ የመጫን ችግር አለበት"
👉 ተጠቃሚዎች
"የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራን ነው"
👉 የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

በመዲናዋ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት እየሰጠ ያለው አገልግሎት ከጊዜ ወደጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም የመዝገየትና ከልክ በላይ የመጫን ችግር አለበት ሲሉ ተጠቃሚዎች ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ተጨማሪ ባቡሮችን ወደስራ ለማስገባት እና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ገነት ገብረእግዛብሔር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለማህበረሰቡ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102896
በመዲናዋ አምስቱም የመግቢያ በሮች አዳዲስ የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ ነው
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በአምስቱም የከተማዋ መግቢያ በሮች ባሉ አካባቢዎች አዳዲስ የገበያ ማዕከላትን የመገንባትና ነባሩን የማስፋፋት ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከተማው ላይ ያለውን የዋጋ ንረትና የምርት አቅርቦት እጥረት ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ቦታዎች የገበያ ማስፋፋት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102902
የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው
******************
(ኢ.ፕ.ድ)

ጠንካራ ህብረ ብሄራዊ አገር መገንባትን አላማ ያደረገ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ ዲሞክራሲ እንዲጐለብት፣ በፌደራል መንግስትና በክልሎች መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ለማስቻል ምክር ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል።

ይህ አይነቱ መድረክም ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርአት እንዲጐለብት በማድረግ ህጋዊና ተቋማዊ ግንኙነት እንዲኖር ለማስቻል አስፈላጊ ነው ብለዋል።

አፈጉባኤው የውይይት መድረኩ ህብረ ብሄራዊና ጠንካራ አገር ለመመስረት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።

ክፍተቶችን ለይቶ በማረም ጠንካራ ህብረ ብሄራዊ ስርአት እንዲፈጠር ለማድረግ በፌደራል መንግስትና በክልል መንግስታት መካከል ያለው ግንኙነት አስፈላጊ ነውም ብለዋል።

የክልሎችና የፌደራል መንግስትና በክልል መንግስታት እንዲሁም በመስሪያ ቤቶች መካከል ስለሚኖረው ግንኙነት ግንዛቤ መፍጠር የውይይት መድረኩ አላማ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በጋራ የምክክር መድረኩ በተለያዩ ምሁራን "የመንግስታት ግንኙነት ለጠንካራ ፌዴራል ስርዓት ግንባታ ያለው ሚና" እና "የመንግስታት ግንኙነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ እና ቀጣይ አቅጣጫ" በሚሉ ርዕሶች ጽሁፎች ቀርበው ምክክር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የክልል አፈ-ጉባዔዎችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ተገኝተዋል።
ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ፖለቲከኞች በኃላፊነት ሊሰሩ ይገባል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ፖለቲከኞች በኃላፊነትና ከሕጋዊ ሥርዓት ባልወጣ መንገድ ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር መብራቱ አለሙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ ዕድገት እና ልማትን ማምጣት የሚቻለው እያንዳንዱን ተግባር በኃላፊነት እና በሕጋዊ ሥርዓት ማከናወን ሲችል ነው፡፡ በመሆኑም በአገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ፖለቲከኞች በኃላፊነት ሊሰሩ ይገባል፡፡

ፖለቲከኞች ፖለቲካቸውን በኃላፊነትና በሕጋዊ መንገድ ማራመድ ይኖርባቸዋል ያሉት ዶክተር መብራቱ፤ በዚህም ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102873
ለተሻለ ውጤት የቅድመ ፈተና ትጋት
*************
(ኢ ፕ ድ)

ያለንበት ዘመን እውቀት ግድ የሚልበት ነው። ሳይንስና ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ ባደገበት በዚህ ዘመን ከትምህርት ውጭ ተወዳዳሪ ሆኖ መኖር አዳጋች ነው። አገራት ኩራታቸው ምንጩ የተማረ የሰው ኃይላቸው ነው፡፡ የሰውኛ ቋንቋ መግባቢያ የሕይወት ማጣፈጫ ቅመም የመኖር ድንቅ ቅኔ ነው መማር።

መማር ሰው መሆን ይመተርበታል፤ ከልክ የሚልቅ ከመለኪያ በላይም ጭምር፡፡ የሰው ልጅ ራሱን በዛሬ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102883
በክልሉ ከአምስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ እንሰት እየለማ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በሲዳማ ክልል ለእንሰት ሀብት ልማት ትኩረት በመስጠትና በስፋት በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102893
ከእንስሳት ሀብት የሚገኘውን ምርት በሳይንሳዊ ዘዴ ለማሳደግ እየተሠራ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)

የእንስሳት ተዋጽዖ አቅርቦትን ለማሳደግ በዝርያ ማሻሻል፣ በመኖ አቅርቦት እና በእንስሳት ጤና ጥበቃ ዙሪያ ሳይንሳዊ የአሰራር ዘዴዎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሆነ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ተዋጽዖ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102899
በሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ምክክር ተካሄደ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የሚደረገው ምክክር በገንዘብ ሚኒስቴር ተጀምሯል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ረቂቅ ላይ ከአጋሮች ጋር እየተካሄደ ያለውን የቴክኒክ ምክክር የመሩት ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ የተለያዩ ለጋሽ አካላትና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።

በረቂቁ ላይ ከቀረበው ገለጻ በኋላ በማሻሻያው ቁልፍ ምሰሶዎች እና ለጋሽ አካላት እገዛ ሊያደርጉባቸው ስለሚችሉት ዘርፎችና በመጪዎቹ ሶስት ዓመታት ማሻሻያውን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስፈልጉ ግብዓቶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል።

በዚሁ ውይይት ላይም ለጋሽ አካላት የማሻሻያውን አጠቃላይ ጥንካሬ ገምግመው በኢኮናሚው ላይ የሚኖረውን አጠቃላይ መረጋጋትና ሊያስከትል የሚችለውን እድገት አድንቀዋል።

በቀጣይ ሳምንትም ረቂቁ ለለጋሽ አገራት አምባሳደሮች ቀርቦ ሊደረግ በሚችሉ ድጋፎች ዙሪያ ያለው ሃሳብ ይዳብራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሙሳ ሙሐመድ
መልካም እድል🙏