Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ ከአምስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ እንሰት እየለማ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በሲዳማ ክልል ለእንሰት ሀብት ልማት ትኩረት በመስጠትና በስፋት በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102893
ከእንስሳት ሀብት የሚገኘውን ምርት በሳይንሳዊ ዘዴ ለማሳደግ እየተሠራ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)

የእንስሳት ተዋጽዖ አቅርቦትን ለማሳደግ በዝርያ ማሻሻል፣ በመኖ አቅርቦት እና በእንስሳት ጤና ጥበቃ ዙሪያ ሳይንሳዊ የአሰራር ዘዴዎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሆነ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ተዋጽዖ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102899
በሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ምክክር ተካሄደ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የሚደረገው ምክክር በገንዘብ ሚኒስቴር ተጀምሯል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ በሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ረቂቅ ላይ ከአጋሮች ጋር እየተካሄደ ያለውን የቴክኒክ ምክክር የመሩት ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ የተለያዩ ለጋሽ አካላትና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል።

በረቂቁ ላይ ከቀረበው ገለጻ በኋላ በማሻሻያው ቁልፍ ምሰሶዎች እና ለጋሽ አካላት እገዛ ሊያደርጉባቸው ስለሚችሉት ዘርፎችና በመጪዎቹ ሶስት ዓመታት ማሻሻያውን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስፈልጉ ግብዓቶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል።

በዚሁ ውይይት ላይም ለጋሽ አካላት የማሻሻያውን አጠቃላይ ጥንካሬ ገምግመው በኢኮናሚው ላይ የሚኖረውን አጠቃላይ መረጋጋትና ሊያስከትል የሚችለውን እድገት አድንቀዋል።

በቀጣይ ሳምንትም ረቂቁ ለለጋሽ አገራት አምባሳደሮች ቀርቦ ሊደረግ በሚችሉ ድጋፎች ዙሪያ ያለው ሃሳብ ይዳብራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሙሳ ሙሐመድ
መልካም እድል🙏
በወላይታ ዞን እየተካሄደ የሚገኘው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ‼️

የወላይታ ዞን የድጋሚ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ መስጠት ሂደት ዛሬ ማለዳ
12፡00 ተጀምሯል። ቦርዱ የድጋሚ ህዝበ ውሳኔውን የሚያከናውኑ የምርጫ አስፈፃሚዎችን በተለያየ መንገድ የመለመለ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ 5215 የምርጫ አስፈፃሚዎች እና ከወላይታ 3845 የምርጫ አስፈፃሚዎች ተሳትፈዋል።

በዛሬው እለት ሁሉም አስፈፃሚዎች በስራ ላይ ተሰማርተው መራጮችን በማስተናገድ ላይ ይገኛሉ። አንድ አንድ ሰልፎች የበዙባቸው ጣቢያዎች ላይ ቦርዱ አሰልጥኖ በተጠባባቂነት የያዛቸውን አስፈፃሚዎችን አሰማርቷል። በ1812 የምርጫ ጣቢያዎች የተሟላ የምርጫ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን ቦርዱ አረጋግጧል።

ከጠዋት 12፡00 ሰዓት እንከ 6፡00 ሰዓት በተገኘው መረጃ 370,552 መራጭ ድምፅ ሰጥቷል። በተያያዘም የድምፅ መስጠት ሂደት ቦርዱ ለሶስት የሀገር ውስጥ ተቋማት የታዛቢነት እውቅና ሰጥቶ በዞኑ የተለያዩ ጣቢያዎች ላይ 214 ታዛቢዎች ተሰማርተዋል።

የድምፅ መስጠት ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ በርከት ያሉ መራጮች ከተሠጣቸው 6 ወር ያልሞላው መታወቂያ ሆኖ ተገኝቷል። ነገር ግን የቦርዱ መመሪያ አንድ ዜጋ ድምፅ መስጠት የሚችለው በመኖርያ ስፍራው ቢያንስ ለስድስት ወር እና ከዚያ በላይ መኖሩ መረጋገጥ እንዳለበት ተጠቅሷል። ስለዚህ እነዚህ መራጮች ከያዙት የነዋሪነት መታወቂያ በተጨማሪ ነዋሪነታቸውን የሚያረጋግጡበት የሶስት ሰዎች ምስክርነት ወይም ሌሎች የሠነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ ድምፅ እንዲሰጡ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም
"በክልላችን ማንም ምንም አይነት ወንጀል ፈጽሞ ማምለጥ የማይችልበት ጠንካራ የጸጥታ መዋቅር አደራጅተናል" የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

በሲዳማ ክልል ዉስጥ ማንም ምንም አይነት ወንጀል ፈጽሞ ማምለጥ የማይችልበት ጠንካራ የጸጥታ መዋቅር አደራጅተናል ሲል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ተጠለፈች የተባለችውን የ8ኛ ክፍል ተማሪ በተደረገዉ ክትትል ትላንት ማታ ከይርጋለም ከተማ ከእነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ማወላቸውን
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ገልጸዋል።

በቅርቡ በሀዋሳ ከተማ ተከሰቱ በተባሉ የጠለፋ ወንጀሎች ምክንያት ስም የሚያጠለሹ አካላት እንደነበሩ ገልጸዉ፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የክልሉን ሰላም አስተማማኝነት ለማስቀጠል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነዉ ያሉት ሀላፊው፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ አስተማማኝ የጸጥታ መዋቅር የተዘረጋ መሆኑን ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡም ሰላሙን ለማረጋገጥ ከፀጥታው ሀይል ጎን ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል።

በአዲሱ አዶላ (ሀዋሳ)
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የተመራ ልዑክ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ እንቅስቃሴን ተመለከቱ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩአን፣ የቻይና የካውስል ሚኒስትር ሚስተር ያንግ እንዲሁም የሲሲሲሲ ( CCCC ) ኢትዮጵያ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል።

ልዑኩን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፊሊሞን ተረፈ እና የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች ልዑኩን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን የቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ( CCCC ) በፓርኩ እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ፕሮጀክቱ በፓርኩ ስለሚያከናውናቸው ስራዎችም ውይይት ተካሂዷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን ተከትሎ የቻይና ባለሀብቶች በፓርኩ በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ለአምባሳደር ዣኦ ዥዩአን ጥሪ ቀርቧል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ስራ ለመመለስ በአመራሮች የታገዘ ቡድን በማቋቋም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው ሲል ኮርፓሬሽኑ ዘግቧል።