Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የተመራ ልዑክ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ እንቅስቃሴን ተመለከቱ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩአን፣ የቻይና የካውስል ሚኒስትር ሚስተር ያንግ እንዲሁም የሲሲሲሲ ( CCCC ) ኢትዮጵያ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል።

ልዑኩን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፊሊሞን ተረፈ እና የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች ልዑኩን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን የቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ( CCCC ) በፓርኩ እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ፕሮጀክቱ በፓርኩ ስለሚያከናውናቸው ስራዎችም ውይይት ተካሂዷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን ተከትሎ የቻይና ባለሀብቶች በፓርኩ በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ለአምባሳደር ዣኦ ዥዩአን ጥሪ ቀርቧል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ስራ ለመመለስ በአመራሮች የታገዘ ቡድን በማቋቋም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው ሲል ኮርፓሬሽኑ ዘግቧል።
በዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስቴር የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረገ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስቴር ኒጌል ሀድልስቶን የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አደረገ።

የልዑካን ቡድኑ በቀጣይ የዩናይትድ ኪንግደም ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓርኮች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ በኢንቨስትመንት በሚሰማሩበት ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይ መስራት በሚችሉባቸው አንኳር ጉዳዮች ላይ ስምምነት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከአጎዋ እግድ ጋር ተያይዞ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በኢንቨስትመንት ለተሰማሩ አለም አቀፍ አምራቾች ሰፊ የገበያ መዳረሻዎችን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ከዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስቴር ጋር ዛሬ የሚያደርገው ስምምነትም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ከታሪፍ ነፃ ገበያ እንዲያገኙ የሚያስችል ነውም ብሏል።
ለምርት ዘመኑ የሚያሰፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)

በ2015/16 ምርት ዘመን የሚውል 12 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ የማጓኀጓዝ ስራ እየተሰራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እስከ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም ድረስ ከሰባት ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ስድስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ሙሉ በሙሉ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው፡፡

የማጓጓዝ ስራው በመኪና እና በባቡር በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን አዳማ ካለው ባቡሩ ጣቢያ እንደደረሰ ወደ ኦሮሚያ፣ አማራና የሲዳማ ክልሎች ሲጓጓዝ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በክልሎች ያሉ የተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት የማጓጓዝ ስራውን በትኩረት እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡

በቀጣይም ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ እና አርብቶ አደሮች ለማቅረብ ግብርና ሚኒስቴር በትኩረት ይሰራል ብሏል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተ.መ.ድ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተ.መ.ድ ዋና ፀሀፊ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ እና የተ.መ.ድ በሶማሊያ የእርዳታ ተልዕኮ ኃላፊ የሆኑትን ካትሮኒያ ላንግን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቸውም አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም ሌሎች የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ አምባሳደር ምስጋኑ በቅርብ ለተሾሙት ልዩ መልዕክተኛ የተሳካ የስራ እንቅስቃሴን ተመኝተው ሰላምን በማምጣት ረገድ የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ አበክራ እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሰላም እና ፀጥታው ረገድ እያበረከተች ላለችው ጉልህ አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን የገለጹት ልዩ መልዕክተኛዋ፤ በቀጣይም በትብብር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የክልሎች ትምህርት ተቋማት ደረጃ ዝቅተኛነት ለትምህርት ጥራት ተግዳሮት ሆኗል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በክልሎች ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ የትምህርት ተቋማት የጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛ መሆን የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተግዳሮት ነው ሲሉ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ገለጹ።

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ከሚገኙ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ የሚሆኑት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102964
በጎነት የዳበሳቸው ደሳሳ ጎጆዎች
************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአብራካቸው ክፋይ የሆኑትን አራት ልጆቻቸውን ለማስተዳደር የጽዳት ስራ እየሰሩ የዕለት ጉርሳቸውን ለማሟላት ከህይወት ጋር ግብግብ የገጠሙ ሴት ናቸው፤ ወይዘሮ መሰረት ጉተማ።

በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ የስድስት ኪሎ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መሰረት፤ ሌት ተቀን ከህይወት ጋር ግብግብ እየገጠሙ የዕለት ጉርስ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102944
«በፉክክር ሳይሆን በትብብር ላይ የተመሰረተ የፌዴራል ሥርዓት መገንባት ያስፈልጋል»
- አቶ አገኘው ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በፉክክር ሳይሆን በትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። ክልሎች የሚያወጧቸው ህጎች ለክልላቸው ካለው ጠቀሜታ አንጻር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ክልሎች ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖም ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ ትናንት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ሲካሄድ ንግግር ያደረጉት አፈ ጉባኤው አቶ አገኘሁ ተሻገር፤ የውይይቱ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102947
በኢትዮጵያ ከ23 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሕፃናት ለአስከፊ ጉልበት ብዝበዛ ተዳርገዋል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ከ23 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሕፃናት ለአስከፊ ጉልበት ብዝበዛ መዳረጋቸውን የአዲስ አበባ ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንዱስትሪ ሰላም ዳይሬክተር አቶ ካሳ ስዩም እንዳስታወቁት፤ በኢትዮጵያ ብዙ ሕፃናት ጎጂና ከባድ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102973
(ፎቶ ከኢንተርኔት)