Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተ.መ.ድ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተ.መ.ድ ዋና ፀሀፊ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ እና የተ.መ.ድ በሶማሊያ የእርዳታ ተልዕኮ ኃላፊ የሆኑትን ካትሮኒያ ላንግን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቸውም አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ደህንነት እንዲሁም ሌሎች የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ አምባሳደር ምስጋኑ በቅርብ ለተሾሙት ልዩ መልዕክተኛ የተሳካ የስራ እንቅስቃሴን ተመኝተው ሰላምን በማምጣት ረገድ የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ አበክራ እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በሰላም እና ፀጥታው ረገድ እያበረከተች ላለችው ጉልህ አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን የገለጹት ልዩ መልዕክተኛዋ፤ በቀጣይም በትብብር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የክልሎች ትምህርት ተቋማት ደረጃ ዝቅተኛነት ለትምህርት ጥራት ተግዳሮት ሆኗል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በክልሎች ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ የትምህርት ተቋማት የጥራት ደረጃቸው ዝቅተኛ መሆን የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተግዳሮት ነው ሲሉ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ገለጹ።

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ከሚገኙ የትምህርት ተቋማት ውስጥ አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ የሚሆኑት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102964
በጎነት የዳበሳቸው ደሳሳ ጎጆዎች
************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአብራካቸው ክፋይ የሆኑትን አራት ልጆቻቸውን ለማስተዳደር የጽዳት ስራ እየሰሩ የዕለት ጉርሳቸውን ለማሟላት ከህይወት ጋር ግብግብ የገጠሙ ሴት ናቸው፤ ወይዘሮ መሰረት ጉተማ።

በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ የስድስት ኪሎ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መሰረት፤ ሌት ተቀን ከህይወት ጋር ግብግብ እየገጠሙ የዕለት ጉርስ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102944
«በፉክክር ሳይሆን በትብብር ላይ የተመሰረተ የፌዴራል ሥርዓት መገንባት ያስፈልጋል»
- አቶ አገኘው ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በፉክክር ሳይሆን በትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። ክልሎች የሚያወጧቸው ህጎች ለክልላቸው ካለው ጠቀሜታ አንጻር ብቻ ሳይሆን ሌሎች ክልሎች ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖም ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች የጋራ የምክክር መድረክ ትናንት በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ሲካሄድ ንግግር ያደረጉት አፈ ጉባኤው አቶ አገኘሁ ተሻገር፤ የውይይቱ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102947
በኢትዮጵያ ከ23 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሕፃናት ለአስከፊ ጉልበት ብዝበዛ ተዳርገዋል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ከ23 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሕፃናት ለአስከፊ ጉልበት ብዝበዛ መዳረጋቸውን የአዲስ አበባ ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የኢንዱስትሪ ሰላም ዳይሬክተር አቶ ካሳ ስዩም እንዳስታወቁት፤ በኢትዮጵያ ብዙ ሕፃናት ጎጂና ከባድ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102973
(ፎቶ ከኢንተርኔት)
የኤሌክትሮኒክስ ግዢ ሥርዓት የጀመሩ ተቋማት ግብይታቸውን በሚያዝያ ወር አጠናቀዋል
************
(ኢ.ፕ.ድ)

- ከ10 ሺህ በላይ አቅራቢዎች በሥርዓቱ ተመዝግበዋል

የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓትን መጠቀም የጀመሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግዥዎችን በሚያዝያ ወር ማጠናቀቃቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ።

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሲስተም ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ታደሰ ከበደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ወደ ሲስተም የገቡት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102979
ከ56 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ ሆነዋል
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ከ56 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማህበረሰብ የጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ሰሞኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና መድህን ተደራሽነትና የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ላይ እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ ከ56 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የማህበረሰብ ጤና መድህን ሽፋን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። ከእነዚህም ....
ሙሉውን ለማንበ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102997
በትግራይ የሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችላቸው ቁመና ላይ ደርሰዋል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል የሚገኙት አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች በአሁኑ ወቅት ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችላቸው ቁመና ላይ መድረሳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ሥራ መግባታቸው አንዱ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102976