በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ባለሀብቶች ወደ እንግሊዝ ሀገር ከታሪፍ ነፃ ገበያ ምርቶቻቸውን ሊያቀርቡ ነው
**************
(ኢፕ.ድ)
የታዳጊ ሀገራት አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ ምርቶቻቸውን ከታሪፍ ነፃ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የመክፈቻ መርሃ ግብር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስቴር ናይጄል ሀድልስተን የታዳጊ ሀገራት ነፃ የንግድ ፕሮግራም በ65 የዓለም ሀገራትና በ37 የአፍሪካ ሀገራት የሚጀመር መሆኑን ገልፀው በኢትዮጵያ በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም በሌሎች የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ምርት የተሰማሩ አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ ላይ ምርቶቻቸውን በነፃ እንዲያቀርቡ ያግዛል ብለዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው ሂደቱ እየተስተዋለ ያለውን የተዛባ የዓለም አቀፍ የንግድ ምጣኔና ስርዓት በመረዳት ፍትሀዊና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሰፍን ፤ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ የማበረታቻ ማዕቀፍ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በ2030 የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 85 በመቶ በማሳደግ ከአምራች ኢንዲስትሪው ዘርፍ 5 ሚሊየን የስራ እድል እና 9 ቢሊየን ዶላር ለማሳካት አቅዶ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲተገብር ቆይቷል ያሉት አቶ ሀሰን ባለፉት ተከታታይ አመታት የCOVID , AGOA እና የሩስያና ዩክሬን ጦርነት እና በሌሎች ምክንያቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ የአብዛኛው ሀገር ኢንዱስትሪ የመቀዝቀዝ አዝማሚያ አሳይቷል።
መንግስት ግን ኢትዮጵያ ታምርት የሚል ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ አብዮት በመፍጠር አለማቀፍ ጫናን መቋቋም የሚችል አምራች ኢንዱስትሪ በመገንባት ላይ ነው ብለዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፣የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሌሊሴ ነሜ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ ተዋናዮች ተገኝተዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል መልዕክት‼️
በቴክኒክና ሞያ ስልጠና ዘርፍ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለንን አጋርነት እና ትብብር ለማጠናከር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ያለመ የሥራ ጉብኝት በጀርመን ሙኒክ፡፡
በቆይታችን ከኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የማህበራት ተወካዮች ጋር በሰው ሃይል ልማት እና ጀርመን በምትታወቅበት የሁለትዮሽ የትብብር ሥልጠና አስፈላጊነት ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡
በሀገራችን በክህሎት ልማት ዘርፍ ትልቅ ሚና ያለው የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ከሙኒክ ቴክኒክኒካል ዩኒቨርሲቲ ጋር መስራት የሚችልበት ሁኔታ ላይ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር መክረናል፡፡ ይህ የትብብር ማዕቀፍ በሁለትዮሽ የትብብር ሥልጠና፣ በጥናትና ምርምር፣ በኢኖቬሽን ፣ የግሉን ሴክተር ተሳትፎ በማሳደግ እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ሲሆን ትብብሩ እንደ ሀገር በክህሎት ልማት ዘርፍ የጀመርነው የሪፎርም ሥራ ውጤታማነት ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት !

ከሐምሌ ወር ጀምሮ 169 የፌደራል ተቋማት ግዥዎቻቸውን በኤሌክትርኒክስ ስርዓት ይፈፅማሉ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ 169 የሚሆኑ የፌዴራል የመንግስት ተቋማት ግዥዎቻቸውን በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት እንደሚፈጽሙ ተገለፀ።
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ከአቅራቢና ከአቅራቢ ማህበራት ጋር በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርአት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ ባደረጉት ንግግር፤ 169 የፌዴራል የመንግስት ተቋማት ከመጪው የሐምሌ ወር ጀምረው የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሰርአትን ይከተላሉ ብለዋል።
ባለፋት አስር ወራት 70 የፌዴራል የመንግስት ተቋማትና 10 ሺህ በላይ አቅራቢዎች በኤሌክትሮኒክስ ግዥ መፈፅመቸውን ጠቁመው በኤሌክትሮኒክስ ግዥ መፈፀማቸው ከ5 እሰከ 25 በመቶ የሚሆነውን የመንግስት በጀት ወጪ ማስቀረት ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ከመንግስት ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነው በጀት ለግዥ የሚውል በመሆኑ በጀቱ ለታለመለት አላማ እንዲውል በኤሌክትሮኒክስ ግዥ መፈጸም አስፈላጊ ነው ብለዋል።
አንድ የመንግስት ተቋም ከወረቀት ወደ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በመግባት ማንኘውንም ግዥ ሲፈፅም የበጀቱን 5 እሰከ 25 በመቶ ያተርፋል፤ በቀላሉ 5 በመቶ የሚሆን ወጪን ቢቆጠብ 40 ሚልየን ብር ቆጠበ ማለት ነው፤ ይህ ደግሞ ለመንግስት ዓመታዊ በጀት ትልቅ ድጋፍ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
የክልል የመንግሰት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ከወረቀት የግዥ ሰርአት በማላቀቅ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሰርአትን እንዲከተሉ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፤ በ2017 ዓ.ም ሁሉም ተቋማት ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርአትን ተከትለው ግዥ እንደሚፈጽሙ አሳውቀዋል።
የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሰርአት ብልሹ የግዥ ሰርአትን በመቅረፍ የመንግስት በጀት በታለመለት አገልግሎት እንዲውል በማድረግ የሀገርን ስልጣኔ ያመጣል ሲሉ ገልፀዋል።
ከፌዴራል የመንግስት ተቋማት በተሻለ የግል አቅራቢዎች የግዥ ሰርአቱ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ነው ያሉት ዋና ዳሬክተሩ፤ ተሳትፏችሁን በማጠናከር ሌብነትን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይገባናል ሲሉም አመላክተዋል።
በታደሰ ብናልፈው

የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን የተመለከተ ሀገራዊ ሪፖርት ይፋ ተደርጓል
****************
ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን በሚመለከት በጥናት ላይ የተመሰረተ ሪፖርት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አቅርቧል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ እንደገለፁት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ ከተቋቋመበት ዓላማ አንፃር በሀገራችን የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ሀገራዊ ሪፓርት ያቀርባል።
በመሆኑም ሪፖርቱ ባለፈው አንድ ዓመት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ምን መልክ ነበረው የሚለውን ያካተተ ሲሆን ለውይይት ቀርቦ የመፍትሄ ሃሳቦችንና አቅጣጫዎችን ለመውሰድ ያለመ ነው።
አቶ ዮናታን አክለውም የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን የመከላከል ስራ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ሁሉም ዜጎችና የተለያዩ ተቋማትንም የሚመለከት በመሆኑ ሁላችንም ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙት ባለድርሻ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ ስለሚሰራጭ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ አሁናዊ ሪፖርት ላይ በቂ ግንዛቤ አግኝተው ድርጊቱን ከመከላከል ረገድ በቂ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የጣሪያ እና ግድግዳ ግብርን ምክንያት በማድረግ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ “ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ደርሰንበታል” ብሏል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑንም አስታውሷል::
በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል ከከከተማ አስተዳደሩ የተገኘው መረጃ አያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በንግድና ኢንቨስትመንት ዙርያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስትር አቶ ናይጄል ሆድልስተን ጋር በመወያየት በንግድና ኢንቨስትመንት ዙርያ አብሮ ለመስራት የሚስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ስምምነቱ በዋናነት ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ዝግጅት በፋይናስና በቴክኒክ ለማገዝ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እስካሁን የአለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ረጅም ጉዞ መጓዟን ያነሱት ሚኒስትሩ ይህን ብቻውን ግብ ባለመሆኑ አለም አቀፍ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኝት ይገባል ብለዋል፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስትር አቶ ናይጄል ሆድልስተን በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ እንደ ሰፊ የሰው ሀብትና የቆዳ ስፋት ባለቤትነቷ ከአፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ ይዛ እስካሁን በአለም የንግድ ድርጅ ውስጥ አባል ለመሆን መዘግየቷ ተገቢ ባለመሆኑ ይህንን ለማሻል በዩናይትድ ኪንግደም በኩል ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው ይበልጥ ተጠቃሚ እድትሆን ለማድረግና የንግድ ሚዛኑን ለማሻሻል በሚቻልበቻው ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጋራ ለመስራትና ለመደገፍ የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም መናገራቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከ ሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት አስራ አንድ ወራት ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰበሰብ አቅዶ ባከናወናቸው ስራዎች ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መለሰ ኪዊ ገልፀዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ከቀጥተኛ ታክስ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ የታክስ አይነቶች 726 ሚሊዮን፣ ታክስ ካልሆኑ 161 ሚሊዮን እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 170 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም አቶ መለሰ አስታውቀዋል።
የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ942 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ለተመዘገበው የአፈጻጸም መሻሻል አስተዋጽዖ ያበረከቱ በየደረጃው የሚገኙ ግብር ከፋዮችን እንድሁም ግብር ሰብሳቢ ተቋማትና ባለሙያዎችን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መለሰ ኪዊ አመስግነዋል።
በቀጣዩ የ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰበሰብ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ያለደረሰኝ የሚከናወኑ ክፍያዎችንና በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ባለስጣን መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
የግብር አሰባሰብ ሂደቱን ዘመናዊ ለማድረግ ቴሌብርን እና ሌሎች የዲጅታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንሰራለን ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከእነተሽከርካሪዎቹ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።
የተለያዩ አልባሳት ቦንዳ፣ ሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዓይነት ሲጋራዎች እና ህገ-ወጥ መድሀኒቶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መነሻቸውን ከጂቡቲ አድርገው አዲስ አበባ ከተማ ሊገቡ ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በጋራ ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ከነ-ተሽከርካሪዎቹ መያዛቸው ታውቋል።
በወንጀሉ የተሳተፋ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሆነ ተገልጿል።
የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን በደረሰኝ ገቢ መደረጋቸው ተጠቅሷል።
የፀጥታ ተቋማቱ በኮንትሮባንድ ላይ እያደረጉ ያሉትን የተቀናጀ ኦፕሬሽንና ክትትል አጠናክረው መቀጠላቸውን እየገለጹ ኅብረተሰቡ እስከአሁን ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።