Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መልካም ዕድል🙏
በአዲስ አበባ የክረምት ትራፊክ በጎፍቃድ አገልግሎት የሚያስተባብሩ አምስት ሺህ በጎ ፍቃደኞች የስራ ስምሪት ወሰዱ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክረምት ትራፊክ በጎፍቃድ አገልግሎት የሚያስተባብሩ አምስት ሺህ በጎ ፍቃደኞች ዛሬ የስራ ስምሪት ወሰዱ።

የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ዛሬ ስምሪቱን የሰጠ ሲሆን፤ 5ሺህ በጎፍቃደኞች በክረምት የትራፊክ በጎ ፍቃድ ተግባር የሚያስተባብሩ ሲሆን፣ በስምሪት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተሳተፉ በጎ ፍቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሂደዋል።

ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
በዋና ዋና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች የተናበቡ ሊሆኑ ይገባል ተባለ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በአስተማማኝ መሰረት ላይ ለመገንባትና በዋና ዋና ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለመፍጠር የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች የተናበቡ ሊሆኑ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ከበደ ደሲሳ ለሁለት ቀናት በአዳማ ሲካሄድ የነበረው የፌዴራል እና የክልል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዓመታዊ የጋራ መድረክ ማጠቃለያ ላይ እንደተናሩት የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ሥራዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ በቅንጅት፣ በመናነብና በመደማመጥ ሙያዊ ስነ ምግባርን በጠበቀ መልኩ ሊሰሩ ይገባል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት በፌዴራልና በክልል ያሉ የኮሙኒኬሽን ተቋማት አደረጃጀቶችና የአሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ የተገሩት ሚኒስትር ዲኤታው፤ ባለሙያውም የመዋቅርና አሰራር ጉድለቶች እንኳን ቢኖሩ ለሕብረተሰቡ ተገቢውን መረጃ በመስጠት ሃገራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በቀጣይ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው የተናገሩት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው በቀጣይ ሁሉም የፌዴራል እና የክልል ኮሙኒኬሽን መዋቅሮች በሁነት ካላንደር ሥራዎቻቸውን ሊመሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ስትራቴጂክ እቅድ ከፌዴራል እቅድ እና ከሃገሪቱ የአስር ዓመት እቅድ ጋር መናበብ እንዳለበት ሚኒስትር ዴኤታዋ አንስተው የፌዴራል ተቋማት ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎች፣ ከዞንና ወረዳዎች ጋር የተናበበ እቅድ እና የሪፖርት ስርአት ሊኖራቸው ይገባልም ብለዋል፡፡

በክልሎች እንዲሁም በፌዴራል ተቋማት መካከል የልምድ ልውውጦች እንደሚኖሩ ሚኒስትር ዲኤታዋ ጠቅሰው የኮሙኒኬሽን አመራጮች በርካታ በመሆናቸው ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም በተለይም ተቋማዊ የኮሙኒኬሽን ተግባቦትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

ሁለተኛው ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ትግበራ በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሥራ ሊታገዝ እንዲገባም በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ለሁለት ቀናት የተካሄደው የጋራ ጉባኤ የአገልግሎቱን የ2015 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሥራዎች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ በመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
"የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገው ንቅናቄ ተወዳዳሪ አገር የመገንባት ሂደት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊሳተፍ ይገባል"
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
**
(ኢ.ፕ.ድ)

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገው ንቅናቄ ተወዳዳሪ አገር የመገንባት ሂደት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊሳተፍ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገር አቀፉን የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ ንቅናቄ መርሃ-ግብር በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግርም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገው ንቅናቄ በዋነኝነት ህብረተሰቡንና የቀድሞ ተማሪዎችን የሚያሳትፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገው ንቅናቄ ተወዳዳሪ አገር የመገንባት ሂደት በመሆኑ የዜጎችን ጠንካራ ትብብርና ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

በንቅናቄው በመላ ኢትዮጵያ ያሉ ከ50 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ በዛሬው እለትም ንቅናቄውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

በንቅናቄው የኀብረተሰቡን ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት በማሰባሰብ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል።
ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

በየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ የተማራችሁ ሁሉ ትናንት የተማራችሁባቸው ትምህርት ቤቶች ዛሬ የናንተን ድጋፍ ይሻሉ።

ድጋፋችንን በተግባር ለማሳየት ሁላችንም በሐሳብ፣በገንዘብ፣በጉልበት እንዲሁም ያለንን ሁሉ ለትምህርት ቤቶች ለማዋል የሚያስችለንን "ትምህርት ለትውልድ" ሀገራዊ ንቅናቄ አስጀምረናል።

የላቀች ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ ቀድመን የላቁ ትምህርት ቤቶችን አብረን እንገንባ!
የባህር ኃይል መልሶ መቋቋም ብቁ የመከላከያ ሠራዊት ቁመና እንዲኖር የሚያስችል ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
እንደ ሀገር የባህር ኃይል መልሶ መቋቋም ብቁ የመከላከያ ሠራዊት ቁመና እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን የቀድሞው የባህር ኃይል አባላት ገለጹ፡፡ የባህር ኃይል በባህር በኩል ኢትዮጵያን ሊያጠቃ ቢመጣ የናቫል ቤዝ ከጎረቤት ሀገር አግኝቶ ጠላትን መመከት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

የቀድሞው የባህር ኃይል አባል ፒቲ ኦፊሰር ወንድወሰን አሰፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የባህር ኃይል መልሶ መቋቋም ዳግም ትንሳኤውን ያሳየ ነው፡፡ እንደ ቀድሞ የባህር ኃይል አባል ፈርሶ የነበረ የባህር ኃይል በህይወት ዘመናችን መልሶ ተደራጅቶ ማየት አስደሳች ነው፡፡እንደ ሀገር የባህር ኃይል መልሶ መቋቋሙም ብቁ የመከላከያ ሠራዊት ቁመና እንዲኖር የሚያስችል ነው፡፡

ልምዳችንን በመጠቀም አሁን ባህር ኃይሉን ለሚቀላቀሉ ወጣት ባህረኞች በማሰልጠኛ ተቋሙ ለሰልጣኖች ስለ ሀገር ፍቅር ስሜት፣ ስለባህር በርና መርከበኝነት ምንነት ላይ ገለጻ በማድረግ ሙያዊ ድጋፍ እናደርጋለን ያሉት የቀድሞ አባሉ፤ አንዳንድ ሰዎች ባህር በር በሌለበት የባህር ኃይሉ መቋቋም አስፈላጊ ነወይ የሚል.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=103986
ከንቲባ አዳንች አቤቤ በአቃቂ ቃሊቲ እየተገነቡ ያሉ 5ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶች የግንባታ ሂደት ጎበኙ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቃቂ ቃሊቲ እየተገነቡ ያሉ አምስት ሺህ ተገጣጣሚ ቤቶች የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል። እየተገነቡ ካሉት ቤቶች አራት መቶ የሚሆኑት በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት ይተላለፋሉ ተብሏል።

ከንቲባዋ እየጨመረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በተለያዩ አማራጮች የቤት ግንባታ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ከንቲባዋ በዛሬእ እለት 54 ማህበር ያሉት አራት ሺ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የሚያስችል የቤት ግንባታ ያስጀመሩ ሲሆን በአቃዊ ቃሊቲ አምስት ሺ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በቅርብም አራት መቶ ቤቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ የከተማው ነዋሪዎች በእጣ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል።