Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ለሚዲያ ተባባሪና መረጃ ሰጪ በመሆን ሐሰተኛ መረጃን መመከት ያስፈልጋል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ለሚዲያ ተባባሪና መረጃ ሰጪ በመሆን ሐሰተኛ መረጃን መመከት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለጸ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እንድሪስ እንደገለጹት፤ ሁሉም የኮሙኒኬሽን መዋቅሮችና መረጃ በእጃቸው ያለ የመንግሥት አካላት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለሚዲያ ተባባሪና መረጃ ሰጪ በመሆን ሐሰተኛ መረጃን መመከት ያስፈልጋል።

እንደ አቶ መሐመድ ገለጻ፤ ከዲጂታል ሚዲያው ጋር ተያይዞ የመጣውን የሐሰተኛ መረጃ መመከት የሚቻለው ትክክለኛውን መረጃ ለማኅበረሰቡ ማቅረብ ሲቻል ነው።

ዘመኑ መረጃን ለሚዲያ ክፍት የሚደረግበትና ሕዝብ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104203
በአዲስ አበባ ከተማ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ182 የመፈተ ኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀመረ
***************************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የ2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዛሬው እለት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

ዘንድሮ በከተማ አስተዳደር በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75 ሺህ 090 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊው ከአቶ አሊ ከማል እና ከየካ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ፈይሳ ወዳጆ ጋር በክፍለከተማው በሚገኙ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የፈተናውን አጀማመር ተመልክተዋል።

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዘንድሮ እንደመጀመሩና ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በእድሜ አነስተኛ እንደመሆናቸው ቢሮው ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሲሰራ ቆይቷል።

በከተማ አስተዳደሩ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን ተጠናቋል።

የ6ኛ ክፍል ፈተናም በተመሳሳይ ሁኔታ ያልምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፈተና አስፈጻሚ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ዛሬ በይፋ ይመረቃል
******************
(ኢ ፕ ድ)

በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ የተገነባው አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ይመረቃል። ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተቋሙ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል።

ሰሞኑን የምረቃው አካል የሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል።

በተራራ የተከበበውና በእጽዋት ያጌጠው አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ዓለም በደረሰበት የሚዲያ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።

ለሚዲያው ሠራተኞች ምቹ የሥራ ከባቢን በመፍጠር ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲያድግ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ኢቢሲ "ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል በአዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክሱ በሁሉም ሚዲየሞቹ አዳዲስ ይዘቶችን እና አቀራረቦችን አካቶ ወደ አድማጭ ተመልካች ለመድረስ ዝግጅቱን አጠናቋል።

ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም