Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአዲስ አበባ ስታዲየም በመጪው ዓመት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ይጀምራል
******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ስታዲየም በመጪው ዓመት መጀመሪያ ወራት ጀምሮ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ገለፁ።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና የተቋሙ ባለሙያዎች ስታዲየሙ ያለበትን የጥገና ደረጃ ጎብኝተዋል።

አቶ ቀጀላ መርዳሳ በዚሁ ወቅት የስታዲየሙ ሁለተኛ ምዕራፍ የእድሳት ስራ ከተጀመረ አራት ወራት አካባቢ መሆኑንና ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ላይ የተመልካች መቀመጫ ወንበር፣ የኤሌክትሪክና የውሃ መስመር ስራዎችና የመጸዳጃ ቤቶች ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት አብዛኛውን ስራ በማጠናቀቅ በመጪው ዓመት መጀመሪያ ወራት ጀምሮ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ይጀምራል ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራ ሁለተኛ ምዕራፍ 65 በመቶ መድረሱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ስታዲየሙ መጀመሪያ ጥገና ለማድረግ ታስቦ እንደነበር አስታውሰው የተሻለ ለማድረግ ወደ እድሳት ማደጉ ተገልጿል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የስታዲየሙን ትራክ የማንጠፍ ስራ ደግሞ በቀጣይ ተጨማሪ በጀት ተይዞለት የሚከናወን መሆኑም አስታውቀዋል።
ሰኔ 29ቀን 2015 ዓ.ም
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከማልዲቭስና ጋምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከማልዲቭስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አህመድ ካሌል እና የጋምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ፀሐፊ ሃቢብ ጃራ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱን ያደረጉት በአዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ነው።

ውይይቶቹ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና የባለ ብዙ ወገን ትብብራቸውን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከዚህ ቀደም ከናም ጉባኤ ጎን ለጎን ከካዛኪስታን፣ ሱዳን፣ ኳታር፣ ቬትናም እና ኔፓል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

አምባሳደር ምስጋኑ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም አቀፋዊ አጋርነት እና ትብብርን ለማጠናከር የፖለቲካ ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ መስራች አባል እንደ መሆኗ የወደፊት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል መርህ ላይ ያተኮረ እና ውጤታማ የባለ ብዙ ወገን ተሳትፎ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሰታውቋል።

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም
በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ እንደሚጥል ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ
***********************
(ኢ ፕ ድ)

በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ስፍራዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ ከመደበኛ በላይ ነጎድጓዳማና በረዶ የቀላቀለ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ እንደሚጥል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው የትንበያ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የሃምሌ ወር የመጀመሪያው አስር ቀናት ሁሉንም የክረምት ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104268
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የፖለቲካ ምክክር አደረጉ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ፋሪስ ሬዚቨርቨ ጋር በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ፣ በባለብዙ ወገንና በሌሎች የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ፣ በባለብዙ ወገን እና በሌሎች የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳዮች ላይ የተካሄደዉ የጋራ የፖለቲካ ምክክር ዋና ዓላማ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሳደግ፣ የትብብር ዋና ዋና መስኮችን መለየት፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ፣ መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ነው።

አምባሳደር መስጋኑ በመክፈቻ ንግግራቸው የምክክር መድረኩ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነትን ለማጠናከር እና የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጎልበት ምቹ መድረክ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በተጨማሪም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ-ባህላዊ መስኮች እንዲሁም ህዝብ-ለህዝብ ያለውን አጋርነት ማጠናከር ያስችላል ብለዋል።

ክቡር ፋሪስ ሬዚቨርቨ (H.E. Mr. Fariz Rzayev) በበኩላቸው በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን ሪፐብሊክ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር መሰል ምክክር ማድረግና ስምምነቶች መፈራረም ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። አክለዉም የተጀመረዉ ግንኙነት ይበልጥ ይጠናከር ዘንድ በአዘርባጃን ያሉትን እድሎች አጥንቶ ሊያቀርብ የሚችል ቲም ቢላክ የተሻለ ይሆናል ብለዋል።

በተካሄደዉ ዉይይት በፖለቲካ ዘርፍ ምክክሩ ያለንን የሁለትዮሽ ትብብርን የበለጠ የሚያጠናክር እንደሚሆን፣ ባኩ የዓለም ቅርስ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ታሪካዊ ከተሞቻችንን እንዴት አለማቀፋዊ ማድረግ እንደምንችልና ሊኖር ስለሚገባዉ የልምድ ልውውጥ ፣ በቱሪዝም ዘርፍ፣ በታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል (Renewable Energy) ዘርፍ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ጉዳይ፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ያለውን ትብብር እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል እንዲሁም ለአገራችን ተማሪዎች የሚሰጡትን ነጻ የትምህርት ዕድል በቁጥር እና በዓይነት እንዲጨምሩ ማድረግ፣ አዘርባጃን ጠንካራ የውጭ አገልግሎት ተቋም ስላላት በዚህ ዘርፍ በሁለቱም ሀገራት የውጭ አገልግሎት ተቋማት መካከል ትብብር ለማድረግ (MOU) ለመፈራረም ጠቃሚ መሆኑ መግባባት ላይ ተደርሳል።

ከዚህ በተጨማሪ አዘርባጃን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸም ያላትን ሲሆን መልካም ተሞክሮ ልምድ ለማካፈልም ፍቃደኛ ሁነዋል።

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሪፐብሊክ ኦፍ አዘርባጃን መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እኤአ በኖቨምበር ወር 1992 ሲሆን በኢትዮጵያ የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ እኤአ በ2012 ተከፍቷል።
በማዕድን ዘርፉ ለሥራ ዕድል ያለውን አቅም ለመጠቀምና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ምክክር ተካሄደ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የማዕድን ዘርፉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያለውን እምቅ አቅም ከመጠቀም ባለፈ እንደ ሀገር በዘርፉ ክህሎት ያለው ባለሙያ በበቂ ሁኔታ ለማፍራት ከማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ።

ማዕድን ሰፊ የሥራ ዕድል ከሚፈጠርባቸው ዘርፎች መካከል አንዱና ሰፊ የሰለጠነ የሰው ኃይል የሚፈልግ ዘርፍ ነው፡፡ እንደ ሀገር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተቋሞቻችንን ውጤት ለማላቅ ደግሞ ተቀናጅቶ መስራት ቁልፍ ነው፡፡

በሰው ኃብትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና የሙያ ደህንነትንና ጤንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመናል፡፡ በስምምነቱ ማዕቀፍ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን እንቅስቃሴ ለመከታተልና በቀጣይም ቅንጅቱ ፈጣን ውጤት እንዲያመጣ በየጊዜው የምናደርጋቸው ውይይቶች ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በሰው ኃብትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ዙሪያ በመቀናጀት የምናከናውናቸው ተግባራት ላይ ውጤቶቻችንን ለማላቅ ላላቸው ቁርጠኝነት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስም ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
የከተማ አስተዳደሩ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች ችግኝ ተከሉ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሰራተኞች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ከአካባቢ ነዋሪዎች ጋር በመተባበር 10ሺህ ችግኞች ተከሉ።

የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳኛው ገብሩ እንደገለፁት ችግኞችን መትከል የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ደህንነቱ በተረጋገጠ ሀገር ላይ ማኖር ነው።

ተቋሙ በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አገልግሎት ከተጀመረ ጀምሮ ሲተክልና ሲንከባከብ ቆይቷል። አሁንም መትከል ብቻ ሳይሆን የመንከባከብ ስራንም ይሰራሉ ብለዋል

ባለስልጣኑ ከአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በተጨማሪ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይም ተሳትፎ ያደርጋል።

በዳግማዊት ግርማ

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
መልካም ዕድል፣ ሰኔ 30ቀን 2015 ዓ.ም‼️
ኮሚሽኑ በ2015 በጀት ዓመት ለ2 ሺህ 904 ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በ2015 በጀት ዓመት ለ2 ሺህ 904 አዲስ ባላሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከዘርፉ በ2015 ዓ.ም በጀት አመት ለባለሀብቶች ከሰጠው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች 27 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 26 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር አግኝቷል። የዕቅዱን 97 ነጥብ 7 በመቶ ማሳካቱንም አስታውቋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የኮሚሹኑን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጄ በማዘመንና ተገልጋዮች ሀብትና ጊዜያቸውን በመቆጠብ ሳይንገላቱ ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት ተጀምሯል፡፡

የተገልጋዮችን ፍላጎትም መሰረት በማድረግ ለ 2 ሺ 904 አዲስ ፍቃድ፤ ለ464 የኢንቨስትመንት ለውጥ ማሻሻያ ፣ለ1 ሺ 854 ኢንቨስትመንት እድሳት እና ለ 232 ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ፈቃድ እንዲሁም 98 ምትክ ፈቃድ መስጠት መቻሉን ከኮኒሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በኢንቨስትመንት ሥራ ለመሰማራት የማምረቻው ፣ የአገልግሎት ፣ የቱሪዝም ልማት ዘርፎች እንዲሁም የባለኮከብ ሆቴል ፣ ሪል እስቴት ዘርፍና የከተማ ግብርና ዘርፍ ለባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ናቸው።

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም