Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መልካም ዕድል፤ ሐምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም‼️
ፍተሻ ከተደረገባቸው 22 ሺ የትምህርት ማስረጃዎች 10 በመቶዎቹ ሀሰተኛና መስፈርቱን የማያሟሉ ናቸው
*******************
(ኢ ፕ ድ )

በተያዘው ዓመት ፍተሻ ከተደረገባቸው 22ሺ የትምህርት ማስረጃዎች አስር በመቶ የሚደርሱት ሀሰተኛና መስፈርቱን የማያሟሉ መሆናቸውን የኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥርና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቸሩጌታ ገነነ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ በትምህርት ዘርፍ ከሚታዩ ችግሮች አንዱ ነው።ችግሩን ለመቀነስ ባለሥልጣኑ ባደረገው ፍተሻ ከ22ሺ የትምህርት ማስረጃዎች መካከል አስር በመቶ የሚደርሱት ሀሰተኛ አልያም መስፈርቱን የማያሟሉ ናቸው፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=587571430232983&id=100069403920568
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጠናከር እየሠሩ ነው
***********************
(ኢ ፕ ድ )

ረጅም ድንበሮች የሚጋሩት ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ማኅበራዊና ኢኮኖ ሚያዊ ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን የደቡብ ሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ።

የደቡብ ሱዳን ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዳንግ ዳው ማሌክ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፣ ሁለቱ ሀገራት ሰፊ ድንበር ይጋራሉ። ስለሆነም ከመሠረተ ልማት ጋር በተያያዘ አበክረን በጋራ ልንሠራባቸው የሚገቡ ብዙ ጉዳዮች አሉን ብለዋል፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=587576246899168&id=100069403920568
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ ማለዳ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙ የከተማችን ወጣቶች ጋር በመሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የደም ልገሳ አድርገናል። በአዕምሮ እና በአካል የበለፀገ ትውልድ ለማፍራት የጀመርናቸው ስራዎቻችን ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል።

የከተማችን ወጣቶች “በጎነት አያጎድልም” ብለው የበጋ የበጎ ፍቃድ ስራዎቻችን ላይ ከፊት ሆነው በመምራት እና ከበጎ አስተሳሰብ እንዲሁም ከሁሉም መልካም ተግባሮች ጋር በመተባበር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

በዚህ ክረምትም ከበጋው ወቅት በተሻለ መልኩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማችን እንዲስፋፋ አቅመ ደካሞችን እንዲደግፉ፣ የአረጋዊያንን ቤት እንዲያድሱ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራችን ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ከተለያዩ አለም ሀገሮች ከተውጣጡ የሀረሪ ዳያስፖራዎች ጋር ተወያዩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ከተለያዩ አለም ሀገሮች ከተውጣጡ የሀረሪ ዳያስፖራዎች ጋር በካናዳ ቶሮንቶ ተወያይቶዋል።

በውይይቱ ላይም ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት ውይይቱ በርካታ ብዥታዎችን ያጠራንበት እና በዋና ዋና ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነው።

በተለይም ችግሮችን በዲያስፖራው ጋር በቅንጅት በመመፍታት በቀጣይም ዳያስፖራው በክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

ለ25ኛው ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው አለም አቀፍ የሀረሪ ባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉላቸው አካላት ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳደሩ በአሉን አስተባባሪ የሆኑት የካናዳ ሀረሪ ኮሙኒቲ እና የሀረሪ ሄሪቴጅ ሴንተር ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበልና መስተንግዶ የላቀ ምስጋና አቀርበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይም የሀረሪ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፣ የክልሉ ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማእከል ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሊድ አልዋ፣ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስን ጨምሮ በካናዳ እና በአካባቢው የሚኖሩ የሀረሪ ኮሚዩኒቲ ተዉካዮች ተገኝተዋል።
#አረንጓዴ_ዐሻራ‼️

ስለ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ታሪክ እንሥራ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን የ2016 ዓ.ም በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር አፀደቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን የ2016 ዓ.ም በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር አፅድቋል።

የተበጀተው በጀት የከተማዋን የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል።

በታደሰ ብናልፈው

ሐምሌ 2ቀን 2015 ዓ.ም