የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን የ2016 ዓ.ም በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር አፀደቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን የ2016 ዓ.ም በጀት 140 ነጥብ 29 ቢሊየን ብር አፅድቋል።
የተበጀተው በጀት የከተማዋን የልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል።
በታደሰ ብናልፈው
ሐምሌ 2ቀን 2015 ዓ.ም

ጨፌ ኦሮሚያ 5ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የጨፌ ኦሮሚያ 2ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔ በአዳማ ከተማ ገልማ አባ ገዳ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ሲሆን አባ ገዳዎች በምርቃት አስጀምረውታል።
በዛሬው ዕለት በተጀመረው በዚህ ጉባኤ በ2015 ዓ.ም ማለትም በተገባደደው በጀት ዓመት የተከናወኑ አጠቃለይ የክልሉ መንግሥት ሥራዎች እንዲሁም በጨፌው የተከናወኑ አበይት ተግባራት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ለምክር ቤቱ ይቀርባሉ።
የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ የተሰሩ ስራዎች፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና የተሰጡ ምላሾች እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ውይይት የሚደረግባቸው አንኳር ጉዳዮች መሆናቸውን የጨፌው አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰአዳ አብዱራህማን በትላንትናው ዕለት መግለጻቸው ይታወሳል።
እንዲሁም በክልሉ የተሠሩ ሥራዎች፣ መልካም ልምዶች እና ድክመቶች ተለይተው ወይይት ከተደረገባቸው በኋላ ለቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም መግለፃቸው አይዘነጋም።
የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እና የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በቃልኪዳን አሳዬ (አዳማ)

የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የተልእኮ ድጋፍ ስልጠና እየሰጠ ነው
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ከአባል አገራቱ ለተወከሉ ተሳታፊዎ የተቀናጀ የተልእኮ ድጋፍ ስልጠና በአዲስ አበባ እየሰጠ ነው።
የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የውጭ ግንኙነትና ወታዳራዊ ትብብር የውጭ ስልጠና ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶክተር መኮንን አበበ በስልጠናው ማስጀመሪያ እንደተናገሩት፣ በእውቅትና በክህሎት ላይ ተመስርቶ የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ተጠባባቂ ስልጠና አዎንታዊ ሚና ያለው ነው።
በቀጣናው የሚስተዋለውን ግጭት ለመከላከል፣ የህዝብን የሰላም ፍላጐት ለሟሟላትና የምስራቅ አፍሪካን ብልጽግና ለማሳድግ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋ።
ስልጠናው በተለይ ግዳጅን በአግባቡ ለመፈጸም በአቅም ግንባታ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው እንደሆነም ተገልጿል።
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያን፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ቡሩንዲ፣ ኮሞሮስ፣ ሩዋንዳ፣ ሲሼልስ እና ዩጋንዳ የተወጣጡ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
በአዲሱ ገረመው
ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም

የሕፃናት የላንቃና ከንፈር መሰንጠቅ ችግር የመበራከቱን ያህል ሕክምናው አልተዳረሰም
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
- አለርት ሆስፒታል ከ100 በላይ ለሆኑ ሕጻናት ህክምና ሰጥቷል
የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ሕፃናት የመብዛታቸውን ያህል የሕክምናው ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆኑን የአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ሕክምና ባለሙያ ዶክተር አታክልቲ ባራኪ አስታወቁ።
አለርት ሆስፒታል ከ100 በላይ ለሚሆኑ ሕፃናት የላንቃ እና ከንፈር ቀዶ ሕክምና ሰጥቷል።
ዶክተር አታክልቲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 20 ሚሊዮን ብር የወጣበት የሕፃናት የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ የቀዶ ሕክምና መስጫ ማዕከል ካስመረቀ ስድስት ወራት ተቆጥረዋል።
በዚህም ዕድሜያቸው ከሰባት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ባለፉት ስድስት ወራት በማዕከሉ የቀዶ ሕክምና ተደርጎላቸዋል።
በቁጥር ከአንድ መቶ በላይ ሕፃናት በማዕከሉ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላቸዋል ያሉት ዶክተር አታክልቲ፤ በሀገር ደረጃ የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ሕፃናት ቁጥር ከፍተኛ ነው። ነገር ግን የቁጥሩን ያህል ሕክምናውን ተደራሽ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች የሚታዩ ቢሆንም አሁንም በርካታ ሥራዎች ይቀራሉ ብለዋል።
ሕክምናውን ተደራሽ ለማድረግ ሆስፒታሉ ከአጋር አካላት ጋር እየሠራ ነው። በዚህም አጋር አካላት ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ወደ ማዕከሉ ይዘው ይመጣሉ።
በሂደቱም በርካታ ተግዳሮቶች ያጋጥማሉ ያሉት ዶክተር አታክልቲ፤ በአብዛኛው የሕፃናቱ ወላጆች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው መሆኑ እና ስለሕክምናው በቂ ግንዛቤ አለመኖሩ ሕፃናቱ የአመጋገብ እና የመጥባት ችግር እንዲያጋጥማቸው ያደርጋል ብለዋል።
ይህም ችግሩ ያለባቸው ሕፃናት በኢንፌክሽንና ሌሎች መሰል ችግሮች እንዲሰቃዩ እንደሚያደርግ እና ባስ ሲልም ከነዚህ ችግሮች ጋር በተያያዘ አምስት ዓመት ሳይሞላቸው ሕይወታቸው እንደሚያልፍ አስረድተዋል።
የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ችግርን በቀላል ቀዶ ሕክምና በመቅረፍ የሕፃናቱን ሕይወት ማስተካከል ይቻላል ያሉት ዶክተር አታክልቲ፤ ስለዚህ ሕክምናውን ተደራሽ ለማድረግ የአጋር ድርጅቶችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሠራ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ይህን ቀላል ቀዶ ሕክምና ተደራሽ በማድረግ የሕፃናት ሕይወት እንዳይጎዳ፤ የመናገር፣ የመስማትና ሌሎች የሥነ ልቦና ችግሮች እንዳይደርሱባቸው የአለርት ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት የላንቃ እና የከንፈር መሰንጠቅ የቀዶ ሕክምና መስጫ ማዕከል ማቋቋሙን ገልጸዋል።
አሁን ላይ በማዕከሉ የቀዶ ሕክምና የሚደረግላቸው ሁለትና ሦስት ዓመት የሞላቸው ሕፃናት ናቸው ያሉት ባለሙያው፤ ወላጆች በሕክምና ተቋማት እንዲወልዱ በማድረግ ሕፃናቱ ስድስት ወር ሲሞላቸው ሕክምና እንዲደረግላቸው እየተሞከረ ነው። ይህም በልጆች ላይ የሚደርሰውን አካላዊ እና ሥነልቦናዊ ጉዳት ይቀንሳል ሲሉ ገልጸዋል።
በሳሙኤል ወንደሰን
አዲስ ዘመን ሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም

600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ትላንት ወደብ ደርሳለች
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
-እስከ ሐምሌ 23/2015 ድረስ ከሶስት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ተጨማሪ ማዳበሪያ ከውጭ እንደሚጓጓዝ ይጠበቃል
-ከውጭ የተጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ከ10 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ደረሰ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለ2015/16 የሰብል ዘመን ከገዛው 15 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከ ሐምሌ 3/2015 ዓ.ም. ድረስ 10 ሚሊዮን 275 ሺህ 320 ኩንታል ከውጭ መጓጓዙን የግርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን አስታወቀ።
ትላንት ሐምሌ 2/2015 ዓ.ም. 600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷንም አስታውቋል።
ወደብ ከደረሰው አጠቃላይ ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 8 ሚሊዮን 487 ሺህ 429 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደር ዩኒየኖች እየተሰራጨ ይገኛል።
እስከ ሐምሌ 23/2015 ዓ.ም. ድረስ ተጨማሪ 3 ሚሊዮን 685 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ከውጭ እንደሚጓጓዝ ይጠበቃል ተብሏል።
ከዚህ መጠን ውስጥ ሁለት ሚሊዮን 485 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ሲሆን፣ ቀሪው 600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ እና 600 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ናቸው።

"ትምህርት ለትውልድ" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ ንቅናቄ በሀዋሳ ተካሄደ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
"ትምህርት ለትውልድ" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ የትምህርት ተሃድሶ ንቅናቄ መድረክ በሀዋሳ ተካሄደ።
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ የንቅናቄ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ ብቁና ተወዳዳሪ ትዉልድ ለማፍራት ጥራት ያለዉ ትምህርት ለዜጎች ማድረስ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራት ለማስፈን ከአምና ጀምሮ በክልል ደረጃ ንቅናቄ መጀመሩን ያስታወሱት ፕሬዘዳንቱ: ባለፉት ሃያ ቀናት በክልሉ በትምህርት ተሐድሶ የተሰሩ ስራወችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንና ያለቁ ትምህርት ቤቶችን ማስመረቀቸውንም ገልፀዋል።
በዚህም ተስፋ ሰጪ ዉጤቶች መመዝገባቸውን ለመመልከት ችለናል ሲሉም ተናግረዋል።
ባለፈው በጀት አመት አንድ መቶ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 83 ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እንደተመረቁና ቀሪዎቹ በተለያየ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አቶ ደስታ ገልጸዋል።
አብዛኛው የክልሉ ነዋሪ የገጠር አከባቢ ነዋሪ በመሆኑና በገጠሩ አከባቢ የትምህርት ተደራሽነትና የጥራት ዉስንነት በመኖሩ ብቁ ዜጋን በማፍራት በኩል ክፍተቶች እንደነበሩ የተናግረው፣ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተስራ መሆኑን ገልጸዋል።
በአዲሱ አዶላ (ሀዋሳ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢጋድ የሱዳንን ግጭት ለመፍታት ያቋቋመውን የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤን ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ማስተናገዳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል ::