Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በክልሉ ካሉ ትምህርት ቤቶች መስፈርቱን የሚያሟሉት 29ኙ ብቻ ናቸው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካሉ 643 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ተቋምነት መስፈርትን የሚያሟሉት 29ኙ ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ሉሌ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ ጥናት ከተደረገባቸው 643 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተቀመጠውን ደረጃ የሚያሟሉት 29ኙ ብቻ ናቸው።

ትምህርት ቤቶቹ ደረጃ የተቀመጠላቸው ባሟሉት ግብአት፣ በመሠረተ ልማታቸውና ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት ተመዝነው መሆኑን ገልጸው ፤ በዚህም ከ601 የመጀመሪያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 572ቱ ደረጃ የወጣላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ደረጃ ከወጣላቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ 143 ቱ ከ50 በመቶ በታች ውጤት ያላቸው በመሆኑ ደረጃ አንድ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። እነዚህ ትምህርት ቤቶችም ከፍተኛ የሚባል የትምህርት መሠረተ ልማት ችግር ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

403 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ደረጃ ሁለት ላይ የተቀመጡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ደረጃውን ለማሟላት በሂደት ላይ በመሆናቸው መስፈርቱን ከሃምሳ እስከ 70 በመቶ ድረስ አሟልተዋል ነው ያሉት።

አቶ ዮሐንስ አንድ ትምህርት ቤት መስፈርቱን አሟላ የሚባለው ደረጃ ሦስት ላይ ሲደርስ መሆኑን አመልክተው፤ በክልሉም ካሉ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 26ቱ ብቻ ደረጃ ሦስት ላይ መቀመጣቸውን ገልጸዋል። ሆኖም አንድም ትምህርት ቤት ደረጃ 4 ላይ አለመድረሱን አስታውቀዋል።

በክልሉ ካሉ 92 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 73ቱ ደረጃ የወጣላቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ከእነዚህ ውስጥም 15 ትምህርት ቤቶች ደረጃውን ሳያሟሉ ቀርተው ደረጃ አንድ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ዮሐንስ 55 የሚሆኑት ደግሞ ደረጃ ሁለትን ለማሟላት እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን፣ ደረጃቸውን አሟልተው ደረጃ 3 ላይ የተቀመጡት ትምህርት ቤቶች 3 ብቻ ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ደረጃ አራት የገባ ትምህርት ቤት አለመኖሩን ጨምረው ገልጸዋል።

እንደ አቶ ዮሐንስ ገለጻ፤ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች የግብአት ችግር ያለባቸው ናቸው። ይህም የሆነው በፊት የነበረው የትምህርት ሥርዓት ከጥራት ይልቅ ተደራሽነት ላይ ያተኮረ በመሆኑ ነው።

አቶ ዮሐንስ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንደ ሀገር ችግር ያለበት ቢሆንም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ ከፍተኛ ችግር መኖሩን ጠቅሰዋል።

ይህንን ለማስተካከል የክልሉ ትምህርት ቢሮ የራሱን ጥረት እያደረገ ነው። በተጠናው ጥናት መሠረትም በትምህርት ቤቶች የሚፈለገውን መሠረተ ልማት ለማሟላት ማስተካከያ እንዲደረግ ለሚመለከተው አካል ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይ እንደ ሀገር የተጀመረው የትምህርት ቤቶች ደረጃ የማሻሻል ንቅናቄ ለውጥ ያመጣል ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓም
በተያዘው የምርት ዘመን የደቡብ ጎንደር ዞን 50 ሺ ሄክታር መሬት በሩዝ ምርት ይሸፈናል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በተያዘው የምርት ዘመን በደቡብ ጎንደር ዞን ብቻ በተለያዩ ሰብሎች ዘር የሚሸፈን 526 ሺ ሄክታር መሬት ዝግጁ የተደረገ ሲሆን እስካሁን 65 በመቶው በዘር ተሸፍኗል ተባለ።

በዛሬው ዕለት በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ቡራ ቀበሌ የሩዝ ክላስተር ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የአካባቢው አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

ከ 526 ሺ ሄክታር መሬት ውስጥ በተያዘው የምርት ዘመን 50 ሺ ሄክታር መሬት በሩዝ ዘር የመሸፈን እቅድ ተይዞ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ካለፈው የምርት ዘመን ጋር ሲነጻጸርም የዘንድሮው የሩዝ ዘር ሽፋን እድገት ያሳየ መሆኑ ተገልጿል። ባለፈው የምርት ዘመን 42 ሺ ሄክታር መሬት በሩዝ ምርት የተሸፈነ መሆኑም የሚታወስ ነው።

የሩዝ ክላስተር ዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ሌየሰ የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ተፈራ እንደገለጹት በዞኑ የሩዝ ምርት እድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ እድገት እያሳየ ሲሆን በሄክታር 28 ኩንታል ምርት ይገኝ የነበረው በአሁኑ ጊዜ በሄክታር 35 ኩንታል ድረስ መማረት መቻሉን ገልጸዋል።

ባለፋት ዓመታት መንግሥት ለሩዝ ምርት ልዩ ትኩረት በመስጠት ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ማዕከል በአካባቢው በማቋቋም ምርታማነትን የሚያሳድጉና በሽታን የመቋቋም አቅም ያላቸውን ዘር ማሻሻል፣ የአስተራረስና የአዘራር ስልትን ማሳደግ፣ የእሴት መጨመርና የገበያ ትስስርን ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

የሊቦ ከምከም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ፀሐይ ቸኮልም በበኩላቸው የሩዝ ምርታማነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን የሩዝ ምርትን ጥራት በማሳደግና እሴት በመጨመር ለገበያ ለማቅረብ የአቅም ማሳደግ ሥራዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።

ሩዝ ከተመረተ በኋላ አሁን ባለው ገበያ ሳይቀናበር በኪሎ 35 ብር የሚሸጥ ሲሆን ከተቀናበረ በኋላ ደግሞ በኪሎ ከ 75 እስከ 80 ብር ይሸጣል ያሉት ዋና አስተዳዳሪዋ የገበሬውንና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ለማስፋት የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

የዘር አቅርቦትን ማሳደግና የጎርፍ መጥለቅለቅን መከላከልም የሩዝ ምርታማነትን ለመጨመር ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አስተዳዳሪዋ ገልጸዋል።

ሩዝ ማምረት በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ አካባቢ በ1976 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን 38 ዓመታትን አሳልፏል። በአሁኑ ጊዜ ደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የሚገኙት ሩዝ አምራች ወረዳዎች ብቻ የሃገሪቱን 65 በመቶ የሩዝ ምርት በመሸፈን ላይ ይገኛሉ ሲል የክልሉ ኮመንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓም
የአረንጓዴ ዐሻራ ተከላ መርሐ ግብር ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን !!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለተፈናቀሉ ወገኖች 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በትግራይ ክልል በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስታን ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ድጋፉን ዛሬ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ አስረክበዋል።

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ እንዳሉት ድጋፉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው።

“የሃይማኖት መሪዎች ግጭት ሳይሆን ሰላም፣ ውድመት ሳይሆን ልማት ለማረጋገጥ ሃላፊነት አለብን” ያሉት ብፁእነታቸው ወደፊትም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የሃይማኖት መሪዎች ለሰላምና ልማት መረጋገጥ ሚናቸው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የተጀመረው መልካም ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓም
«ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የጤና ሥርዓታችንን ማጠናከር ችለናል»
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኮቪድ ወቅትን መጥፎ ክስተት ወደ ዕድል በመቀየር የጤና ሥርዓቱን ማጠናከር እንደተቻለ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ አስታወቁ። ከኮቪድ በኋላ የጽኑ ሕሙማን ክፍል በእጥፍ አድጓል።

የቢሮ ኃላፊው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኮቪድ 19 ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ዓለምን በከፍተኛ ሁኔታ የፈተነ ወረርሽኝ ነበር። ወረርሽኙ ለኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት ዕድልም ሆኖ አልፏል።

የወረርሽኙን መጥፎ ክስተት እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀምና ወደ ዕድል በመቀየር የጤና ሥርዓቱን ማጠናከር ተችሏል።

ዓለም በወረርሽኙ ሳቢያ በሩን ዘግቶ በመቆየቱ የተለያዩ ግብዓቶችን ለማግኘት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተከስተዋል ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ኮቪድ 19 የዓለም የጤና ችግር ብቻ ሳይሆን፤ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ማስከተሉን፤ ከቫይረሱ ጫና በርካታ የዓለም ኩባንያዎች እስካሁን ማንሰራራት አለመቻላቸውን ገልጸዋል።

ወረርሽኙ ያስከተለው ዓለም አቀፋዊ ቀውስ እንዳለ ሆኖ እንደ ሀገር ዕድል ማምጣቱንም ተናግረዋል።
የቢሮ ኃላፊው፤ «በወረርሽኙ ወቅት ምን ዓይነት የጤና ሥርዓት እንዳለን አይተንበታል። ብዙ ዕድሎች አምጥቶልን አቅማችንን እንድናደራጅ አድርጎናል።

እንደ ከተማም ሆነ እንደ ሀገር በፊት የነበሩንን የጽኑ ሕሙማን ክፍሎች ከእጥፍ በላይ ማሳደግ ችለናል። በቀጣይ እንደ ኮቪድ ዓይነት ወረርሽኝ ሲመጣ ምን ማድረግ እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት ተወስዷል» ብለዋል።

በኮቪድ ወቅት ምን ዓይነት የጤና ሥርዓት እንዳለና መጥፎ ክስተቶችን ወደ ዕድል በመውሰድ የጤና ሥርዓቱን ማጠናከር እንደሚቻል ትልቅ ትምህርት ተወስዷል ነው ያሉት። ከዚህ በኋላ ለሚፈጠሩ የጤና ቀውሶች ምላሽ ለመስጠት ትልቅ አቅም መፈጠሩንም አመልክተዋል።

በወረርሽኙ በርካታ ባለሙያዎች የሕዝብን ጤና ለማቆየት ሕይወታቸውን እንደሰጡ ጠቅሰው፤ ወቅቱ መሰል ክስተቶች ሲመጡ ምን መደረግ እንዳለበት ትልቅ ትምህርት የተገኘበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
እንደ ቢሮ ኃላፊው ገለጻ፤ በቋሚነት ማንኛውም ዓይነት በሽታ ከመከሰቱ በፊት የዳሰሳ ጥናት የሚሠራ ቡድን ከፌዴራል ጀምሮ እስከታችኛው የመንግሥት መዋቅር ያለ ሲሆን፤ ይህ ተጠናክሮ ሥራውን ያስቀጥላል።

ዓለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ፈታኝ የሆኑ ክስተቶች ሲፈጠሩ ጫናው በሀገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን እንደ ዓለምአቀፍ ነው የሚታየው ያሉት ዶክተር ዮሐንስ፤ ኮቪድ 19 በዓለምአቀፍ ደረጃ ያስከተለው ጫና እንደ ኢትዮጵያም ቀላል የማይባል እንደሆነ ጠቅሰዋል። ነገር ግን በሌሎች የዓለም ሀገራት የታየው አስከፊ ሁኔታ በኢትዮጵያ አልነበረም ብለዋል።

ይህም በባለሙያውና በጤና ሴክተሩ ጥንካሬና በመንግሥትም ቁርጠኝነት እንደነበር አስታውቀዋል። በኮቪድ ወቅት ሁሉም ያሳየው ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ነው ዶክተር ዮሐንስ የተናገሩት።

በወቅቱ ከግለሰቦች ጀምሮ የተለያዩ ተቋማት ጭምር የሰጡት በጎ ምላሽ አበረታች እንደነበር ዶክተር ዮሐንስ ጠቅሰው፤ መተባበር በጤናው ሥርዓት ላይ ምን ያህል ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ያየንበት ነው ብለዋል።

በአዲሱ ገረመው

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በባህርዳር ከተማ ያለውን የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴ ተመለከተ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በባህርዳር ከተማ ያለውን የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴ ተመለከተ።

ልዑኩ በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በአለም ባንክ በጀት እየተገነቡ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችንና በግለሠቦች እየተሠሩ ያሉ "የሌማት ቱሩፋት"ስራዎች የሆኑትን የበሬ ማድለብ ፣የዶሮ እርባታ እና እንቁላል ምርት ፣የወተት ልማት ፣የማርና መሰል የእንስሳት ሀብት ልማቶችን ተመልክቷል።

ልዑኩ ሌላው በጉብኝቱ በከተማው ኢንዱስትሪ መንደር ካሉ ፋብርካዎች መካከል የጌታሰው አያሌው ቶፕ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ፣የሻምበል መንገሻ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፣ ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፋብሪካን፣የቢአይካ የግራናይትና እምነ-በረድ ፋብሪካዎችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።

በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችንና የስራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ሰራተኞች የማበረታታት ተግባር ማከናወኑንም ከከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓም