Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ እክል በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል
**
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ርብርብ በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወደ ነበረበት ተመልሷል።

በተቀረው የሀገሪቱ ክፍሎች ያጋጠመውን የኤሌክትሪክ መቋረጥ ችግር ለመፍታት ተቋሙ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለኢቢሲ አስታውቋል።
"የኢትዮጵያና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
******************
(ኢ ፕ ድ)
እየተሻሻለ የመጣው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል::

ውይይታቸው በሁለትዮሽና በወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።

ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ኢጋድ በአዲስ አበባ ያደረገውን ውይይት ኢትዮጵያ በማስተናገዷ አመስግነው የሱዳን ኃይሎች የተኩስ አቁም በማድረግ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ እና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

የሱዳን ሰላም ራሳቸው ሱዳናውያን ባለቤት በሆኑበት በአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ ማዕቀፍ እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ጥረቶች የተደገፈ ሊሆን እንደሚገባው ማመላከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ ም
ሀረር ከተማ የአለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና ተመዘገበች
************
(ኢ.ፕ.ድ)

ሀረር ከተማ ሀረር ከሰሃራ በታች ካሉ ከተሞች የመጀመሪያዋ የአለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት (Organization of World Heritage Cities) አባል ከተማ ሆና ተመዝግባለች።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪም ካናዳ ሀገር ኩቢክ ከተማ በተካሄደው የፊርማ ስነስርዓት ሀረር ከተማ የአለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና የተመዘገበችበት ፊርማ አኑረዋል።

ሀረር ከተማ 115 ሀገራትን በአባልነት በያዘው የቅርስ ከተሞች ድርጅት ከፈረንጆች አቆጣጣር ከሰኔ ወር 2023 ጀምሮ ነው የተመዘገበችው።

ሀረር ከተማ የቅርስ ከተሞች መካከል አንዷ ሆና መመዝገቧ ከተማዋ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን ለማልማት እና ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የቅርስ ከተሞች በጋራ ጉዳዮቻቸው ተመካክረው አቅጣጫ በማስቀመጥ ተግዳሮቶችን ለመሻገርና እድሎችን ለማስፋት እንደሚጠቅም ይታመናል።

ሀረር ከተማ የጁገል አለም አቀፍ ቅርስንን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ አለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ከተማ ከመሆኗ በተጨማሪ ከተማዋ ዜጎች በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚኖሩባት ከተማ በሚል በተባበሩት መንግስት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም ዩኔስኮ እውቅና እንደተሰጣት ይታወሳል።

በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይም የሀረሪ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፣ የክልሉ ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድን ጨምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማእከል ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሊድ አልዋን መገኘታቸውን ከክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች፣ መልካም ዕድል‼️
ትናንት ምሽት በሃገሪቱ በረካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት ተመልሷል
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት ተመልሷል፡፡

ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት የተመለሰው በማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ነው፡፡

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በትግዕስት ለተጠባበቃችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ይታወሳል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
በአማራ ክልል ሦስት ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ 500 ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

👉የመንገድ ሽፋኑን ከ51 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ለማድረስ እየተሠራ ነው
****************************
(ኢ ፕ ድ)

በ2015 በጀት ዓመት ሦስት ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ 500 የመንገድና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቁን የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በ2022 ዓ.ም የክልሉን የመንገድ ሽፋን 51 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በትግሉ ተስፋሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት 541 የመንገድ፣ የድልድይ፣ የዲዛይን እና የተያያዥ ....

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0gYvYG2zBvzBWubFpQvj4LnJghZLH7dgVd5rVqjfGZjCyCG8ZikZBmX6h7umyzz2Kl&id=100069403920568&mibextid=Nif5ozB
የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻል ከወላጅ ተማሪ ህብረትና ከትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል
********************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ ስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከወላጅ ተማሪ ህብረትና ከትምህርት አመራሮች ጋር የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻ "ትምህርት ለትውልድ" በሚል መሪ ሃሳብ ውይይት እያካሄደ ይገኛል

የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ የትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥ ጥራት የተጠበቀ እና ብቁ ዜጋን ማፋራት እንዲችሉ ለማድረግ የሁሉንም ትብብር ይጠይቃል።

በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ላይ ወላጆች፣ የትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በገንዘባቸዉ፣ በእዉቀታቸውና በጉልበታቸው እገዛ በማድረግ የትምህርት ተቋማት ደረጃ እንዲሻሽል ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የትምህርት ተቋማት ምን ችግር አለባቸው፣ ምን ውጤት አስመዘገቡ፣ ችግሮችን የሚፈቱ አካላት እነማን ናቸው የሚሉትን ጉዳዮች በመለየት የትምህርት ተቋማትን ለማሻሻል ሰፊ ንቅናቄ ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የትምህርት ንቅናቄው ከወላጅ ተማሪ ህብረትና ከትምህርት አመራሮች ጋር በአራዳ ክፍለ ከተማ እየተካሄ ሲሆን፤ አርብ በከተማ ደረጃ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በሄለን ወንድምነው

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም