Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ለሁለተኛው ምዕራፍ አረንጓዴ አሻራ ታሪካዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል

👉 ለ500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር ለሚደረገው ተከላ 9ሺህ 500 ቦታዎች ተዘጋጅተዋል፣

👉 ለዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ እስካሁን 6.4 ቢሊዮን የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ተቆፍሯል፣

********
(ኢ ፕ ድ)

በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የሚደረገው መርሐግብር ምን ያህል ችግኝ እንደተተከለ፣ በተከላው የተሳተፈውን የሰው ኃይልና የተሸፈነውን መሬት የሚያሳይ የካርታ ዝግጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መዘጋጀቱን ፕሮፌሰር ኢያሱ ተናግረዋል፡፡

የመጀመሪያውን ምዕራፍ በስኬት በማጠናቀቅ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ የተሸጋገረው የአረንጓዴ አሻራ ልማት የምዕራፉን የመጀመሪያ አመት ስራ በስኬት ለማጠናቀቅ ሰፊ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በዘንድሮው አመት 6.5 ቢሊዮን ችግኝ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ለመትከል ሰፊ ስራ እየተሰራ ሲሆን ይህን ለማሳካት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ ‹500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር› ለመትከል የሚደረገው መርሐግብር ነው፡፡

በዚህ አመት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሰፊ የችግኝ ዝግጅት ከመደረጉ ባለፈ እስካሁን 6.4 ቢሊዮን የችግኝ መትከያ ጉድጓድ መቆፈሩን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ ኤሊያስ/ፕሮፌሰር/ 500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር ለሚደረገው ተከላ 9500 ቦታዎች እንደተዘጋጁና ይህም 361415 ሄክታር መሬት እንደሚሸፍን ተናግረዋል፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ለጥራት፣ ለፍራፍሬና ለአገር በቀል ዝርያዎች ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን 60 በመቶ የጥምር ደን እርሻ፣ 35 በመቶ የፍራፍሬ እንዲሁም 5 በመቶ ለከተማ ውበት የሚሆኑ ዘርፈ ብዙ ችግኞች ናቸው፡፡

በመሆኑም 500 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር እነዚህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚተገበር ይሆናል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የመስራት አቅም ያለው የማህበረሰብ ክፍል በዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ አሻራውን ማስቀመጥ እንዳለበት ፕሮፌሰር ኢያሱ መግለፃቸውን የግብርና ሚኒስትቴር አስታውቋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እየሰጠ ሲሆን በአካባቢ ጥበቃ፣ ኢኮኖሚያዊ ተቀሜታ፣ ስራ እድል ፈጠራና ለአገር ገፅታ ግንባታ የጎላ ድርሻ አበርክቷል፡፡
የለሚ ናሽል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ 65 ከመቶ ደርሷል
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እየተገነባ የሚገኘው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ግንባታ 65 ከመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡

የአማራ ክልል የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ አዲስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የፋብሪካው ግንባታ እየተፋጠነ ነው። አስፈላጊ የሚባሉ ማሽኖችም ከቦታው እየደረሱ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት 3000 ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፤ አንድ ሺህ 500 ቻይናውያን በፋብሪካው ግንባታ ላይ እየተሳተፉና የዕውቀት ሽግግር እየተፈጠረ መሆኑንም አብራርተዋል።

የፋብሪካው ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቆ ምርት እንደሚጀምርም አቶ ያየህ ገልጸዋል።

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ በኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና በቻይናው ዌስት ቻይና የሲሚንቶ አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ሽርክና የተመሰረተ ነው፡፡

ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም
በክፍለዮሐንስ አንበርብር
በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ እክል በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል
**
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ችግሩን ለመፍታት ባደረገው ርብርብ በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወደ ነበረበት ተመልሷል።

በተቀረው የሀገሪቱ ክፍሎች ያጋጠመውን የኤሌክትሪክ መቋረጥ ችግር ለመፍታት ተቋሙ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለኢቢሲ አስታውቋል።
"የኢትዮጵያና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን ይገባል"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
******************
(ኢ ፕ ድ)
እየተሻሻለ የመጣው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል::

ውይይታቸው በሁለትዮሽና በወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።

ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ኢጋድ በአዲስ አበባ ያደረገውን ውይይት ኢትዮጵያ በማስተናገዷ አመስግነው የሱዳን ኃይሎች የተኩስ አቁም በማድረግ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ እና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በበኩላቸው እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

የሱዳን ሰላም ራሳቸው ሱዳናውያን ባለቤት በሆኑበት በአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ ማዕቀፍ እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ጥረቶች የተደገፈ ሊሆን እንደሚገባው ማመላከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ ም
ሀረር ከተማ የአለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና ተመዘገበች
************
(ኢ.ፕ.ድ)

ሀረር ከተማ ሀረር ከሰሃራ በታች ካሉ ከተሞች የመጀመሪያዋ የአለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት (Organization of World Heritage Cities) አባል ከተማ ሆና ተመዝግባለች።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪም ካናዳ ሀገር ኩቢክ ከተማ በተካሄደው የፊርማ ስነስርዓት ሀረር ከተማ የአለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና የተመዘገበችበት ፊርማ አኑረዋል።

ሀረር ከተማ 115 ሀገራትን በአባልነት በያዘው የቅርስ ከተሞች ድርጅት ከፈረንጆች አቆጣጣር ከሰኔ ወር 2023 ጀምሮ ነው የተመዘገበችው።

ሀረር ከተማ የቅርስ ከተሞች መካከል አንዷ ሆና መመዝገቧ ከተማዋ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን ለማልማት እና ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የቅርስ ከተሞች በጋራ ጉዳዮቻቸው ተመካክረው አቅጣጫ በማስቀመጥ ተግዳሮቶችን ለመሻገርና እድሎችን ለማስፋት እንደሚጠቅም ይታመናል።

ሀረር ከተማ የጁገል አለም አቀፍ ቅርስንን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ አለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ከተማ ከመሆኗ በተጨማሪ ከተማዋ ዜጎች በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚኖሩባት ከተማ በሚል በተባበሩት መንግስት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም ዩኔስኮ እውቅና እንደተሰጣት ይታወሳል።

በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይም የሀረሪ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፣ የክልሉ ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድን ጨምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማእከል ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሊድ አልዋን መገኘታቸውን ከክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች፣ መልካም ዕድል‼️
ትናንት ምሽት በሃገሪቱ በረካታ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት ተመልሷል
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት ተመልሷል፡፡

ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት የተመለሰው በማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል በተደረገ ከፍተኛ ጥረት ነው፡፡

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በትግዕስት ለተጠባበቃችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ይታወሳል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
በአማራ ክልል ሦስት ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ 500 ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

👉የመንገድ ሽፋኑን ከ51 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ለማድረስ እየተሠራ ነው
****************************
(ኢ ፕ ድ)

በ2015 በጀት ዓመት ሦስት ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ 500 የመንገድና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቁን የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በ2022 ዓ.ም የክልሉን የመንገድ ሽፋን 51 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በትግሉ ተስፋሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት 541 የመንገድ፣ የድልድይ፣ የዲዛይን እና የተያያዥ ....

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0gYvYG2zBvzBWubFpQvj4LnJghZLH7dgVd5rVqjfGZjCyCG8ZikZBmX6h7umyzz2Kl&id=100069403920568&mibextid=Nif5ozB