Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሸበሌ ባንክ በጅግጅጋ በተከሰተው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ነጋዴዎች 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

ሸበሌ ባንክ በጅግጅጋ ከተማ በገቢያ ማዕከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች ለመደገፍና ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የሸበሌ ባንክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከደር አህመድ ከባንኩ አመራሮች ጋር በመሆን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ አስረክበዋል።

ረይስ ማይክሮ ፋይናንስም አንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን በክልሉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ተገኝተው አስረክበዋል።

የክልሉ መንግሥት በጅግጅጋ ከተማ የገበያ ማዕከል ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ንብረታቸውን ካጡ ነጋዴዎች ጋር ውይይት ማካሄዱ ይታወሳል።

የገበያ ማዕከሉን በተሻለና በዘመናዊ መልኩ በመገንባት የክልሉ መንግሥት ከተመረጡ ኮሚቴዎችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ሁሴን ሃሺ በመድረኩ ላይ መግለጻቸውን ይታወሳል።
ሐምሌ 5 ቀን2015 ዓ. ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገቡ
****************************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ43ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጀሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ባጫ ደበሌን ጨምሮ ሌሎች የኬንያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

“የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ከሐምሌ 6 እስከ 8/2015 በሚካሄደው የምክር ቤቱ ስብስባ የሕብረቱ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የሕብረቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቀጣናዊ የአፍሪካ ተቋማት ኃላፊዎች እና እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ የሚቀይር ኩባንያ በኢንቨስትመንት ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገለፀ
************************
(ኢ ፕ ድ)

በነዳጅ የሚሰሩ ባለሶስት እግር እና ባለ አራት እግር ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ሲስተም የሚቀይር ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገልጿል።

የኢንቨስትመንቱ ባለቤት ኢንጂነር እሸቱ መኮንን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጋር መክረዋል።

የኢንቨስትመንት ሀሳቡ ባለቤትም ስለኢንቨስትመንት እቅዱ ማብራሪያ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

ኩባንያው በኡንዱስትሪ ፓርኮች ግዙፍ የመገጣጠሚያ ወርክሾፕ በመክፈት በአንድ አመት አንድ ሺህ ባለሶስት እግር እንዲሁም 200 ባለአራት እግር ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ሲስተም ለመቀየር የመጀመሪያ እቅድ እንዳለው ተገልጿል።

በውይይቱም ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ሽፈራው ኢንቨስትመንቱ እንደ ሀገር ያለው ጠቀሜታ ጉልህ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስትመንቱ መሳካት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከካሜሩን አቻቸው ጋር ውይይት አካሄዱ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ነገ መካሄድ በሚጀምረው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ በፊት ከካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጄዩን ምቤላ ጋር በሁለትዮሽ፤ በባለብዙ ወገንና በሁለቱ አገሮች የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ ውይይት አካሄደዋል።

የፖለቲካ ምክክር፤ በባለብዙ ወገን መድረክና በሌሎች ጉዳዩች በጋራ አብሮ መስራት ስለሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ውይይት በቅርቡ እንደሚካሄድ ተገልፆል ።

በሁለትዮሽ ውይይቱ ወቅት አቶ ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ አገራት ጋር ለሚኖረን ግንኘነት የበለጠ ትኩረትና ዋጋ እንሰጣለን ብለዋል። በተጨማሪ ስለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ገለፃ አድርገዋል።

በአገሪቱ የሰሜኑ ክፍል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት መንግስት በመርህ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ጋና በአለምአቀፍ መድረክ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም
በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)