Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከውጭ ጎብኚዎች ከ39 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሰስ ሆኗል
********************
(ኢ ፕ ድ )
በ2015 በጀት ዓመት በቱሪዝሙ ዘርፍ ከውጭ ጎብኚዎች የተገኘ ከ39 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ከተማዋ ኢኮኖሚ ፈሰስ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ባሕል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፋት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ዓይናቸው ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0kpwW3XdU6ZDer8UVYtdU2kuUhMzDAccr9fsEkx5k7F4fDnqhPjEiSsQKd8BB8tyAl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz
ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም‼️
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የተገነቡትን ከ 70 በላይ የመሸጫ ሱቆች የተካተቱበት የአቃቂ ሰብል ምርት ገበያ ማዕከልን እና በ140,000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሰፈረውን የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከልን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

ህዝባችንን በብርቱ እየፈተነ ያለውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ከጀመርናቸው ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የሰብል ምርት ገበያ ማዕከል፣ ህብረተሰቡ በቀጥታ ከአምራቹ እንዲሸምት የሚያስችለው እና ገበያውን በማረጋጋት ትልቅ አስተዋፅዖ ያለው ነው።

የምርት ገበያው ሱቆችን ጨምሮ መጋዘን፣ ወፍጮ ቤት እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት የተካተቱበት ሲሆን ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አምራቾች እና አርሶአደሮች የስራ እድል ይፈጥራል። የእንስሳት ልህቀት ማዕከሉ ደግሞ የዶሮና የወተት ላም እርባታ፣ የከብት ማደለብ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ እንዲሁም የምርት ማሳያና መሸጫ ቦታዎችን ያካተተ ነው።

ይህ የልህቀት ማዕከል በዘርፉ ለሚሰማሩ 485 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን የእዉቀት፣ የክህሎት፣ የምርምር፣ የግብዓት፣ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ምንጭ ሆኖ ያገለግላል። የነዋሪዎቻችንን የኑሮ ጫናዎች ለማቃለል እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በታማኝነትና በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን።
በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማዳበሪያና ባዮጋዝ የሚያመርት ፋብሪካ በ17 ሚሊዮን ዶላር እየተገነባ ነው
********************
(ኢ ፕ ድ )
ከኢንዱስትሪ ፓርክ የሚወጣውን ተረፈ ምርት እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ማዳበሪያና ባዮጋዝ የሚያመርት ፋብሪካ እየተገነባ መሆኑ የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ አስታወቀ።

የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ልኪሳ እንደገለጹት፤ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የግብርና ተረፈ ምርቶችን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ማዳበሪያንና ባዮጋዝን ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0unftp2QvD4m7axyxrPj2LbnEFNmDRRu7e9vRreq7jw7k83kgkuWgW8LdwzHj14qHl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz
የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተገነባው የተቀናጀ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ተመረቀ
***********************
(ኢ ፕ ድ)

በአቃቂ ቃሊቲ ኮዬ ፈጬ ወረዳ 10 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተገነባው የተቀናጀ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል።

በምረቃ መርሐግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይና የከተማ አስተዳደሩ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አብዱልቃድር ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ የዶሮና እንቁላል ማርቢያ የእንስሳት ማድለቢያንና የምርት ማሳያና መሸጫዎችን ጨምሮ አርሶ አደሩን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚረዱ የልማት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡

በማርቆስ በላይ

ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም