Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኮሚሽኑ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ለማቋቋም እየሰራ ነው
************
(ኢ.ፕ.ድ)

የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት እስከ ታህሳስ ወር ድረስ 75 ሺህ የተለያዩ የቀድሞ ተዋጊዎችን የማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የቀድሞው ተዋጊዎችን ትጥቅ የፈቱ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር እያደረገ ይገኛል።

የቀድሞ ተዋጊዎችን በኢኮኖሚ፣ በስነ-ልቦናና በማህበራዊ ጉዳዮች የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የመጣውን ስላም ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽ ኮሚሽነር አባሳደር ተሾመ ቶጋ ገልጸዋል።

በ2016 በጀት ዓመት 75ሺህ የቀድሞ ትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ማህበረሰቡ ለመመለስና ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታትና መልሶ በማቋቋም የሀገርን ሠላምና እድገት በማፈጠን በኩል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አመላክተዋል።

የኮሚሽነሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሻንቆ ደለለኝ በበኩላቸው ከሚቋቋሙት የቀድሞው 75 ሺህ ተዋጊዎች መካከል 50 ሺህ የሚሆኑት የህወሓት ተዋጊዎችና 25 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከሌሎች ክልሎች ናቸው ብለዋል።

የቀድሞችን ተዋጊዎችን ለማቋቋም የሲቪል ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ አመላክተዋል።

ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
በታደሰ ብናልፍ
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ዛሬ ማለዳ “ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል የትምህርት ንቅናቄ አስጀምረናል።

ትምህርት ዋነኛ የትውልድ ግንባታ ስራችን ነው። ተማሪዎቻችን በዕውቀትና በክሕሎት እንዲሁም በመልካም ስነምግባር የሚገነቡባቸው ትምህርት ቤቶች በአግባቡ እንዲደራጁ፣ ግብዓት ተሟልቶላቸው ከአዋኪ ነገሮች ጸድተው ለተማሪዎቻችን ምቹ የመማሪያ ስፍራ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎችን ሰርተናል።

ሆኖም አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች ናቸው። የትምህርት ስራ በመንግስት ብቻ የሚከወን አይደለም። ይልቁኑ ኅብረተሰቡ በባለቤትነት ሲሳተፍ ሩቅ የሚመስለው ይቀርባል፤ ዜጎችን ቀድሞ ከተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ጋር በማስተሳሰር በዕውቀት፣ በቁሳቁስና በገንዘብ እንዲደግፉ ማድረግ ትምህርት ቤቶቻችንን ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ያግዘናል። ባለሀብቶች የጀመሩትን ማኅበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ልምድ ሌሎች የኅብረሰተሰብ ክፍሎችም እንዲጋሩት ማድረግ፣ የበጎ ፈቃድ ስራን ባሕል ማድረግ አዲስ አበባ ማኅበራዊ ፍትህ የነገሰባት ከተማ እንድትሆን የምንሰራውን ስራ ለማሳካት አቅም ይሆነናል። ጸጋዎቻችንን እየለየን ተቋሞቻችንን በጋራ በማልማት የሁሉም የሆነች አዲስ አበባን ለመጪው ትውልድ እንገነባለን።

ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፣ ከሞሮኮ እንዲሁም ከቻድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር እና ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር በኬንያ ናይሮቢ ተወያይተዋል።

አቶ ደመቀ ሚኒስትሮች ስለ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተስፋ ሰጪ አፈፃፀም እና ኢትዮጵያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽኖችን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እየሰራች መሆኑን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፓንዶር ደቡብ አፍሪካ የሰላም ማስፈጸሚያ እቅዶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

የሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡሪታ ሞሮኮ ለኢትዮጵያ ልዩ ቦታ እንደምትሰጥ እና እንደ ግብርና እና ትምህርት ባሉ ዘርፎች በትብብር መስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል ።

በተጨማሪም አቶ ደመቀ መኮንን ከቻድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህማት ሳሌህ አናዲፍ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ሁለቱ ሚኒስትሮች ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

43ኛው የአፍሪካ ኀብር የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በኬንያ ናይሮቢ እየካሄደ ይገኛል ።

ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
#ኢፕድ_ድንቃድንቅ‼️

ትልቁ የኩላሊት ጠጠር ከስሪላንካዊው በህክምና ተወግዷል

ኩንጌህ ይባላል፤ ሲሪላንካዊ የ62 ዓመት የዕድሜ ባላፀጋ ነው። በጉብዝናው ወራትም አገሩን በውትድርና ያገለገለ ጡረተኛ የቀድሞ ወታደር ነው።

ይህ ሲሪላንካዊ ጤንነቱ እንደቀድሞው አልሆን ቢለው ጊዜ ከእለታት በአንዱ ቀን ወደ ወታደሮች ሆስፒታል ያመራል።

አስፈላጊውን ምርመራ ካካሄደ በኋላም ሀኪሞቹ የኩላሊት ጠጠር እንዳለበት ይነግሩታል፤ በፍጥነትም በህክምና መወገድ አለበት ሲሉ አከሉለት።

ሲሪላንካዊው በሀኪሞቹ ምክረ ሃሳብ ተስማምቶም ለቀዶ ጥገና ዝግጁ ሆነ።

የሆስፒታሉ ሀኪሞችም በዶክተር ኩጋዳስ ሱታርሻን እየተመሩ እአአ ሰኔ 1 ቀን 2023 ከሲሪላንካዊው ኩላሊት እስካሁን ከሰው ልጆች ከተወገዱት ጠጠሮች ሁሉ በርዝመቱም፣ በስፋቱም ሆነ በክብደቱ ትልቅ የሆነውን የኩላሊት ጠጠር ማውጣት ቻሉ።

ይህ የኪላሊት ጠጠር ርዝመቱ 13.37 ሴ.ሜ (5.26 ኢንች) እና 10.55 ሴ.ሜ (4.15 ኢንች) ስፋት እና 800 ግራም (1.76 ፓውንድ) ክብደት ያለው መሆኑ በሀኪሞች ልኬት ተረጋገጠ።

እስካሁን ከተመዘገቡት የኩላሊት ጠጠሮች መካከልም ትልቁ የኩላሊት ጠጠር ተብሎ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሊመዘገብ ቻለ።

ከዚህ በፊት እአአ በ2008 ይህ የዓለም ሪከርድ ተይዞ የነበረው በፓኪስታናዊው ዋዚር መሀመድ ሲሆን በወቅቱም 620 ግራም የሚመዝን የኩላሊት ጠጠር ነበር የተወገደለት፡፡

ከኩንጌህ የተወገደው የኩላሊት ጠጠር ከቀኝ ኩላሊቱ ሲሆን ቀዶ ጥገናውን ያደረጉት ዶክተር የኩጋህ ኩላሊት አሁንም በመደበኛነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የኩንጌህ የውስጥ የሠውነት ክፍሎቹ በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑንም ሀኪሙ ተናግረዋል።

ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም
በሀይማኖት ከበደ