ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
**********************************************
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን አምባሳደር ከሆኑት ኤፍጌኒ ተረክህን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው ወቅት የሩሲያ ከተሞች ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው የትብብር መንገዶች ዙሪያ መምክራቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያና ጀርመን የ25 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ጀርመን ለምርትና ግብይት ሰንሰለት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት የሚውል የ25 ሚሊዮን ዩሮ (የ1.5 ቢሊዮን ብር) የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ ስነስርአት ተፈራረሙ፡፡
የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው ሲፈርሙ በጀርመን መንግስት በኩል የጀርመን የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ህብረት ቡድን ዳይሬክተር ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ ፈርመዋል፡፡
የፋይናንስ ድጋፉ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃምና በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በዝናብ ተጠቅመው ክፍተኛ ምርት ለሚያመርቱ አካባቢዎች ከአየር ንብረቱና ከስነምዳሩ ጋር የተጣጣመ ዘላቂ የምርት እድገትና የግብይት ሰንሰለት ለማጠናከር የሚውል ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በተለየ ትኩረት የሚያደርገው በአዝርእትና ጥራጥሬ ምርቶች ላይ ሲሆን አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር፣ የግብርና መሳሪያዎች፣ የመረጃና የዘመናዊ የግብርና አመራራ ስልት ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም በምርት ግብይቱ ሰንሰለት ተዋናይ የሆኑ ባለድርሻዎችን አቅም በማጎልበት ላይ ነው፡፡
በምርትና ግብይቱ አስተዋጽኦ ያላቸውን የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ የግብርና ልማት ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርጥ ዘር ተቋማትና የፕሮጀክት አስፈጻሚ አካትን አቅም ማጎልበትም የፕሮጀክቱ አላማ መሆኑ ታውቋል፡፡
በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የኢትዮጵያና የጀርመን የሁለትዮሽ ትብብር ከአንድ ምዕተ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረ ጠንካራ ወዳጅነት መሆኑን አመለክተው የጀርመን መንግስት ኢትዮጵያ የነደፈችውን ሁለተኛውን የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሸሻያ አጀንዳና የ10 አመቱን መሪ የልማት ዕቅድ እንደሚደግፍ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሀምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሽልማት ተበረከተላቸው
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በ13ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማት የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እንግሊዝ ለንደን በተካሄደው የአፍሪካውያን የስኬታማዎች ሽልማት ትናንት ምሽት ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ ስነ ስርዓት ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል ።
የአሸናፊነት ሽልማቱ ኢጋድ በአካባቢው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ላደረገው አስተዋፅኦ መሆኑን ተገልፆል ፤ ይህ ሽልማት ለስኬታማ ተግባር የተሰጠ ዕውቅና መሆኑን ሸላሚ ድርጀቱ አስታውቋል ። ከብዙ የኢጋድ ስኬቶች ውስጥ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ የተደረገው ጥረት የሚጠቀስ መሆኑ ተመላክቷል ።
የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማቶች ለአህጉሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለሚያደርጉ በአፍሪካ ውስጥ ታዋቂ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን እውቅና በመስጠት እና በማክበር የአፍሪካን የላቀ ደረጃ የሚያከብር ዓመታዊ የሽልማት ሥነሥርዓት ነው።
ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ዛሬ 24 የስፖርት ማዘውተሪያዎችንና የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን ከ410 ሚሊዮን ብር በላይ ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አዲስ አበባን ለዛሬና ለነገው ትውልድ ምቹ ለማድረግ፣ በከተማችን ልጆች እንደ ልባቸው የሚቦርቁባት ፣ በየአካባቢያቸው በቂ የመጫወቻ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ባበረከቱልን "የመደመር ትውልድ" መፃሀፍ የሰጡንን አደራ ተቀብለን እና ቃላችንን ጠብቀን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ 7 ቱን የወጣት የስፖርት ማዘውተሪያ እና የህፃናት መጫወቻ በ110 ሚሊዮን ብር "ከመደመር ትውልድ" መፅሃፍ ሽያጭ ባገኘነው ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ቀሪዎቹ 17ቱ ፕሮጀክቶች ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ከ300 ሚሊዮን በላይ በሆነ ወጪ የገነባቸው ናቸው ።ይህም የከተማችን ልጆች በአካል እና በአእምሮ የበለጸጉ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ የሰጠነውን ትኩረት ያሳያል።
በዚህ በጀት ዓመት ብቻ በከተማችን እስካሁን ድረስ ከ5,000 በላይ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለመረጠን ህዝብ በትጋትና በታማኝነት ማገልገላችንን አረጋግጠናል።