Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሽልማት ተበረከተላቸው
**********************
(ኢ ፕ ድ)

በ13ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማት የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እንግሊዝ ለንደን በተካሄደው የአፍሪካውያን የስኬታማዎች ሽልማት ትናንት ምሽት ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ ስነ ስርዓት ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል ።

የአሸናፊነት ሽልማቱ ኢጋድ በአካባቢው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ላደረገው አስተዋፅኦ መሆኑን ተገልፆል ፤ ይህ ሽልማት ለስኬታማ ተግባር የተሰጠ ዕውቅና መሆኑን ሸላሚ ድርጀቱ አስታውቋል ። ከብዙ የኢጋድ ስኬቶች ውስጥ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ የተደረገው ጥረት የሚጠቀስ መሆኑ ተመላክቷል ።

የአፍሪካ አሸናፊዎች ሽልማቶች ለአህጉሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ለሚያደርጉ በአፍሪካ ውስጥ ታዋቂ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን እውቅና በመስጠት እና በማክበር የአፍሪካን የላቀ ደረጃ የሚያከብር ዓመታዊ የሽልማት ሥነሥርዓት ነው።

ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ዛሬ 24 የስፖርት ማዘውተሪያዎችንና የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን ከ410 ሚሊዮን ብር በላይ ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አዲስ አበባን ለዛሬና ለነገው ትውልድ ምቹ ለማድረግ፣ በከተማችን ልጆች እንደ ልባቸው የሚቦርቁባት ፣ በየአካባቢያቸው በቂ የመጫወቻ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ እንዲኖራቸው ለማድረግ ባበረከቱልን "የመደመር ትውልድ" መፃሀፍ የሰጡንን አደራ ተቀብለን እና ቃላችንን ጠብቀን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ 7 ቱን የወጣት የስፖርት ማዘውተሪያ እና የህፃናት መጫወቻ በ110 ሚሊዮን ብር "ከመደመር ትውልድ" መፅሃፍ ሽያጭ ባገኘነው ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::

ቀሪዎቹ 17ቱ ፕሮጀክቶች ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ከ300 ሚሊዮን በላይ በሆነ ወጪ የገነባቸው ናቸው ።ይህም የከተማችን ልጆች በአካል እና በአእምሮ የበለጸጉ ሆነው እንዲያድጉ ለማድረግ የሰጠነውን ትኩረት ያሳያል።
በዚህ በጀት ዓመት ብቻ በከተማችን እስካሁን ድረስ ከ5,000 በላይ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለመረጠን ህዝብ በትጋትና በታማኝነት ማገልገላችንን አረጋግጠናል።
የተጠያቂነት ሥርዓት አለመኖር ለመንግሥት ንብረት ብክነት ምክንያት ሆኗል
********************
(ኢ ፕ ድ)
የተጠያቂነት ሥርዓት አለመኖር ለመንግሥት ንብረት ብክነት ምክንያት እንደሆነ የግዢና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ እስካሁን የመንግሥት ንብረት ያለአግባብ ያስቀመጠ ወይንም አገልግሎት የማይሰጥ ንብረትን በወቅቱ ያላስወገደ ተጠያቂ የሚሆንበት የሕግ አግባብ ...
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02Tz4F8PBfkoiN99B8SkcKLNF5ZCXMWYS4wcLVJJfd3uXvgv5qRx7uAgL55TquAEiXl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz
በትግራይ ክልል 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል በተያዘው ክረምት 6 ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሥራ መጀመሩን የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ገለፁ።

የቢሮው ዳይሬክተር አስተባባሪ አቶ ተስፋይ ተክለሃይማኖት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት፤ ከፌዴራል መንግሥት እና ከበጎ አድራጊዎች በተገኘ እገዛ በያዝነው ክረምት ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02V5WP6u3dJTFMT45amG8qcRScMan8hYtvciDqPQ39o3mhMgHuwpchyYuFVDKZ33VQl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz
በኦሮሚያ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል
👉ከሦስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አስራ አንድ ወራት በስድስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በፕሮጀክቶቹ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሀመድዚያድ ገለቶ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ባለፉት አስራ አንድ ወራት በስድስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ንጹህ ....

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02AbigFv5SHQJ59TeBrZ2KEpRjqD5sB5egFKq965jkRr6R8GNka4PKZ9wETnVQ74fnl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz