በኦሮሚያ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል
👉ከሦስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አስራ አንድ ወራት በስድስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በፕሮጀክቶቹ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሀመድዚያድ ገለቶ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ ባለፉት አስራ አንድ ወራት በስድስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ ንጹህ ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02AbigFv5SHQJ59TeBrZ2KEpRjqD5sB5egFKq965jkRr6R8GNka4PKZ9wETnVQ74fnl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz

#ኢፕድ_ድንቃድንቅ ‼
የዓለማችን ረጅሙ ዘፈን🎼
ብዙውን ጊዜ ብዙዎቻችን የምናዳምጠው አንድ ዘፈን ርዝማኔው ከሶስት እስከ አምስት ደቂቃ፤ ቢረዝም 10 ደቂቃ እንደሆነ ይታወቃል።
እአአ "ከ2013 እስከ 2018 ባሉት አመታት በቢልቦርድ ላይ ከተቀመጡ ሙዚቃዎች መካከልም አማካይ የአንድ ዘፈን ርዝማኔ ከሶስት ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ወደ 3 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ መቀነሱን ኳርትዝ በ2019 ባወጣው መረጃ አስነብቧል።
ረጅሙ ዘፈን ተብሎ የነበረውም የፍቅር ዘፈን ሲሆን፤ የ10 ደቂቃ ቆይታ እንደነበረው ዘገባው አመላክቷል። አልፎ አልፎም ከዚህ ዘለቅ ያለ ርዝማኔ ያላቸው ዘፈኖች ታይተዋል።
የብዙ ሙያዎች ባለቤት የሆነው ህንዳዊው ጸሐፊ፣ ተመራማሪ እና አነቃቂ ንግግር አድራጊዊው ዶ/ር ጃጋዴሽ ፒላይ ከዚህ የተለየ ስራውን ይዞ ብቅ ብሎ፤ ዓለምን አስደምሟል።
ያሰበውን ለማድረግ ባደረጋቸው ውጣ ውረዶች ከተጋፈጠው ረጅም ጉዞ በኋላ፤ ዶ/ር ፒላይ ረጅምም ብቻ ተብሎ የሚገለጽጸውን ሳይሆን በጣም ረጅም የሆነውን ዘፈን ይዞ ብቅ ብሏል።
የዶክተር ፒላይ ዘፈን ርዝማኔ ዓለምን ጉድ አስብሎ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይም ሊሰፍር ችሏል።
ይህ ባለ ሪከርዱ ዘፈን 138 ሰዓት ከ41 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ርዝመት ያለው መሆኑን ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ያገኘነው መረጀጃያሳያል።
ይህ የዓለማችን ረጅሙ ዘፈን አምስት ቀናት ሳይቋረጥ መደመጥ የሚችል ነውም ተብሏል።
የዘፈኑ ግጥም ከ15 ሺህ በላይ ስንኞች ያሉት ሲሆን፤ ዘፈኑን አቀናብሮ ለመጨረስ የአራት ዓመታት ከ63 ቀናት እድሜን የወሰደ መሆኑም ተገልጿል።
ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓም
በሙሳ መሀመድ

በአዲስ አበባና አካባቢዋ 495 አደጋዎች ማጋጠማቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በተጠናቀቀዉ የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ አበባና አካባቢዋ 495 አደጋዎች ማጋጠማቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ እንደገለጸው፤ ከደረሱት አደጋዎች ውስጥ 326 የእሳት አደጋዎች ናቸው። ቀሪዎቹ ከእሳት ዉጪ ያጋጠሙ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ናቸው ብሏል።
በደረሱት አደጋዎች ምክንያት የ110 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ 165 በሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሷል።
864 ሚሊዮን 416 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ ዘጠኝ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረትንም ማዳን መቻላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።
ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ .ም

የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት እየተከናወነ ነው
*************^
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የሚሾሙ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት እየተከናወነ ነው።
ለእነዚሁ አባቶች ሥርዓተ ጸሎተ አስኬማ በዋዜማው ተከናውኗል።
በዓለ ሢመቱ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ምዕመናን በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ሢመተ ኤጲስቆጶስነት እየተፈጸምላቸው ያሉት ዘጠኝ አባቶች በሥርዓተ ቤተክርስቲያን በተቀመጠው መሠረት በዘጠኝ አህጉረ ስብከት የሚመደቡ ናቸው።