Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

በቴክኔክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆቻችን በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናችውን 6ሺህ 244 ተመራቂዎች ዛሬ አስመርቀናል። የተመረቃችሁ ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስ ያላችሁ፤ ከተማችሁ ከናንት ብዙ ትጠብቃለች።

ተመራቂዎች የቀሰማችሁትን ዕውቀትና ክህሎት ተጠቅማችሁ ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች የስራ ዕድል የምትፈጥሩ፣ ተወዳዳሪና ጥራት ያለው ምርት በማምረት ሀገር የምታኮሩ ትጉህ ዜጋ ለመሆን በርትታችሁ ስሩ።

ፈጣሪ አኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም
"እናታችን በብዙ ልፋት እኛን ለወግ ለማረግ አብቅታናለች፤ እሷ ዛሬ ለዚህ በመብቃቷ በጣም ደስተኛ ነኝ"
- ወጣት ሚኪያስ ይማነ
*****
(ኢ ፕ ድ)

"እናታችን ለፈታ እኛን አሰተምራ ለወግ ለማዕረግ አብቅታናለች፤ ዛሬ እሷ በተራዋ ለዚህ በመብቃቷ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ እኔም በተራዬ ላስመርቃት ነው የመጣሁት" ሲል እናቱን ለማሰመረቅ የመጣው ወጣት ሚኪያስ ይማነ ተናግሯል።

የወጣት ሚኪያስ ይማነ ወላጅ እናት ወይዘሮ ምህረት ወልደማርያም በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ተመርቀዋል።

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 6ሺህ 244 ሰልጣኞችን በሚሊኒየም አዳራሽ በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ አንዷ የሆኑትን ወላጂ እናቱን ሊያስመርቅ የተገኘው ወጣት ሚኪያስ ይማነ፣ እናታችን በብዙ ልፋትና መከራ አልፋ እኛን አስተምራ አድርሳናለች፤ እሷ በተራዋ ለዚህ በመብቃቷና በዚህ ደስታ ላይ ተሳትፌ የእናቴን ደስታ በማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ ሲል ለኢፕድ ተናግሯል።

ወጣት ሚኪያሰ ለኢፕድ እንደገለጸው፣ እናታችን ሳትማር ለፈታ እኛን ለወግ ለማዕረግ አብቅታናለች እኔ ደግሞ በተራዬ ላስመርቃት ነው የመጣሁት ይላል።

ከእናቴ የተረዳሁት ትምህርትን እድሜ እንደማይገድብ ነው ያለው ወጣት ሚኪያስ የእናቴ ጥንካሬ፣ አልበገር ባይነትና ለዚህ ደረጃ መድረስ ለቀጣይ ሕይወቱን ትልቅ ስንቅ እንደሚሆንለትና ብዙ ነገር እንደተማረበት ነግሮናል።

ሌሎች እናቶች ከእኔ እናት በመማር ወልደን ከብደን ልጆቻችንን ብቻ ካስተማርን በቂ ነው የሚለውን ሀሳብ መቅረፍ አለባቸው፤ ምክንያቱም ሁሉም ነገር ካለፈ በኋላ እንዳዲስ የመጀመር እድሉ ስላላቸው ነው ይላል ወጣት ሚኪያሰ።

ለመማር እድሜ አይወስንም የሚለው ወጣት ሚኪያሰ እናቶቻችን ትልቅ ለውጥ ልያመጡ እንደሚችሉ በመረዳት ተምረው ዕራሳቸውንም ሀገራቸውንም ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

የዛሬ ተመራቅና የወጣት ሚኪያስ ይማነ ወላጅ እናት ወይዘሮ ምህረት ወልደማርያም፣ ከአዲስ አበባ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ተመርቅያለሁ፡፡ ነገር ግን ሶስት ልጆችን ወልጄ ያለአባት አስቴምሬ ለወግ ለማረግ አብቅቼ የልጅ ልጆቼን ማየቴ ለዛሬዋ ቀን ለመድረስ እንዳላገዳቸው ይናገራሉ ።

ሰው ሲማርነው ትልቅ ደረጃ የሚደርሰው ያሉት ወይዘሮ ምህረት ሌሎች እናቶች ችሎታው እያላቸው ቤት ከሚቀመጡ እኔን በማየት እንዲማሩና ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ፈልጋለው ብለዋል፡፡

በቃልኪዳን አሳዬ

ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ተፈራረመዋል።

ስምምነቱ በአገራቱ በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች ተላልፈው እንዲሰጡ ማድረግ የሚያስችል ማእቀፍ መፍጠር የሚያስችል መሆኑን በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር ማእቀፍ ዳይሬክተር አቶ የሱፍ ጀማዎ ተናግረዋል።

በስምምነቱ የተቀመጡ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ተፈላጊዎቹ ተላልፈው ይሰጣሉ።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከቱርክ፣ ከአረብ ኤምረቶች፣ ቻይና፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳና ከሱዳን ጋር ተመሳሳይ ምምነት አላት ብለዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክልሉ ከጎብኚዎች አንድ ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር አግኝቷል
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክልሉን ከጎበኙ ቱሪስቶች አንድ ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለጸ።

የክልሉ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት ከጎብኚዎች በተለያየ መልኩ ሁለት ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፤ አንድ ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል። ይህም የእቅዱን 70 በመቶ ያሳካ ነው።

በበጀት ዓመቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ክልሉን መጎብኘታቸውን የሚናገሩት ኃላፊው፤ ቢሮዉ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን በማበረታታት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ አንድ ነጥብ 3 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ክልሉን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105966